ለሁለት ቀናት በሀዋሣ ሲካሄድ የቆየው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት 3ኛ ዙር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስት የዞን ካቢኔዎችን ሹመትና ከ32 ነጥብ 8 በላይ ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ፡፡


ለሁለት ቀናት በሀዋሣ ሲካሄድ የቆየው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት 3ኛ ዙር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስት የዞን ካቢኔዎችን ሹመትና ከ32 ነጥብ 8 በላይ ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ፡፡የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሊዮን ማቴዎስ ለም/ቤቱ በእጩነት ያቀረቧቸው ካቢኔዎች የዞኑ ግብይትና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ የከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኃላፊ በመሆን በም/ቤቱ ሙሉ ድምፅ መመረጣቸው ታውቋል፡፡
በተጨማሪም ም/ቤቱ ለቀጣይ ወራት የዞን ማዕከል፣ 19 ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዲሁም ለሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ የሚጠቀሙበትን ከ32 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ በጀት ማፅደቁ ተመልክቷል፡፡
በም/ቤቱ የኢኮኖሚ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሲምቦ ሽብሩ የተጨማሪ በጀት ደንብ ሰነድ ለም/ቤቱ አባላት ሲያቀርቡ ከተመደበው ተጨማሪ በጀት ከ6 ነጥብ 9 በላይ ሚሊዮን በ2ዐዐ3 የበጀት አመት በተለያዩ ምክንያት ስራ ላይ ያልዋለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ቀሪው ከ25 ነጥብ 9 በ ላይ ሚሊዮን በጀት ደግሞ የዞኑ ማዕከል፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ከእቅዳቸው በላይ የሰበሰቡት መሆኑን አቶ ሱምቦ መጠቆማቸውን የዘገበው የዞኑ ባህል ቱሪዝም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር