በየኣስር ኣመቱ በመንግስት ኣካላት የምነሳውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ሃሳብ የሰለቻቸው የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የክልል ጥያቄ ለማንሳት መገደዳቸው ተገለጸ

New

በየኣስር ኣመቱ በመንግስት ኣካላት የምነሳውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ሃሳብ የሰለቻቸው የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የክልል ጥያቄ ለማንሳት መገደዳቸው ተገልጿል::
በሲዳማ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰላማዊ ሰልፍኞ የክልል ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከሶስት ቀናት ባሃላ ተመሳሳይ የክልል ጥያቄ ሰልፍ በሃዋሳ ለማካሄድ ታስቧል::
በዛሬው እለት በሲዳማ ዞን በጭሬ ወረዳ በጭሬ ኩንቡልታ፣ በበንሳ፣ሁላ እና በጠጥቻ የክልል ጥያቄ ባነሱ ሰዎች የተካሄዱ ሰልፎች ያለምንም ግጭት በሰላም መጠናቀቃቸው ተገልጿል::
ዴኢህደን/ ኢህኣዴግ የሃዋሳን ከተማ በኮታ ለማስተዳዳር በሚል ያቀረበውን ኣማራጭ  ሀሳብ በመቃወም የተጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ተቀጣጥሎ የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ያለ ኮታ የማስተዳደር መብት ጥያቄነት ኣልፎ ክልል ይገባኛል ጥያቄ በመሆኑ በመላው ሲዳማ ዞን ውስጥ ህዝባዊ ንቅናቄ ፍጥሯል::
በየኣስር ኣመቱ በመንግስት ኣካላት የምነሳውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ሃሳብ የሰለቻቸው የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የክልል ጥያቄ ለማንሳት መገደዳቸው ተገልጿል::
በመላው ሲዳማ ዞን ውስጥ የተቀጣጠለውን የክልል ጥያቄ ለመቀልበስ የግዥው ፓርቲ ኣባላት ወይም ካድሬዎች ህዝቡን እንዲያወያዩ ወደየ ወረዳዎች በመላክ ላይ ሲሆን፥ የወረዳዎቹ ህዝብ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ መምጣቻቸውን በመጠባባቅ ላይ ነው ተብሏል::
በሲዳማ ዞን ውስጥ በኣንድ ሳምንት ጊዜ  ውስጥ ካጫፍ እስከ ጫፍ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ መንግስትን ግራ ያጋባው ሲሆን እስከ ኣሁን የንቅናቄው መሪዎች ተለይተው ኣለማቻወቃቸው ሁኔታውን ኣስቸጋሪ እንዳደረገው እየተነገረ ነው::
በሌሎች የዞኑ ወረዳዎች እየተደረጉ ያሉ የክልል ጥያቄ ሰልፎች በሚቀጥለ ሶስት ቀናት ውስጥ በሃዋሳ ለማሄድ መታሰቡ በሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ ታውቋል::

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር