በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉን በመተሳሰብና በመረዳዳት ተከበረ


አዋሳ ነሐሴ 11/2004 በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ኢድ አል ፈጥር በዓልን አቅመ ደካሞችን በመርዳት፣ በተለያዩ ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡትንና የታመሙትን በመጠየቅ በሰላምና በደስታ ማክበራቸው ተገለፀ፡፡
የእምነቱ ተከታዮች መካከል ሀጂ ሰይድ አደም፣ መሃመድ ኑር፣ ከድር ዴዳና ወይዘሪት ነዕማ አማን በሰጡት አስተያየት የእስልምና ሃይማኖት በሰው ልጆች መካከል ታማኝነትን፣ ትዕግስትን፣ ፍቅርንና ማህበራዊ አንድነትን የሚያሰፍን ነው፡፡
የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ለእምነታቸው ታማኝ፣ ለፈጣሪያቸው ታዛዥ በመሆን ለሀገር ዕድገትና ሠላም ዘብ መቆም እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡
ሙስልሙ ህብረተሰብ ለዘመናት ያዳበረውን ከሌሎች እምነትት ተከታዮች ጋር ተከባብሮና ተቻችሎ በፍቅር አብሮ የመኖር ባህሉን በበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል፡፡
በዓሉን እንደወትሮ ሁሉ ሃይማኖቱ በሚያዘው መሰረት በሰላማዊና በመልካም ሁኔታ ለማክበር መዘጋጀታቸውን ገልፀው፣ አንዳንድ ኃይማኖትን ሽፋን አድርገው ድብቅ አጀንዳቸውን ለማራመድ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችንም አጋልጠው ለህግ እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል፡፡ የእስልምና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ አፍራሽ ተልዕኮ አንግበው ከእምነቱ ውጪ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችንአጥብቀው እንደሚያውግዙም ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ በየቀበሌው የሚካሄደው የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አባላት ምርጫ በሠላማዊ መንገድ እንዲካሄድ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስተያየት ሰጪዎቹ ማረጋገጣቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር