የሲዳማ ኣመራሮች በቅርቡ በሚከበሩት የሲዳማ ቋንቋ ስምፖዚዬ እና የዘመን መለዎጫ ፊቼ በኣላት ኣከባበር ዙሪያ ተፋጠዋል፤ሁለቱም በኣላት ከሃዋሳ ከተማ ውጪ እንዲከበሩ ሳይደረግ ኣይቀርም እየተባለ ነው


የውስጥ ኣዋቅ ምንጮች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትወርክ እንደተነገሩት፤ ባለፈው ሳምንት መገባዳጃ ላይ በክልሉ ፕሬዚዳንት ሰብሳቢነት በበኣላቱ ኣከባበር ዙሪያ ላይ በመከረው ዝግ ስብሰባ የተለያዩ ሃሳቦች ተንጸባርቀዋል።

የዞኑ ኣስተዳዳሪን እና የከተማዋ ከንቲባ በተሳተፉበት በዚህ ስብሰባ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሁለቱም የሲዳማ ህዝብ በኣላት ከሃዋሳ ከተማ ውጪ በወረዳዎች እንዲከበሩ የሚል ሀሳብ ያነሱ ሲሆን፤ ለዚህም የጸጥታ ጉዳይን እንደምክንያትነት ኣንስተዋል።

በኣላቱ በሃዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይከበሩ ማድረግ በቅርቡ ከከተማዋ ኣስተዳደር ጋር በተያያዘ ተነስቶ ለነበረው ህዝባዊ ንቅናቄ መባባስ ምክንያት ይሆናል በሚል ኣንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች የፕሬዚዳንቱን ሀሳብ የተቃዎሙ ሲሆን፤እንደኣማራጭም የከተማዋን ጸጥታ ሁኔታ ኣጠናክረው በኣላቱ ሃዋሳ እንዲከበሩ መደረግ ኣለበት ብለዋል።

ኣንዳንድ የሲዳማ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ በሲዳማ ህዝብ ዘንድ በደማቅ ሁኔታ የሚከበሩትን እነዚህን በኣላት ከሃዋሳ ከተማ እንዳይከበሩ መከልከልም ሆነ መፍቀድ ለህዝባዊው ንቅናቄ የራሳቸው የሆነ ኣዎንታዊ ገጽታ ኣላቸው።

በኣላቱ ከሃዋሳ ከተማ እንዲከበሩ ከተፈቀደ በኣላቱን ለማክበር የሚሰባሰበው ህዝብ ከሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ጋር በተያያዘ ያላቸውን ቅሬታ ለመግለጽ ኣጋጣሚ የሚፈጥር ሲሆን፤ መከልከሉ ደግሞ መንግስት ለህዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ኣለመሆኑ እንድታወቅ ያስችላል ብለዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር