ከኣስር ኣመት በፊት የክልል ጥያቄ ስላነሱ በመንግስት የጸጥታ ሃይል ስለተገደሉትን የሲዳማ ሰዎች የኣዲስ ዘመን ጋዜጣ ምን ጽፎ እንደነበር ያስታውሳሉ?




በአዋሳ ከተማ ባለፈው ዓርብ በህገ ወጥ ሰልፈኞችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ ያነሳሱ ፀረ ሰላም ኃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የሶስት ወረዳዎችና የአዋሳ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖትመሪዎች ጠየቁ።


በሲዳማ ዞን የሸበዲኖ፣ የቦረቻና የአዋሳ ዙሪያ ወረዳዎች እንዲሁም የአዋሳ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎች ትናንት በግጭቱ መንስኤ ላይ ለግማሽ ቀን ከተወያዩ በኋላ ባወጡት የአቋም መግለጫ "አዋሳ ልትሸጥ ነው፤ ሲዳማ ሊባረርነው" በማለት አሉባልታዎችን እየነዙ ህዝቡን ለህገ ወጥ ሰልፍ በማነሳሳት ለደረሰው ጉዳት ተጠያቂ የሆኑ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ኃይሎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።


ሁለት ፖሊሶችን ጨምሮ ለ15 ሰዎች ህይወት ማለፍና አንድ ፖሊስን ጨምሮ ለ25 ሰዎች ፈቃድ እስኪገኝና ሌሎች መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ሰልፉ እንዳይካሄድ የሀገር ሽማግሌዎች በሲዳማ ህዝብ ባህል መሰረት የሰልፉን አስተባባሪዎች ቢማፀኑም አስተባባሪዎቹ እምቢተኛ ሆነው ችግሩ እንዲፈጠር ማድረጋቸውን እነዚሁ የአገር ሽማግሌዎችተናግረዋል።


መንግሥት የህዝብን ሰላም፤ የልማት ተቋማቱንና የከተማዋን ደህነት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት የሀገር ሽማግሌዎቹና የሃይማኖት አባቶቹ ጠቁመው የሲዳማ ህዝብ ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በሰላምና በአንድነት መኖር እንደሚፈልግና ፀረ ሰላም ኃይሎች በተለይ ሲዳማን ከወላይታ ህዝብ ጋር ለማጋጨት የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚያወግዙ አስታውቀዋል።


ደኢህአዴግ-ኢህአዴግ የከተሞችን የወደፊት የልማት አቅጣጫ ለመወሰንያወጣቸውን የልማት ዕቅዶች እንደሚደግፉም ገልጸዋል።


የሀገር ሽማግሌዎቹና የሃይማኖት መሪዎች በግጭቱ በደረሰው ጉዳት በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጠው ወደየመጡበት አካባቢ ሲመለሱ ህብረተሰቡ ስለ ግጭቱ መንስኤ ግንዛቤ እንዲያገኝ እንደሚያደርጉ አመልክተዋል።


ህገ ወጥ ሰልፉን እንደቀሰቀሱ የተጠረጠሩ 12 ግለሰቦች ከትላንት በስቲያ በፖሊስ መያዛቸውን ምክትል አስዳዳሪው ገልጸው ቀሪ ተጠርጣሪዎችንለመያዝም ክትትሉ ቀጥሏል ብለዋል። ባለፈው ዓርብ ግጭቱ የተቀሰቀሰበትአካባቢ በአዋሳ ዙሪያ ወረዳ ልዩ ስሙ ሎቄ የተባለው ስፍራ ከአዋሳ ከተማ ከ5 እስከ 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።


ከአዲስ ዘመን ግንቦት 20 ቀን 1994
ምንጭ http://archives.ethiozena.net/%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5%E1%8D%A1%E1%8B%98%E1%88%98%E1%8A%95/%E1%88%9B%E1%8B%8D%E1%8C%AB/1994/%E1%8C%8D%E1%8A%95%E1%89%A6%E1%89%B5/20/%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5%E1%8D%A1%E1%8B%98%E1%88%98%E1%8A%95.19940920.1.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር