በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ የሚገኙ ግንባር ቀደም አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ተሸለሙ


በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ የሚገኙ  ግንባር ቀደም አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ተሸለሙ::አርሶ አደሮቹ ለሽልማት የበቁት በተጠናቀቀው የበጅ ዓመት በቡና ተክል፤ ሰብል ምርት እንዲሁም በእንስሳት እርባታና በባህላዊና ዘመናዊ መስኖ አጠቃቀም ረገድ የላቀ ውጤት በማስመዝገባቸውና መነሻ ካፒታላቸውም ከ5 መቶ ሺህ እሰክ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ማፍራት በመቻላቸው ነው::

የወረዳው የግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሌጣ ለገሰ ሽልማቱ ምርትና ምርታማነትን ከፍ ከማድረግ በተጨማሪ የማስፋት ስትራቴጂን አጠናክሮ በማስቀጠል የውድድር መንፈስን ማዳበር እነንዲያስችል  አስረድተዋል::

የሸበዲኖ ወረዳ ደኢህዴን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ታፈሰ በበኩላቸው የተዘጋጀውን ሽልማት ካበረከቱ በኋላ  እንዳሉት ያገኙትን ውጤት በማስጠበቅ በሚቀጥሉት ጊዜያትም የበለጠ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል::

የወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት ከአስተዳደሩ  ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሽልማት ስነ ስርዓት 99 ግንባር ቀደም አርሶ አደሮችና 38 የግብርና ባለሙያዎች እንደተሸለሙ ከወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል::

http://www.smm.gov.et/_Text/04HamTextN604.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር