የኣቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በሲዳማ ሲጧጧፍ የነበረው እስር ጋብ ማለቱ ተገለጸ


የሲዳማ ክልል ጥያቄን ኣንግቦ በተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት በምል ሃዋሳ ከተማን ጭምሮ በተለያዩ የሲዳማ ወረዳዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ይካሄድ የነበረው ግለሰቦችን የማሰር እንቅስቃሴ ጋብ ብሏል።

በኣለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች መታሰራቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ከታሰሩት ማካከል ካላ ብርሃኑ ሀንካራን ጨምሮ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ሃዋሳ ከተማ ከምገኘው ፍርድ ቤት የቀረቡ ወደ ኣስር የሚሆኑ ግለሰቦች ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ ማረሚያ ቤት ተመልሰዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ መለስ ዜናዊን ይተካሉ ተብሎ የሚጠበቁት የኣገሪቱ ምክትም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሲዳማ የክልል ጥያቄን በተመለከተ በምኖራቸው ኣቋም ላይ የተለያዩ ኣስተያዬቶች እየተሰጡ ነው።

ያነጋገርናቸው ካላ ደመቀ ዳንጋሞ እና ቤላሞ ባሻ የሃዋሣ ከተማ ነዋሪዎች እንደምሉት ከሆነ፤ ኣቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሲዳማ ህዝብ ጋር የኖሩና ሲዳማን ህዝብ ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆናቸው ለክልል ጥያቄው ኣዎንታዊ ምላሽ ልሰጡ ይችላሉ።

ይህንን ኣስተያየት የተቃረኑት ካላ ኣስፋ ላላንጎ እና ካላ ናኦራ ቡኤ በበኩላቸው፤ ኣቶ ኃይለማርያም ካለፉት ኣስር ዓመታት ጀምሮ ጸረ ሲዳማ ኣቋም ያላቸው እና ከኣስር ኣመታት በፊት በርካታ ሲዳማዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እንዲገደሉ ካደረጉት የደቡብ ክልል ባላስልጣናት መካከል ኣንዱ በመሆናቸው የክልል ጥያቄውን በተመለከት የሚኖራቸው ኣቋም ኣዎንታዊ ልሆን ኣይችልም ብለዋል።

ክቡራን የብሎጋችን ኣንባቢያን የሲዳማ ክልል ጥያቄ እና የወደፊት እጣ ፋንታ በተመለከተ ያላችሁን ኣስተያየት በሚከተለው ኣድራሻ ላኩልን፦nomonanoto@gmail.com   

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር