በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብቡን አስታወቀ፡፡



ጽህፈት ቤቱ በአመቱ ለመሰብሰብ ያቀደው 6 ሚሊዮን ብር ሲሆን  ከ9 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ሊሰበሰበብ መቻሉን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምስራቅ በቴ ገልፀዋል፡፡የአመቱ እቅድ ክንውን አፈፃፀም 98 ነጥብ 2 ከመቶ መሆኑንና ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ3 ሚሊዮን 61ዐ ሺህ 196 ብር ብልጫ ማሳየቱን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
ገቢው ሊሰበሰብ የቻለው ከቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆኑ ገቢዎች እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢዎች መሆኑን አብራርተዋል፡፡ለገቢው መጨመር የግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግብር የመክፈል ግንበዛቤ እያደገ መምጣት፣ የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነት መፈጠርና የወረዳው መስተዳደርና ባለድርሻ አካላት ከገቢ ሰብሳቢው ጽህፈት ቤት ጋር የተቀናጀ ሥራ በማከናወናቸው መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይ አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በማፈላለግ የተጀመረውን የ5 ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አቶ ምስራቅ መናገራቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር