የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ግለ ታሪክ


ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ግለ ታሪክ
አመሠራረት

የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የተመሠረተው 1997 . ነው፡፡ ሲዳማ ቡና በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የሚገኙ ወጣቶችን በስፖርት በማሳተፍ የአካባቢውን ህዝብ የሚወክል ጠንካራ ቡድን ማቋቋም በሚል ህሳቤ በጥቂት ስፖርት ወዳድ ወጣቶች የተቋቋመ ቡድን ነው፡፡        
 ዳራ በሲዳማ ልዩ ዞን የአንድ ወረዳ ስያሜ ስም ነው፡፡ ክለቡ ሲመሰረትም የነበረው ስያሜ ‹‹ዳራ ክለብ›› የሚል ነው፡፡ ይሁንና ክለቡ በ1999ዓ.ም የገንዘብ ችግር ስለገጠመው የስም ለውጥ ለማድረግ ተገዷል፡፡ በዚህም መሰረት ክለቡ በ1999ዓ.ም በኢትዮጲያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ለመካፈል የገጠመውን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ ሲል ለዞኑ ምክር ቤት ባቀረበው የዕርዳታ ጥያቄ መሠረት የክለቡ ስያሜ ‹‹ሲዳማ ዳራ›› ሊባል ችሏል፡፡ ይሁን እንጂ ክለቡ በዚህ ስያሜ ቢሆንም ብዙ መዝለቅ አልቻለም፡፡
 ክለቡ በክልል ክለቦች ውድድር ወደ ብሄራዊ ሊግ የመሳተፍ ዕድልን አገኘ፡፡ ይህ ውድድር ደግሞ ከክልል ክልል በመዘዋወር የሚደረግ በመሆኑ ከፍተኛ ውጪ ይጠይቃል፡፡ ይህን ወጪ ደግሞ ዞኑ ብቻዬን የምቋቋመው አይደለም በማለቱ ለሦስተኛ ጊዜ የስም ለውጥ በማድረግ ዛሬ ያለውን ስያሜ እንዲይዝ ተደርጓል፡፡
 የሲዳማ ልዩ ዞን በቡና ልማት ዘርፍ ከሚታወቁ የሀገራችን አካባቢዎች አንድዋ ናት፡፡ ስለሆነም አብዛኛው የአካባቢው ህብረተሰብ በቡና ልማትና ንግድ ዘርፍ የተሰማራ ነው፡፡ ከቡና ንግድ ጋር በተያያዘ በርካታ ባለሀብቶችም በዚህ ዞን ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም የስፖርት ክለቡን የገንዘብ ችግር በቀጣይነት ለመቅረፍና ክለቡን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የክለቡ ስያሜ የዞኑንና የነጋዴውን ማህበረሰብ ያማከለ መሆን አለበት በሚል የክለቡ ስያሜ ‹‹ሲዳማ ቡና›› ሊባል ችሏል፡፡ በዚህም መሰረት የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብን በባለቤትነት እያስተዳደሩት የሚገኙት የሲዳማ ልዩ ዞንና በሲዳማ በቡናው ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ ሲዳማ ቡና ዛሬ ያለውን ስያሜ ያገኘው በ1999ዓ.ም መጨረሻ ነው፡፡
አደረጃጀት
        የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ በሲዳማ ወጣቶችና ስፖርት /ቤትና በቡናው ንግድ ዘርፍ በተሰማሩ ባለሀብቶች የሚተዳደር ቡድን ቢሆንም በስርዓትና ደንብ የተቀረፀ አደረጃጀት የለውም፡፡ ክለቡ በአሁኑ ወቅት የሚመራውበሲዳማ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ነው፡፡                                                                                                                                                                                                                                      በአጠቃላይ ክለቡ ማንኛውንም እንቅስቃሴ የሚያከናውነው በውሰት በተሾሙ የኮሚሽኑ ሠራተኞች ነው፡፡ አሁን ባለው የክለቡ አሰራር የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ መንግሰቱ ሳሳሞ የስፖርት ክለቡ ፕሬዝደንት ናቸው፡፡ የክለቡን ማንኛውንምእንቅስቃሴ በአብዛኛው የሚወስኑት እሳቸው ናቸው፡፡ በቀጣይነት ግን ክለቡ ራሱን ችሎ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ህዝባዊ አደረጃጀት እንዲኖረው ህግና ስርዓት እየተቀረፀ መሆኑንና በቅርቡም ይፋ እንደሚሆን ከክለቡ ሰዎችያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአሰልጣኞች ቡድን አባላት
.
ስም ዝርዝር
የስራ ድርሻ
1
አቶ ክሩቤል ዘካሪያስ
ሰብሳቢ
2
አቶ ፈቀደ እሸቴ
አባል
3
ተካልኝ ጀብር
አባል
4
አቶ ታረቀኝ አሰፋ
ዋና አሰልጣኝ
5
አቶ ካሳሁን ገብሬ
ምክትል አሰልጣኝ
6
አቶ አበባው በለጠ
የህክምና ባለሙያ
7
/ ትሩፋት ወርቁ
የቡድን መሪ
 sidama-coffee-team-sportaddis






ዋና ቡድን አባላት ዝርዝር
.
ስም ዝርዝር
የስራ ድርሻ
1
ሲሳይ ባንጫ
ግብ ጠባቂ
2
አዱኛ ፀጋዬ
ግብ ጠባቂ
3
ሞገስ ታደሰ
ተከላካይ
4
መኩሪያ ደሱ
ተከላካይ
5
ደረጀ ፍሬው
ተከላካይ
6
ሚካኤል ጆርጆ
አጥቂ
7
ሲሳይ አማረ
አጥቂ
8
አብድራዛቅ ናስር
ተከላካይ
9
ነፃነት ገብሬ
አጥቂ
10
ምትኩ ሰኣ
አማካኝ
11
አመሌ ምልኪያስ
አጥቂ
12
ወንድማገኝ ተሾመ
አጥቂ
13
ዳግም ተርፋሳ
ግብ ጠባቂ
14
አሸናፊ አደም
አጥቂ
15
ዘርዓይ ሙሉ
አማካኝ
16
ሙጂብ ቃሲም
አጥቂ
17
እርቅይሁን እንድሪያስ
ተከላካይ
18
ቢያድግልኝ ኤልያስ
አማካኝ
19
ቢንያም አድማሱ
አማካኝ
20
መንግስቱ ታደለ
አማካኝ
21
አዲሱ አላሮ
አማካኝ
22
መስቀሌ መንግስቱ
አጥቂ
23
ሄኖክ አየለ
አጥቂ
24


25


 በጀት
 2004. ውድድር ዘመን የክለቡ አጠቃላይ በጀት 3.5 000.000 ብር ነው፡፡ ክለቡ ይህን በጀት ከሲዳማ ወጣቶችና ስፖርት /ቤት፤ከቡና ነጋዴዎችና ከገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እንደሚሸፍን ያገኘነው መረጃያመለክታል፡፡
 ዓርማ
 የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የራሱ መለያ ዓርማ አለው፡፡ የሲዳማ ዞን በለምነቱና በቡና አብቃይነቱ በብዛት የሚታወቅ ነው፡፡ የክለቡ ዓርማም ይህን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ዓርማውም የቡና ፍሬን የያዘ ቅጠል ነው፡፡አረንጓዴው ቅጠል የሲዳማን ዞን ለምነት ሲያመለክት ፍሬው ደግሞ በዞኑ የቡና ምርት በስፋት እንዳለ የሚያንፀባርቅ ነው፡፡
 የመወዳደሪያ መለያ
 ክለቡ ሁለት አይነት የመወዳደሪያ ማሊያ አለው፡፡ የመጀመሪያው የክለቡ መወዳደሪያ ማሊያ ቀለም አረንጓዴ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቀይ በነ ነው፡፡ ለዘንድሮ ውድድር ዘመን ያስመዘገበውም እነዚህን ቀለም ያላቸውማሊያዎች ነው፡፡ የሁለቱ ማሊያ ቀለሞች በክልሉ ያለውን ለምነትና ሠላም ያንፀባርቃል በሚል እንደተመረጠም ይነገራል፡፡
 የሀገር ውስጥ ውድድር ተሳትፎና ውጤት
 አጭር የምስረታ ዕድሜ ያለው ሲዳማ ቡና በሀገር አቀፍ ደረጃ መወዳደር የጀመረው 2000. ነው፡፡ በብሄራዊ ሊግ ሁለት ዓመት 2000-2001 በፕርሚየር ሊግ ደግሞ ከ2002ዓ.ም ጀምሮ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ ክለቡበእስካሁን የሀገር ውስጥ ውድድር ተሳትፎ 2001. የብሄራዊ ሊግ ዋንጫ አሸናፊና የኮከብ አሰልጣኝና ተጨዋች ተሸላሚ ለመሆን ከመቻሉ ውጪ በፕርሚየር ሊጉ ተመሳሳይ ስኬትን ማግኘት አልቻልም፡፡
 የኢንተርናሽናል ውድድር ተሳትፎና ውጤት
 ክለቡ በእስካሁን ጉዟው በኢንተርናሽናል ውድድር የመሳተፍ ዕድልን አላገኘም፡፡
dagne-sidama-sportaddis
የመወዳደሪያና ልምምድ ሜዳ
 ሲዳማ ቡና የሊግ ውድድሩን የሚያከናውነው በይረጋለምና ሀዋሳ ስታዲየሞች ነው፡፡ ልምምዱን የሚያከናውነውም በእነዚህ ሜዳዎች ነው፡፡ የክለቡ የመጀመሪያ የመወዳደሪያና ልምምድ ሜዳ ይርጋለም ስታዲየም ነው፡፡ይርጋለም ስታዲየም የሲዳማ ዞን ወጣቶችና ስፖርት /ቤት ንብረት ነው፡፡ ስታዲየሙ ለተመልካች መቀመጫነት የሚያገለግል ምቹ የመቀመጫ ስፍራ የለውም፡፡ የመጫወቻ ሜዳውም አመቺ አይደለም፡፡ ስለሆነም ዘንድሮ ቡድኑበይረጋለም የሚያደርገውን ጨዋታ ወደ ሃዋሳ በመዛወር የእድሳት ስራ በማከናወን ላይ ነው፡፡ በቅርቡም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 ደጋፊ
 ሲዳማ ቡና በሜዳው በተለይም ይርጋለም ሲጫወት ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ተመልካች ወደ ስታዲየም በመግባት ቡድኑን ያበረታታል፡፡ ቡድኑ በዚህ ከተማ ግጥሚያውን ሲያደርግ የጨዋታው ፊሽካ የሚነፋው የኢትዮጲያ ህዝብመዝሙር ከተዘመረ በሆላ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ የይርጋለምን ተመልካች ከሌሎች ለየት ያደርገዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ቡድኑ ግጥሚያውን በሀዋሳ ስታዲየም ሲያከናውንም በርካታ ደጋፊ ወደ ሀዋሳ ይጓዛል፡፡ የአካባቢው ነዋሪ በተለይበአሁኑ ጊዜ ክለቡን በሁለንተናዊ መልኩ ለመደገፍ ከፍተኛ መነሳሳትን እያሳየ ቢሆንም የተደራጀ የደጋፊ ማህበር የለውም፡፡ ክለቡ በቅርቡ ይፋ በሚያደርገው አዲስ መዋቅር ግን ደጋፊውም በክለቡ ስራ አመራር ቦርድ ውስጥ ድምፅስለሚኖረው ደጋፊውን በማህበር የማደራጀት ስራ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን ከክለቡ የቅርብ ሰዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 የማሊያ ስፖንሰር
 ክለቡ አስካሁን ድረስ የማሊያው ላይ ስፖንሠር ተጠቅሞ አያውቅም፡፡ ወደፊት ግን ለመጠቀም ዕቅድ ይዟ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
 የስፖርት ክለቡ ሙሉ አድራሻ
 የሲዳማ ስፖርት ክለብ /ቤት የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ ሲዳማ ዞን ወጣቶችና ስፖርት /ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡
ስልክ፡- 0462-202963

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር