በሀዋሣ ከተማ ዙሪያ የሚሰራው የተፋሰስ ልማት ሥራ ውጤት እየታየበት መሆኑ ተገለፀ፡፡


በሀዋሣ ከተማ ዙሪያ የሚሰራው የተፋሰስ ልማት ሥራ ውጤት እየታየበት መሆኑ ተገለፀ፡፡በተፋሰስ ልማት በተደራጁ ወጣቶች ሠሞኑን ከ25 ሺህ በላይ የሀገር በቀል የዛፍ ችግኞች  በታቦር ተራራ ላይ ተክለዋል፡፡
ተክለው በኢየሩሳላም የህፃናትና የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት የተከናወነ መሆኑም ተመልክቷል፡፡የጽህፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ማስረሻ ክብረት እንደገለፁት ድርጅቱ በከተማው በአከባቢ ጥበቃ ሥራ በተደጋጋሚ ባከናወነው ተግባር ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችሏል፡፡
ተከላውን በይፋ ያስጀመሩት የሃዋሣ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በላይ በቀለ በበኩላቸው የከተማውን ልማት ለማፋጠንና ፀዳቷን ለመጠበቅ በአከባቢ ጥበቃ ሥራ ላይ የተሠማሩ ወጣቶች ያበረከቱት አስተዋፅፆ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፤ አስተዳደሩም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
በዕለቱ ከኢየሩሳሌም ህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ለ3 ማህበራት ከ75 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የእርሻ መሣሪያዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡በተከላውም ከከተማ አስተዳደሩ፤ ከየትምህርት  ቤት የአከባቢ ጥበቃ ክበብ አባል ተማሪዎች፤ በማህበር የተደራጁ ወጣቶችና ሌሎችም ተሣታፊ ሆነዋል፡፡ ባልደረባችን በረከት ጌታቸው እንደዘገበችው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/11NehTextN204.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር