የፌደራሉ መንግስትና የሲዳማ ዞን በአዋሳ እጣ ፈንታ ላይ ውጥረት የበዛበት ውይይት እያካሄዱ ነው

New

ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የፌደራል መንግስቱ አዋሳን በስሩ ለማድረግ እቅድ እንዳለው ሲታወቅ፣ የሲዳማ ዞን በበኩሉ ድርጊቱን ይቃመዋል። በቅርቡ በተደረገው ውይይት ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር፣ የሲዳማ ዞን ባለስልጣናትም የፌደራል መንግስቱ ባለስልጣናት የሚመሩትን ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸውንና ጉዳዩን ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እውቅና ውጭ እያካሄዱት ነው።

አዲሱ ውዝግብ የአዋሳን ህዝብ ትኩረት መያዙም ታውቋል። በ1994 ኣም በፌደራል መንግስትና በዞኑ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት  ከ40 እስከ 100 የሚደርሱ የሲዳማ ተወላጆች መገደላቸው ይታወሳል።
የመለስ መንግስት ከፍተኛ የህዝብ እልቂት ያስከተለውን የቆየ ችግር መልሶ በማምጣት ሌላ ችግር ለመፍጠር ለምን እንደተነሳሳ ግልጽ የሆነ ነገር የለም ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች።
http://www.ethsat.com/2012/06/09/%E1%8B%A8%E1%8D%8C%E1%8B%B0%E1%88%AB%E1%88%89-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%88%B2%E1%8B%B3%E1%88%9B-%E1%8B%9E%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%8B%E1%88%B3/

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር