በመልጋ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በወንዶገነትም ተመሳሳይ ተቃውሞ ተነስቷል።

New


ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ከሶስት ቀናት በፊት በሲዳማ ዞን በመልጋ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ ወደ ወንዶገነትም ተዛምቶ፣ የባሻ ወረዳ ሊቀመንበር መገደሉንና የወረዳው መስተዳደር መኪና መቃጠሉን ዘጋቢያችን ገልጧል። በግጭቱም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ፣ ነገር ግን በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች መቁሰላቸው ታውቋል።

ሁለቱ ወረዳዎች ኩታገጠም ሲሆኑ፣ በመልጋ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው ባለስልጣናት ህዝቡን ለማሳመን ወደ ታች ወርደው በሚነጋገሩበት ጊዜ ነው ግጭቱ የተነሳው።

በእነዚህ አካባቢዎች ያለው አብዛኛው ሰው በከብት ርቢ የሚተዳደር የነፍስ ወከፍ መሳሪያ የታጠቀ መሆኑ ፣ በወረዳ ባለስልጣናት እና በፖሊሶች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዳባባሰው ዘጋቢያችን አክሎ ገልጧል።

መልጋ እና ወንዶገነት ወረዳዎች አሁንም በፌደራል ልዩ ሀይል ቁጥጥር ሲሆኑ፣ ዜናውን እስካጠናከርንበት ሰአት ድረስ ውጥረት እናደለ ዘጋቢያችን ገልጧል።

በመልጋ ወረዳ ወረዳ ሰሞኑን በተነሳው ግጭት 12 የፌደራል ፖሊስ አባላትና ከ20 በላይ ሲቪሎች መቁሰላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የዞኑ ነዋሪዎች ክልል የመሆን ጥያቄያችን መልስ እስካላገኘ ድረስ ግብር አንገብርም በማለት ጠንካራ አቋም ይዘዋል።

የክልሉ ምክርቤት ከትናንት በስቲያ ስብሰባ ቢያካሂድም በዞኑ ስላለው ግጭት ምንም ውሳኔ ሳያሳልፍ ተበትኖአል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር