በሲዳማ ባህል አዳራሽ የተሰበሰቡ ሰዎች አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ተቃወሙ

ሲዳማን በተመለከተ ኢሳት ያቀረበውን ዜና(የመጨረሻ ዜና) እዚህ ላይ ይመልከቱ 

ሐምሌ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  
ኢሳት ዜና:- የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት በጥንቃቄ የመረጣቸው የሲዳማ ተወላጆች በዛሬው እለት በሲዳማ ባህል አዳራሽ ተሰብስበው የክልሉ መንግስት ያቀረባቸውን ጥያቄዎች ህዝቡ እንዲጠይቅ አደርገዋል።
12 ጥያቄዎች ለባለስልጣናት የቀረቡ ሲሆን፣ አቶ ሽፈራው ” የሲዳማን ጥያቄ አሁን ለማቅረብ እንደማይቻል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሽሎአቸው ወደ ስራ ሲመለሱ እንደሚያቀርቡት ተናግረዋል።
በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ፣ የስብሰባውን አካሄድ ለመቃወም የሞከሩም ነበሩ።
አዋጅ አዋጅ የሚል ርእስ አለው ወረቀት ዛሬ በአዋሳ ሲበተን እንደነበር ዘጋቢያችን ገልጧል።
ዛሬ በተበተነው  ወረቀት ላይ ” ጊዜው ወደ መጨረሻው በመቃረቡ ይህንን ትውልድ ገዳይና ዘር ጨራሽ አፈናና እጅ አዙር አገዛዝ ሁከት በሌለበት በሰለጠነ መንገድ አንድ ላይ በመሆን ” እንቃወመው የሚል መልክት ተላልፎአል።
ኢሳት ባለፈው ሳምንት ዛሬ በሲዳማ በሀል አዳራሽ ስብሰባ እንደሚካሄድ ዘግቦ እንደነበር ይታወሳል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር