የሲዳማ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጠ፤ የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄ ያለ ምንም ቅድምያ ሁኔታ አፋጣኝ መልስ እንዲያሰጠው ጠየቀ



ከሲዳማ ፖለቲካ ድርጅቶች ኀብረት፡ ስለሲዳማ የወቅቱ ሁኔታን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

ተንኰለኞችና ወንጃለኞች በተፈጥሮአቸው የገሙ ስለሆኔ እነሱን ያካተተ መንግሥት፡ አገርንና መንግሥትንም ጭምር ያገማል፡ ላል ሚካኤል ጋድ ስለመንግሥት ተመራማሪ። የወያኔ አገዛዝም በኢትዮጵያ በዚህ መልክ የሚታይ ነው። ወያኔ የሕዝቦች አብሮ መኖርንና ሰላማዊ ሕይወትን የማይቀበል ስለሆነ እንደታመሰ ለ20 ዓመታት የቆየ ሲሆን፡ ሀገራዊ ራዕይ የሌላቸው የወንጃለኖች ጥርቃሞ ነው። የሲዳማ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት ይህንን ከተረዳ የቆየ ቢሆንም አሁን የደረሰንበት ደረጃ በጣም አደገኛ እየሆነ በመምጣቱ፡ ወያኔ በአስቸኳይ ተመንግሎ መውደቅ ያለበት መሆኑን ህብረቱ አሰምሮበታል።
ድርጅታችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሲዳማ በመካሄድ ላይ ያለውን ሁኔታ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ፡ ለመላው ኢትዮጵያውያን ለማሳወቅና እንደ ስልቻ በትዕቢት የተወጠረው ወያኔ ከዚህ ተንኰለኛ ተግባሩ ይቆጠብ ይሆን በማለት ለማሳሰብ የወጣ መግለጫ ነው።
ሴራኛው ወያኔ በሲዳማ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረው ዛሬ ሳይሆን የአዲስ አበባን ቤተመንግሥት ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡በዚህም በሲዳማ ውስጥ ተወልዶ ያደገውን እጅጉ ገ/ሚካኤል የተባለውን ትግሬ በመመልመልና በመሾም የሲዳማ ታጋዮችን እነፊሣ ፍቾን በስውር አስገድሎዋል። ቀጥሎም የተቃሚዎችን ጐራ ለማዳከም አንዳንድ ለጥቅማጥቅም የተገዙ ግላሰቦችን በመናኛ ገንዘብና መሬት (ቤት መሥሪያ ቦታ) በመስጠትና በመደለል ወደ ወያኔ እንድቀላቀሉ በማድረግ ትግለችን ለማኰለሸት ሞክረዋል: ግን አልተሰካላቸውም።
ከዚህም ሌላ፡ በረከት ስሞን ኤርትራዊውን አማራ፡ ኩማ ደመቅሣ ትግሬውን ኦሮሞ ብለው እንደ ሾሙው ሁሉ በሲዳማ ውስጥ ተወልደው ያደጉትን፡ 1ኛ ሽፈረው ሽጉጤ፡ 2ኛ ደሴ ደልኬ፡ 3ኛ ሳሙኤል ሼባን ለሥርዓቱ ታመኝ የሆኑትን የወላይታ ብሔረሰብ አበላት ሲዳማ ናቸው በማለት በኰታ ሾሞቸአል። ይህ ሁሉ ሤራ ሲዳማን በመቆጣጠር፡ የህዝብን ዲሞክራሲያዊ ትግል ለማኰለሻትና ለመምታት ነበር ዓለማው።
የዛሬው የውጭ ጉዳይና ም/ጠቅላይ ሚንስተር ተብየው ኃ/ማሪያም ዳሣለኝ ለዚህ ቦታ የበቀው፡ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ለማስከበር ጥያቄ አቅርበው ተገቢውን መልስ ባለማግኘታቸው ተቃውሞአቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ ከወጣው ሕዝብ መካከል 100 ሲዳማዎችን ያስጨፈጨፈና ሬሳቸውን በአውሬ ያስበላው ፋሽስት ግለሰብ ነው፡ ይህንን ሥልጣን ያገኘው በዚህ በገማ ተግባሩ ነው። ዛሬም እስከመጨረሻው የ100ዎቹ ንጹሐን ደም ኃ/ማሪያም ደሣለኝን ትጣራለች።
ዛሬ በሲዳማ ላይ እየተካሄደ ያለው ሴራ እንደት ነው? በሞት ጐዳና ላይ በጣር እየተጓዘ ያለው ወያኔ፡ የሲዳማን ሕዝብ ትግል ለመጨፈለቅ እየሞከረ ያለ ሲሆን፡ ታክትኩን ቀረብ ብለን ብንመለከት፡ በአርባጉጉና በሐረር ላይ የአማራ ብሔር አባለትን  ፍጭፎ የአከልዳማን ድራማ እንደሠረውና፡ እንዲሁም በጂማና በሸዋ አብያተ ክርስትያናትን በማቃጠል፡ እስላሞች አደረጉ በማለት ክርስትያንና እስላምን ለማጋጨትና እንዲሁም የእስልምና ተከታዮችን ለመከፋፈል እንደሞከረው ዓይነት፡ ሲዳማን ከወላይታና ከሌላውም ኀብረተሰብ ለማጋጨት በተወከዮቹ በእነሽፈራው ሽጉጤና ኃ/ማሪያም ደሣለኝ በተገዙና ከወላይታ አረካ ወረዳ
ተጭነው በመጡት አማከይነት /ሲዳማ ከአዋሣ ከተማ ይውጣ/ የሚል መፈክር አስይዘው ሰላማዊ ሰልፈ አስደርገዋል። ከዚህም በተያያዘ በቅጥረኛው ወያኔ ካድሬዎች አማከይነት፡ ሠረተው በሰላማዊ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎች እንድፈናቀሉ ተደርገዋል።
እንዲሁም ከዚያ ቀደም ብለው የሐዋሣ አስታዳደር ሠራተኞችን ለሴራቸው እንዲያመቻቸው ስለፈለጉ በሙስና ስም ወደ ወህኒ እንድወርዱ ተደርገዋል። ለመሆኑ ከእነሽፈራው ሽጉጤ ጀምሮ እስከ በሰበሰው የወያኔ ቍንጮ ድረስ በሙስና የተዘፈቁት ዓለም ያወቀላቸው የእነመለስ በለቤት አዜብ መስፍን እያሉ፡ የወረዳ ሠራተኞች በሙስና መታሠራቸው የፍትህ አልባነት በስተቀር ሌላ ለማለት አይቻልም።
በወያኔ ተግባር የሲዳማ ሕዝብ ተቆጥቶአል፡ እነሱ ግን በማስፈራራት የተንኰል ዓለማቸውን ተግባራዊ ለማድረግ፡ ሲዳማን ከመንደር እስከ መንደር ወደ ወታዳራዊ ካምፕ ቀይረዋል። በገዛ መንደሩ ሰላማዊ ሕይወቱን እያናጉ ናቸው።
የሲዳማ ድርጅቶች ሕብረት በጉዳዩ ላይ በስፋት ከተወያያ በኋላ የሚከተሉትን ውሰኔዎች አስተላልፎአል፡
1ኛ/ የፈዴራል ጦር በአስቸኳይ ከሲዳማ ክልል እንድወጣ፡
2ኛ/ የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄ ያለ ምንም ቅድምያ ሁኔታ አፋጣኝ መልስ እንዲያገኝ፡
3ኛ/ በሲዳማ ሕዝብ ላይ በግፍ ግድያ ያካሄዱት ኃይለማሪያም ደሣለኝ፡ ሽፈራው ሽጉጤ፡ በረከት ስምኦንና ግብረ አበሮቻቸው በአስቸኳይ ለፍርድ እንድቀርቡ፡
4ኛ/ በወያኔ ሤራ በግፍ የታሠሩት የሐዋሣ ከተማ አስተዳደር ሠራተኞች በአስቸኳይ ተፈትተው ወደ ሥራ ገበታቸው እንድመለሱ፡
5ኛ/ በእስላም ተከታዮች ላይ የሚካሄደው አሰቃቂ ግድያና አፈና በአስቸኳይ እንድቆም፡
6ኛ/ በወያኔ ቅጥረኞች በመናኛ ጥቅም ተገዝተው፡ በሲዳማ ሕዝብ ላይ ትንኰላ የሚያከናውኑ የወላይታ ብሔረሰብ አበላት ከድርጊታቸው እንድቆጥቡ ድርጅቱ ያሳስበል።
ድል ለዴሞክራሲ ወዳዱ ሕዝብ
የሲዳማ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት



ምንጭ  http://www.sidamaliberation-front.org/

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር