የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ የሚነጋገር የምክክር መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው



አዲስ አበባ፣ግንቦት 13 2004 (ዋኢማ) - የኢትዮጵያን የልማት እቅድ ለማሳካት በተዘጋጀ አዲስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ የሚነጋገር የምክክር መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።
የምክክር መድረኩ ላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ ደሴ ዳልኬ እንደገለጹት አዲሱ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ረቂቅ ፖሊሲ የሀገሪቱን ውስን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀምና ሊፈጠር የሚችለውን አለም አቀፍ ተጽእኖ ለመቋቋም የሚያግዝ ነው።
በውድድር ማእቀፍ ውስጥ በሚካሄደው እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ለመሆን እንደሚያስችልም ተናግረዋል።
ፖሊሲው ሀገሪቱ የተያያዘችውን ፈጣንና ዘላቂ የእድገት ጉዞ በአስተማማኝ ሁኔታ ወደፊት በማራመድ ለልማት እቅዱ ተግባራዊነት የሚረዱ የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም ለማገዝ እንደሚያስችል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር