ለሲዳማ ልማት ድርጅቶች መንኮታኮት ደኢህዴን ተጠያቂ ነው



ደኢህዴን ለሲዳማ ህዝብ ካለው ስር የሰደደ ጥላቻ የተነሳ የሲዳማ ልማት ድርጅቶችን በሰው ሃይልም ሆነ በገንዘብ ኣቅም እንዲዳከሙ ካደረጋቸው ወዲህ ታማኝ ካድሬዎች እየተፈራረቁ የግል ህይወታቸውን የሚገነቡበት አንጡራ ሃብታቸው ከመሆን ባሻገር፤ጠያቂ የሌለባቸው ነፃ የግል ኑሮ መገንቢያ የኢኮኖሚ ቀጠናዎች እና የተለያዩ ወንጀሎችን ሰርተው ነገር ግን ለስርዓቱ/ለደኢህዴን አስፈላጊ የሆኑ ግለሰቦች ጊዜያዊ ማገገሚያ፣ መደበቂያና መሸሸጊያም ጭምር ሆነዋል፡፡
የደኢህዴን መሰሪ አመራር የድርጅታቸው ዋናው ዓላማና ግብ የሲዳማን ህዝብ መብት መግፈፍና ማዋረድ እስከሚመስል ድረስ ህዝባችንን የበደሉ፣ ያዋረዱ፣ ወደ ኋልዮሽ እንድያድግ ያደረጉና ለዚህም አሁንም ድረስ እየተጉ ያሉ ስለሆነና ያደረሱብን በደል እንዲህ በቀላሉ ተገልጾ የማያልቅ ቢሆንም ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ አኳር አንኳሩን እንደሚከተለው ገልጸናል፡፡
ሲህዴድ ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ ለደኢህዴን ባስረከበበት ማግስት የደኢህዴን አመራር የመጀመሪያውን ጸረ ሲዳማ እርምጃ የነበረው የአይሪሽ መንግስት በሲዳማ መስተዳድር የሚያደርገውን የልማት ድጋፍ እንዲያቋርጥ ማድረግ ነበር እና የአይሪሽን መንግስት እርዳታ በተለያየ መንገድ በማዋከብ እርዳታ ፕሮግራሙ ምንም ዓይነት የልማት ስራዎቹን የማቆሚያ ዕቅድ /Phase out Strategy/ ለማዘጋጀት ዕድልና ጊዜ እንኳን ሳይሰጡት በፍጥነት እርዳታው እንዲቋረጥ ማድረግ ነበር፡፡
የተጀመሩ የልማት ስራዎች ባሉበት ቆሙ፡፡ የልማት ድጋፍ በማስቆም ላይ ብቻ ያልተወሰኑት ደኢህዴኖ ች፤በመቀጠልም የልማት ቀናዕ የሆኑ የብሔሩ የልማት ቀያሾችና መሪ ተዋናዮች የሆኑትን በተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶች የስም ማጥፋት ፕሮፖጋንዳ በመንዛት ከሃገር እንዲሰደዱ ማድረግ ነበር። እናም ይህንን መሰሪ ተንኮል በወራት ጊዜ ውስጥ አሳኩት፡፡ የአየርላንድ መንግስት ድጋፍ ያለ ቅድመ-ሁኔታ ሲቆም የልማት ስራዎችም ባሉበት ቆሙ፡፡ የሲዳማ ልማት አርበኞችም ከፍሎቹ ከስራቸው ታጋዱ ገምሶቹ ወደ ውጭ ተሰደዱ፡፡
ከዚያም በሃላ .ለሲዳማ ህዝብ የልማት ስራዎችን በዘላቂነት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ያግዛሉ ተብለው የተደራጁት የልማት ተቋማት በተለይም የሲዳማ ማይክሮ ፋይናንስና ሲዳማ ልማት ኮርፖሬሽንን ለማፍረስ ያልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም፡፡ ዛሬም ቢሆን ለህዝብ ልማት ደጋፊ ሳይሆን የደኢህዴን ታማኝ ካድሬዎች እየተፈራረቁ የግል ህይወታቸውን የሚገነቡበት አንጡራ ሃብታቸው እንጂ የሕዝብ ንብረቶች አይደሉም፡፡ ጠያቂ የሌለባቸው ነፃ የግል ኑሮ መገንቢያ የኢኮኖሚ ቀጠናዎች ሆነዋል፡፡ የተለያዩ ወንጀሎችን ሰርተው ነገር ግን ለስርዓቱ/ለደኢህዴን አስፈላጊ የሆኑ ግለሰቦች ጊዜያዊ ማገገሚያ፣ መደበቂያና መሸሸጊያም ጭምር ሆነዋል፡፡ 
የሲዳማ ልማት ማህበር በኢትዮጵያ ካሉ ግንባር ቀደም ማህበራት አንዱ ሲሆን የሕዝብ ልማት አጋርነቱን በተግባር ማሳየት የቻለው የሲዳማ ዞን መስተዳድር ሙሉ በሙሉ ከአስተዳደርና ፖለቲካ ስልጣን እስካልወጣበት ጊዜ ድረስ ብቻ ነበር፡፡ ሲህዴድ ማንነቱን አሳልፎ እንደሸጠ ደኢህዴን የወሰደው አፋጣኝ እርምጃ የሲዳማ ልማት ማህበር ያለውን ገንዘብ ወደ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ እንዲያዛውር ማስገደድ ነበር፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በብድር ስም የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ወስዶ ነገደበት፡፡ ማህበሩ ግን የበይ ተመልካች እንዲሆን ተፈረደበት፡፡ በዝቅተኛ ደረጃም ቢሆን የሚያገኛቸው ገቢዎች በማህበሩ እየተደጎሙ ማህበራዊ ችግራቸውን  እንዲቋቋሙ የተመደቡ ሠራተኞች መጧሪያነት የሚዘል አቅም እንዳይኖረው መንገዶች ሁሉ ተዘግተውበታል፡፡ 
ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ ሕዝቡ በቁጭት ማህበሩን መልሶ ለማቋቋም በመነሳሳት ከአርሶ አደር እስከ መንግስት ሠራተኛ የአንድ ወር ደመወዝ መዋጮ ድረስ ገንዘብ የተሰበሰበ ሲሆን ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ የልማት ስራ እንዲሰራ አልተፈቀደም፡፡ ሕዝቡ ያዋጣው በርካታ ሚሊዮን ብሮች በዝግ አካውንት በባንክ ተቀምጧልም ይባላል፡፡ ለነገሩ እንዴት ብሎ ነው ለልማት የተዋጣው ገንዝብ በዚግ ኣካውንት የሚቀመጠው? ህዝቡ ልማት በተጠማበት በኣሁኑ ጊዜ ስራ ላይያልዋለ ግንዘብ መቼ ነው ለህዝቡ የሚደርሰው? ጉዳዩ ኧረ መልስ ያለው ያስብላል ነገር ግን ሕዝባዊ ልማት ለማካሄድ የደኢህዴን መልካም ፈቃድ ይጠይቃልና እነሆ እስከ ዛሬ ስለዚህ ገንዘብ እንዲወራ አይፈለግም፡፡
እጅግ የሚያስቆጨውና የሚያሳዝነው ጉዳይ የሲዳማ ልማት ማህበር ቴሌቶን ለማዘጋጀት የሚያስችል አገር አቀፍ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ጥናታዊ ዝግጅት አጠናቅቆ የደኢህዴን መልካም ፈቃድ በመጥፋቱ የሲዳማ ልማት ጥናት ፕሮጀክት ሌሎች የታደሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ተጠቅመው ሃገር አቀፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን በማዘጋጀት ለህዝባቸው በጎ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሕዝባዊ የልማት አውታሮችን አጠናክረዋል፡፡
የሲዳማ ልማት ማህበር ግን በግዛ ከተማው የሌሎች ብሄሮች የልማት ማህበራት የተለያዩ ቴሌቶኖችን እና ህዝባዊ የመዋጮ ፕሮግራሞችን እያካሄዱ ለህዝባቸው የልማት ገንዝብ ሲያሰባስቡ እነርሱ ግን በሌሎች የመዋጮ ፕሮ ግራሞች ላይ ተወካይ ከመላክ ባሻገር ልማት ለተጠማው ህዝብ ምንም ሲያደርጉ ኣይታዩም።
የልማት ማህበሩ የስራ መኪኖችም ቢሆኑ ምን ሰርተው ጋራዥ እንደሚገቡ ባይታወቅም ከጋራዥ የሚወጡት  ለደኢህዴን ባለስላጣናት ቤት መስሪያ ድንጋይ ከማመላለስ ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር