ባለፈው ሳምንት ግጭት ተከስቶባቸው የነበሩት የማልጋ እና የወንዶ ገነት ወረዳዎች እየተረጋጉ መምጣታቸው ተገለጸ



በፈዴራል ፖሊስ እና በመልጋ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ  በወረዳው የነበረው ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት በመቀነስ ላይ ያለ ቢሆንም መንግስታዊ ስራዎች እንደቆሙ ናቸው።

ግጭቱን ምክንያት ኣድርጎ ወደ ወረዳው የገባው የመንግስት የጸጥታ ኃይል እስከኣሁን ድረስ ጉጉማን ጨምሮ በወረዳው እንደሰፈረ ይገኛል።

ኣንዳንድ የወረዳው ነዋሪዎች የጸጥታው ኃይል ከወረዳው በኣስቸካይ ለቆ እንዲወጣ በመጠየቅ ላይ ናቸው።

ባለፈው ሳምንት በወረዳው ህዝብ እና በፊዴራል ፖለስ ኃይል መካከል በተፈጠረው ግጭት ከሁለቱም ወገን ሰዎች መጎዳታቸው ይታወሳል።

በተያያዘ ዜና የማልጋ ወረዳ ግጭት ተከትሎ በወንዶ ገነት ወረዳ ተፈጥሮ የነበረው ኣለመረጋጋት እንዲሁ በመስከን ላይ ነው።  

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር