በሀዋሳ ከተማ በበጀት ዓመቱ ከ6 ሺህ በላይ ባለቤት አልባ ውሾች ተወግደዋል



ሀዋሳ፣ ሀምሌ 27፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ6 ሺህ በላይ ባለቤት የሌላቸው ውሾች መወገዳቸውን የሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ ፅፈት ቤት ገለፀ።
ውሾቹ ባለቤት አልባና በእብድ ውሻ በሽታ ተጠቂ በመሆናቸው ምክንያት በሽታው በሰዎችም ላይ እየተስፋፋ የመጣበት ሁኔታ በመኖሩ ተወግደዋል ብሏል ፅፈት ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት።
ከዚህ ባሻገርም በከተማዋ የሚገኙ ባለቤት ያሏቸው ውሾችን የእብድ ውሻ በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠቱን ነው ያስታወቀው።
በእብድ ውሻ የተነከሱ ሰዎችም በ48 ስአት ውስጥ ወደ ህክምና ተቋማት ከመጡ በሽታው የመዳን እድሉ ሰፊ በመሆኑ በከተማዋ የሚገኙ የጤና ተቋማት አገልገሎቱን እየሰጡ እንደሚገኙ ኤልሳቤጥ ካሳ ዘግባለች ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር