የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ኣመራር ካላ ቤታና ሆጤሳ ሕዝቦች ነጻ የሆነችና የበለጸገች በዘር ያልተከፋፈለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መተባበር አለባቸው ኣሉ፤ ሲኣን በተለያዩ ጉባኤዎች ላይ የሲዳማን ህዝብ በመወከል ላይ ነው

በእንግሊዝ በተካሄደው ለኣዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ጉባኤ የተገኙት ካላ ቤታና ለተሰብሳቢዎች እንደተናገሩት፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በየትኛውም መንገድ ቢሆን ለመተባበር መንገድ ማግኘት አለብን።

መለስ ባሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኢትዮጵያውያንን እየተጠቀመ እንደሆነ ሁሉ እኛ ደግሞ ለመተባበር እርስበርስ መደጋገፍና መተጋገዝ አለብን ያሉት ካላ ቤታና፤  ሕዝቦች ነጻ የሆነችና የበለጸገች በዘር ያልተከፋፈለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መተባበር አለባቸው” ብለዋል።

 የጉባኤን ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦ 
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በእንግሊዝ

“የንቅናቄያችን የእንግሊዝ አገር ስብሰባ ስኬታማ ውጤቶች” ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ
ባለፈው ሳምንት መጠናቀቂያ አካባቢ በእንግሊዝ አገር ሪዲንግ ከተማ በአገራችን ስላለው ”የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የመሬት ነጠቃ እና የፖለቲካ መብቶች ረገጣ” የንቅናቄያችን የእንግሊዝ ንዑስ (chapter) የሁለት ቀን ስብሰባ አካሂዶ ነበር። በተለይ በስብሰባው መጠናቀቂያ ላይ ከዚህ በፊት ጎራ ለይተው እርስበርስ በዘር፣ በዓላማ፣ በአካሄድ፣ በፕሮግራም ወዘተ የነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ቡድኖች - የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሲዳማ ተወላጆች እንዲሁም ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ክርስቲያኖች፣ እስላሞች፣ የአንድነት ደጋፊዎች፣ የነጻ አውጪ ግንባሮች፣ የትጥቅ ትግል ደጋፊዎች፣ የሰላማዊ ትግል አራማጆች፣ ወዘተ - በአንድ ቦታ ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በስብሰባው መጠናቀቂያ ወቅት ሲተቃቀፉ፣ እርስ በርስ በፈገግታ ሲነጋገሩ እንዲሁም የግል መረጃዎቻቸውን ሲለዋወጡ መመልከቱ ብቻ የስብሰባውን ስኬት በግልጽ የሚያሳይ ነበር።
ከላይ እንደተገለጸው ንቅናቄያችን ይህንን ስብሰባ ያካሄደበት ዋንኛ ዓላማ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የአቶ መለስ አገዛዝ ከሚያካሂደው አምባገነናዊ ስርዓት ባሻገር ለሥልጣን መቆያ እንዲያመቸው የአገራችንን ለም መሬት ለተለያዩ የውጪ ድርጅቶች በነጻ ከመስጠት ባልተናነሰ መልኩ ነዋሪዎችን በማፈናቀል እያደረሰ ያለው የአንድን አገር ኅልውና ፈጽሞ አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ሕዝባችን ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግና ለተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲዘጋጅ ለማድረግ ነው። የስብሰባው አቅጣጫ ወዴት ሊሄድ እንደሚችል በእርግጠኝነት አስቀድሞ ለመገመት የሚያስቸግር የነበረ ቢሆንም በስብሰባው ላይ ንግግር ያደረጉት ግለሰቦች ግን በእያንዳንዱ ንግግራቸው የሁላችንም የጋራ ችግር የሆነውን ይህንን ጉዳይ በጋራ በመነጋገር፣ በመወያየት እና በመተባበር መፍትሔ ማምጣት እንዳለብን በአጽንዖት ሲናገሩ ተደምጠዋል። እንዲህ ዓይነቱ ተስፋ ፈንጣቂ አስተሳሰብና የትብብር መንፈስ ”ኢትዮጵያውያን አብረው ሊሠሩ አይችሉም” ሲሉ ለነበሩ የተናገሩትን ደግመው እንዲያስቡበት እንደሚያደርጋቸው እርግጠኞች ነን።

ስብሰባው የተከፈተው የንቅናቄያች አመራር አባልና የስብሰባው አስተባባሪ በሆኑት አቶ አቻሜ ሻና ነበር። እርሳቸውም ከደቡብ የኢትዮጵያ ክልል ተወላጅ እንደመሆናቸው ከዓመታት በፊት ወደ ንቅናቄያችን እንዲመጡና አሁን ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያደረጋቸው ”ከዘር ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ” የሚለውና ”ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ነጻ ሊሆን አይችልም” የተሰኙት የንቅናቄያችን ዋነኛ መርሆዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በመቀጠልም የንቅናቄያችንን ዋና ኃላፊ አቶ ኦባንግ ሜቶን በማስተዋወቅ ወደመድረኩ ጋብዘዋል።

አቶ ኦባንግም የስብሰባውን አዘጋጆች ካመሰገኑ በኋላ ”ንቅናቄያችን ሥልጣን ለመያዝ ዓላማ ያለው የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያውንን በአንድነት በማሰባሰብ በአገራችን ላይ ሰላም እኩልነት እና ፍትሕ እንዲመሠረት እንዲሁም ሁሉም የሚሳተፍበት የፖለቲካ ማኅበረሰብ መፍጠር” ነው ብለዋል። በመቀጠልም የንቅናቄያችን መመሪያዎች እንዴት በተለያየ ጠርዝ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በአንድ ጠረጴዛ ላይ በማምጣት በመተባበር እንዲሰሩ እንደሚያደር ሲያስረዱ ”በቁጥር ጥቂት የማይሆኑ ግለሰቦች ‹ኢትዮጵያ› በሚለው ስም መጠራት ወይም አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ በሆነው ሰንደቅ ዓላማ ሥር መታየት እንደማይፈልጉ” ተናግረዋል። ሆኖም ግን ”ኢትዮጵያ” የሚለው ስምም ሆነ ”የሶስት ኅብረ ቀለም” ውህድ የሆነው ሰንደቅ ዓላማ ማንንም ሰው እንዳልገደለ ካስገነዘቡ በኋላ ባለፉት ባገራችን ላይ በነበሩት አገዛዞች የተለያየ ችግር የነበረ ቢሆንም እዚያ ላይ ብቻ ማተኮር ለአሁኑ ችግራችን መፍትሔ እንደማይሆን ይልቁንም ወደፊት የሁላችንም መኖሪያ እንድትሆን ለምንፈልጋት ”አዲሲቷ ኢትዮጵያ” ያሉንን ቅራኔዎችና ልዩነቶች ወደኋላ በመተው ከፈጣሪ ለተሰጡን መብቶች መከበር መተባበር እንደሚገባ በአጽንዖት ተናግረዋል። አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ አገዛዝ ኢትዮጵያውያንን ”እኛ” እና ”እነርሱ” በማለት የከፋፈለ ቢሆንም ንቅናቄያችን ግን ”ኢትዮጵያ” በምትባለው አገር ውስጥ እንዲህ ዓይነቱ መከፋፈል ይቅርና ”ጠላት” በማለት ሰዎችን የምናገልል ሳንሆን ሁሉም ወደመተባበር እንዲመጡ በዓላማ ደረጃ እንደሚንቀሳቀስ ተናግረዋል።

ለሁለት ቀን በተካሄደው በዚህ ስብሰባ በርካታ ንግግሮች የተሰሙ ሲሆን የተወሰኑቱን ከዚህ እንደሚከተለው አጠር ባለ መልኩ እናቀርባለን።
አቶ አቻሜ ሻና፤ ከንቅናቄያችን የእንግሊዝ ንዑስ
”የአቶ መለስ አገዛዝ የተባበሩት መንግሥታት ስላወጣው የሚሊኒየም የልማት ዕቅዶች በተደጋጋሚ የሚያወራ ቢሆንም በርካታ ኢትዮጵያውያን ግን እነዚህ ዕቅዶች በተጨባጭ ምን እንዲያስገኙ የታቀዱ ስለመሆናቸው በቂ ግንዛቤ የላቸውም። እነዚህን ዕቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚሰጠው ዕርዳታም ሆነ ገንዘብ ለኅብረተሰቡ የረጅም ጊዜ ጥቅም በሚያስገኙ ተግባራት ላይ እየዋሉ አይደለም። ለምሳሌ የንጹህ ውሃ አቅርቦትን በተመለከተ አዲስ ከሚቆፈሩት ጉድጓዶች የሚወጣው የውሃ ጥራት አጠያያቂ ከመሆኑ ባሻገር ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በርካታ ሰዎች የተበላሸ ውሃ እየጠጡ እንደሆነ ነው። ከሚሊኒየም የልማት ዕቅዶች የሚመጣው ገንዘብ መዋል የሚገባው ጉድጓድ እየቆፈሩ ውሃ ለማውጣት ብቻ ሳይሆን ዘላቂነት ያለው ንጹህ ውሃ ማቅረብና ማከፋፈል እንዲሁም የውሃ ማጣራት ዕቅዶችን ለመተግበር ነው። ለምሳሌ ያህል በመዲናዋ አዲስ አበባ የሚገኙት የውሃ ጉድጓዶች በከፍተኛ ሁኔታ የተበከሉ ከመሆናቸው ባሻገር ከዚህ የሚገኘው ውሃ ለመጠጥነት ፍጆታ መዋል የማይችል ነው። በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ጥቃቅን ለሆኑና ፈጽሞ ዘላቂነት ለሌላቸው ፕሮጀክቶች ውሏል በማለት ”ዕድገት ተመዝግቧል” እንዲሁም ”ልማት ተፋጥኗል” እያለ በየጊዜው ሪፖርት የሚያደርገው የአቶ መለስ አገዛዝ በዕርዳታ የሚቀበለውን ገንዘብ ሕዝብን ለዘላቂነት በሚጠቅሙ ፕሮጀክቶች ላይ አለማዋሉ የእርዳታው ገንዘብ ለግል ጥቅም ለመዋሉ አንዱ ጠቋሚ ነው። ከዚህም ሌላ ጥቂት የሕወሃት ባለሥልጣኖች ከመጠን በላይ ሃብት እያጋበሱ አብዛኛው የአገራችን ሕዝብ ግን በድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆ ”መካከለኛ የገቢ ዕርከን ላይ” አሉ የሚባሉት እንኳን ቀን አንድ ጊዜ ተመግበው መዋላቸው ተዓምር እየሆነ የመጣበት ነው። ይህም በአገዛዙ ውስጥ የሚገኙት ለሕዝብ ደንታ የሌላቸው ከመሆኑ አልፎ በአገራችን ያለውን የሞራል መላሸቅ የደረሰበትን ደረጃ በጉልህ የሚያሳይ ነው። ለልማት በሚል ሽፋን ሕዝብ እየተራበ የአገራችንን አንጡራ ሃብት የሆነውን ለም መሬት በነጻ ከመስጠት ፈጽሞ በማይለይ መልኩ ለውጪ ባለሃብቶች መስጠት ፈጽሞ ዝም ልንለው የማይገባ ጉዳይ ነው። በየቀኑ እየተሰቃየና እየሞተ ላለው ሕዝባችን በፍጹም ጀርባችንን ልንሰጥ አይገባም” በማለት የብዙዎችን ስሜት የነካ ንግግር አቶ አቻሜ ሰጥተዋል።
አቶ ወንድሙ መኮንን፤ በእንግሊዝ አገር የሲቪክ ድርጅቶች
”በአሁኑ ጊዜ ህወሃት የኢህአዴግ ወኪል በሆኑ እየተጠቀመ የሥልጣን መሠረቱን እያሰፋው ይገኛል። ገበሬውን መቶ በመቶ በመቆጣጠር ለም መሬቱን በቁጥጥራቸው ሥር አድርገውታል። በአሁኑ ጊዜ የመሬት ባለቤትነት በኢትዮጵያ ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን አገዛዙ የመሬት ባለቤት በመሆኑ ገበሬው ምን ያህል አርሶ ያለማው ይሁን አይሁን ህወሃት የፈለገውን መሬት በፈለገው ጊዜ ለፈለገው ይሰጣል የሰጠውንም መልሶ ይወስዳል። ይህም ለህወሃት በገጠሪቱ የአገራችን ክልል ባለው ሕዝባችን ህይወት ላይ ያለውን ፍጹማዊ ቁጥጥር የሚያሳይ ነው። ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 90% የሚሆነው በህወሃት ቁጥጥር ሥር ሲሆን በባህሪው የአጥፊነት ጠባይ ያለው ይህ ድርጅት ሕዝባችንን መሳሪያ አልባ በማድረግ ራሱን እስከ አፍንጫው ማስታጠቁ በገሃድ የሚታይ ተግባር ነው። ኢትዮጵያውያን ወንድሞችና እህቶችን እርስበርስ በማጫረስ አገራችንን እየሸጠ ነው። የዚህን አጥፊ ድርጅት ተግባር ለመቋቋም ያለን ብቸኛ አማራጭ ሁላችንም በመተባበር አገራችንን ከማዳን በስተቀር ምንም አማራጭ የለንም” በማለት ሃሳባቸውን ቋጭተዋል።
ዶ/ር አረጋዊ በርሔ፤ ከትግራይ ኅብረት ለብሔራዊ ዴሞክራሲ
”ካሉብን ችግሮች መካከል አንዱ ምሁራን እርስበርሳቸው በመገናኘትና በመነጋገር አሁን ያለውን አሠራር በመጠቀም ለአገራቸው ዓላማ ማዋል አለመቻላቸው ነው። ይህ ዓይነቱ ችግር ወደኋላ እስከ 100 ዓመት ድረስ ይሄዳል - ምክንያቱም እስካሁን በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት ኖሮን አያውቅም። ህወሃት ለትግራይ ሰዎች ቆሞ አያውቅም፤ ይልቁንም መለስ የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ በአገሪቷ ውስጥ በየትኛውም ክልል ላስቀመጣቸውና ከየትኛውም ብሔር ለመጡ አሻንጉሊቶች ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች። አሁን የምናደርገው ለወደፊቱ መሠረት የሚጥል በመሆኑ ሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ማኅበራት ሁሉንም ሕዝብ ያካተተ ማንንም የማያገልል ኅብረት ሊፈጥሩ ይገባል። ይህ ሕዝብን መሠረት ያደረገ ትብብር በሕዝብ እንድንተዳደርና ለሕዝብ ተጠያቂ እንድንሆን ያደርገናል። ስለዚህ ምሁራን በትብብር መሥራት የሚቻልበትን መንገድ በማመቻቸት ለሕግ የበላይነት በቁርጠኝነት በመታገል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መርህ እንደሚለው ‹ለሰብዓዊነት› በጋራ መቆም አማራጭ የሌለው ነው” በማለት የመፍትሔ አሳባቸውን ጠቁመዋል።
ዶ/ር ሽጉጥ ገለታ፤ ከኦነግ
”ይህ በጣም ጥሩ ጅማሬ ነው። ይህ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚያደርገው ሌሎችንም የማሰባሰቡ ሥራ ‹ይበል› የሚያሰኝ ተግባር ነው። በብዙዎች ዘንድ ኦነግን አስመልክቶ የተዛባ አመለካከት እንዳለ የታወቀ ነው። እኛ ከሌሎች ጋር በመሆን የኮ/ሎ መንግሥቱን አገዛዝ በመጣል ለሁላችንም ነጻነት አብረን ታግለን ነበር። ከማንኛውም ዓይነት ጭቆና ነጻ መውጣት የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ እጅለእጅ በመያያዝ በእኩልነትና በፈቃደኝነት የተመሠረተ የፖለቲካ ኅብረት ለመፍጠር መንገዱን የሚጠርግ እንደሆነ ኦነግ ሁልጊዜ በአጽንዖት የሚያምንበት ጉዳይ ነው። ሆኖም ግን የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመጠቀም ተቀጣጣይነት ያላቸውን ግጭቶች እንዲፈጠሩ በማድረግ ለዘመናት ተቻችለው በሰላም አብረው የኖሩ ሕዝቦችን ሲያጋጭ እንደቆየ ግልጽ ነው።

ዛሬ ኢትዮጵያ በአንድ ግለሰብ ጨካኝ አምባገነናዊ ሥርዓት ቀንበር ሥር ትገኛለች። ስለሆነም ኢትዮጵያ ዛሬ በተስፋና ተስፋ በመቁረጥ እንዲሁም በለውጥና በመከፋፈል አጣብቂኝ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች። ምንም እንኳን እውነታው ይህንን ቢመስልም የሁላችንም ምርጫ ተስፋና ለውጥ እንደሚሆኑ ተስፋ አለኝ። ታዲያ ጥያቄው ይህ ለውጥ እንዲመጣና የተስፋ ብርሃን በሁሉም ውስጥ እንዲፈነጥቅ የምናደርግበት መንገዱ ምን ይሆን የሚለው ነው። እንዲያውም ጉዳዩን በፖለቲካ ቋንቋ ለመግለጽ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምንድር ነው ማድረግ ያለባቸው? የኦነግ ጥያቄ የነጻነት፣ የዴሞክራሲ፣ የፍትሕና የሰላም ጥያቄ ነው። ይህንንም ደግሞ አብዛኛዎቹ የተቃዋሚ ኃይሎች የሚጋሩት ሃሳብ ነው። ስለዚህ የህወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ በኅብረት ለመታገል የሚያግደን ምንም እንቅፋት እንደሌለ ይህ በግልጽ የሚያሳይ ነው። ምንም እንኳን ኦነግ ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም የተነሳ ቢሆንም የሌሎችም ሕዝቦች ጥቅም መከበር ግድ ይለናል። ስለዚህ የሕዝባችንን ጥቅም የምናስከብርበት መንገድ በመቀየስ ተባብረን ለመሥራት የምንችልበትን መንገድ እንቀይስ” በማለት የድርጅታቸው ተባብሮ ለመሥራት ያለውን ዓላማ ገልጽዋል።
አቶ ታደሰ ብሩ፤ ከግንቦት 7
”ልንጠይቃቸው የሚገባን ሦስት ጥያቄዎች አሉ፡- 1) ኢትዮጵያውያን ሁልጊዜ ተባብረን ለመሥራት የማንችለው ለምንድነው? 2) ብቃት ያለውና የተዋጣለት ኅብረት ለመመሥረት አስቸጋሪ የሆነብን ለምንድነው? 3) አሁን ካለንበት አዙሪት ለመውጣት ምን ማድረግ አለብን? ኅብረት ለመፍጠር ችግር የሚሆኑ ቢያንስ አምስት ምክንያቶች አሉ፡- 1) ለመተባበርና ለመቀራረብ የጸና ፍላጎትና አለመኖር፤ 2) የታማኝነት ቃልኪዳን ማጣት፤ 3) አለመተማመን፤ 4) የጉዳዩ ባለቤትነት በትክክል ባለመተርጎሙ ምክንያት የአንድ ግለሰብ በምክንያት ላይ የተመሠረተ አስተሳሰብ ለብዙሃኑ ትርጉም አልባ ሲሆን እና መተባበር ”የኔ ችግር አይደለም” ወደሚል አስተሳሰብ ሲያመራ፤ 5) ትብብር ከትንሽ ቡድኖች ይልቅ በትልልቅ ቡድኖች መካከል ተግባራዊ ማድረግ አስቸጋሪ በመሆኑ ነው። ይህ የዝኛ ኢትዮጵያውያን ችግር ብቻ ሳይሆን በዓለምአቀፍ ደረጃ ከሰዎች ባህሪይ ጋር በተዛማጅነት የሚጠቀስ ምክንያት ነው። ስለሆነም የሲቪክ ድርጅቶች ይህን ችግር በመቅረፍ በኩል የሚጫወቱት ሚና አሌ የማይባል ነው። ችግሩንም በትክክል አጥንተው ለውጤት የበቁ ለመተባበር የሚያስችላቸውን ፕሮግራም ተግባራዊ ሲደርጉ በአውሮጳ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ ወዘተ የተመለከትነው ነው። ስለሆነም ለስኬት የበቁ ሕዝቦች ራሳቸውን መስዋዕት ለማድረግ እንዲሁም ለቆሙለት ዓላማ ራሳቸውን ሲሰጡ የምንመለከተው ሐቅ ነው። አለመታደል ሆኖ ግን እስካሁን ይህንን ዓይነት በኢትዮጵያውያን መካከልም ሆነ በሲቪክ ድርጅቶች መካከል ሲፈጸም አልተመለከትንም። ሆኖ እንደ ‹ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ› ዓይነት ድርጅቶች በሕዝቦች መካከል መቀራረብን በመፍጠር ትልቅ ሚና ሊጫወቱ” እንደሚችሉ ዕምነታቸው መሆኑን ገልጽዋል።

በንቲ ማዴራ፤ ከሪዲንግ ዓለምአቀፍ የትብብር ማዕከል
”ኢትዮጵያውያን ተባብረው መሥራት አለባቸው፤ ካልሆነ ግን የውጪ ኃይሎች የአገራችሁን ሃብት ለመዝረፍ ምንም የሚከለክላቸው አይኖርም። ልክ የካሪቢያን አገር ሕዝቦች ለዓለም ሙዝ እያመረቱ እንደሚሰጡ እነርሱ ግን የጥቅሙ ተካፋይ እንዳልሆኑ ሁሉ እናንተም እንዲሁ እየተበዘበዛችሁ መኖራችሁ አይቀሬ ነው። የአገራችሁ መጻዒ ዕድል መልካም እንዲሆን የምታስቡ ከሆነ ተባብራችሁ መሥራት አለባችሁ” በማለት የውጪ አገር ቢሆኑም ለኢትዮጵያውያን ጉባዔተኞች ያላቸውን ልምድ አካፍለዋል።

በጠና ሂጦሳ፤ ከሲዳማ አርነት ንቅናቄ
”በየትኛውም መንገድ ቢሆን ለመተባበር መንገድ ማግኘት አለብን። መለስ ባሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኢትዮጵያውያንን እየተጠቀመ እንደሆነ ሁሉ እኛ ደግሞ ለመተባበር እርስበርስ መደጋገፍና መተጋገዝ አለብን። ሕዝቦች ነጻ የሆነችና የበለጸገች በዘር ያልተከፋፈለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መተባበር አለባቸው” ብለዋል።

ጥያቄና መልስ
እነዚህ ግለሰቦች ንግግር ካደረጉ በኋላ የጥያቄና መልስ ክፍለጊዜ የቀጠለ ሲሆን በወቅቱም የአርበኞች ግንባር አባል የሆኑት አቶ ዮሴፍ ሃይማኖት የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል፡- ”በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚያስፈልገው ያልወገነ ሠራዊት እና ነጻ የፍትሕ አካል ያካተተ ሕዝባዊ መንግሥት ነው። ወገናዊ ያልሆነ ሠራዊት ዛሬ ቢኖረን መለስ ፈጽሞ በሥልጣን አይቆይም ነበር። ሕግን የሚያከብርና ለሕግ የበላይነት የሚገዛ እንዲሁም በሕዝቦች መካከል እኩልነት እንዲኖር የሚያደርግ መንግሥት ለመመሥረት ሁላችንም መታገል አለብን። ይህም የሕዝቦች እኩልነት ‹ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ› መመሪያ አድርጎ የሚከተለው ዓይነት ሁሉንም የሚያቅፍ መሆን አለበት፤ ወደዚህ ንቅናቄ የሳበኝም አንዱ ይህ ነው” በማለት ተጠቃሽነት ያለው ንግግር አድርገዋል።

የአቶ ኦባንግ የማጠቃለያ ንግግር
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝቦች የሚመሠረት፣ ለሕዝብ የሚቆምና የሕዝብ የሆነ መንግሥት ለመመሥረት መንገዱን ለመጥረግ ነው። አንዳንድ ሰዎች ንቅናቄያችን ሥልጣን ለመያዝ ዓላማው ያደረገ የፖለቲካ ድርጅት አድርገው ሊወስዱት ይችላሉ። ሆኖም ይህ የንቅናቄያችን ዓላማ እንዳልሆነ ሊያውቁት ይገባል። በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ዓላማቸውን ለሕዝብ የሚያቀርቡበት የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን ለማምጣት መታገል የንቅናቄያችን ዋንኛው ዓላማ ነው። በዚህ ስብሰባ ላይ ሁሉም ተናጋሪዎች በግልጽ እንዳስቀመጡት በትብብር ለመሥራትና በአገራችን ለውጥ ለማምጣት በመካከላችን ምቹ ሁኔታ እንዳለ ግልጽ ነው። ስለዚህም በመፈቃቀር እና በቅንነት እስከተጓዝን ድረስ ይህን ትብብር ዕውን የማናደርግበት ምንም ምክንያት የለም። ይህም ቅንነት ከራሳችን - ከልባችን - ይጀምራል። ራሳችንን ከዘረኝነት፣ ከጎሰኝነት፣ ከክልላዊ ጠባብነት፣ ወዘተ ነጻ ማድረግ አለብን። በዘረኝነት መንፈስ ከተሸበብን ግን በኦጋዴን በረሃ ባዶ እግሩን ለሚሄደው ሕጻን ወይም መንገድ ዳር በየጎዳናው ለሚተኙት የኦሮሞ አፍላ ወጣቶች ወይም ወላጆቹን በሞት ላጣው የአማራ ወጣት ወይም ከሚኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለው መግቢያ ላጡት የአገራችን ገበሬዎች ”የኔ ወገኖች አይደሉም” በማለት ቅንጣት ታህል ርህራሄ ልናሳያቸው አንችልም። ለዚህም ነው በእርግጥ ለመተባበር ከፈለግን ከእንደዚህ ዓይነት ጠባብ አስተሳሰብ አስቀድመን ነጻ መውጣት ያለብን። ሌላውን ነጻ ለማውጣት ከመታገላችን በፊት በመጀመሪያ ከራሳችን - ከልባችን መጀመር አለብን። ራሳችንን ከእንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ነጻ ሳናወጣ ለሌላው ነጻነት መታገል ፈጽሞ አንችልም፤ መተባበርም ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ይሆናል። ስለዚህ በሌሎች ላይ ጣታችንን ከመቀሰራችን በፊት ረጋ ብለን ለማዳመጥ እንሞክር። ምናልባት በሃሳቡ የማንስማማም ከሆነ ጥቃት ከመሰንዘርና ለማጥፋት ከመሄድ ይልቅ ሥርዓት ባለው መንገድ በአክብሮት ተቃውሞአችንን እንግለጽ። ከሁሉ በፊት የሕዝባችን የየዕለት መከራና ስቃይ ይሰማን። ለራሳችን ክብርና ዝና ከመሮጥ እንቆጠብ፤ ሁሉንም ሰው በቀና ኅሊና እንመልከተው። ለሰው ዘር በሙሉ ትሁት እንሁን። ሰዎችን ከጎሳ፣ ከዘር፣ ከቆዳቸው ቀለም፣ ከጾታቸው፣ ከሚከተሉት የፖለቲካ መርህ፣ ከሃይማኖታቸው ወዘተ በፊት በሰብዓዊነታቸው - የአምላክ ፍጡራን በመሆናቸው - እናክብራቸው። ”ከዘር በፊት ሰብዓዊነትን እናስቀድም”!

ፈጣሪ ሁልጊዜ የምንናፍቀውን ነጻነት ይስጠን! አገራችንንም ይጠብቅ!!
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በእንግሊዝ
User Rating: / 2 
PoorBest 

  ምንጭ ፦http://www.ethiopiazare.com/others/press-release/1536-solidarity-movement-in-england

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር