በሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ 16ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ተግባራዊ ያደረጉ 228 አባወራዎችና እማወራዎች ማስመረቁን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ::


በሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ 16ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ተግባራዊ ያደረጉ 228 አባወራዎችና እማወራዎች ማስመረቁን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ::የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታደሰ አኔቦ አንዳሉት በጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም የግልና የአካባቢ ንጽህናን፣ የቤተሰብ ጤና ክብካቤንና የተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር በቤተሰብ ደረጃ እውን እንዲሆን መጠነ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል::
ርብርቡን ስኬታማ ለማድረግም በወረዳው የዛሬዎቹን ጨምሮ 38 ሺህ 459 አባወራና እማወራዎች መሰልጠናቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል::የዞኑ ጤና መምሪያ መከላከልና ጤና ማጎልበት ኦፊሰር አቶ ኢማላ ላሚቻ በበኩላቸው መንግስት የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ የነደፈውን የጤና ፖሊሲ ስኬታማ ማድረግ ከተመራቂዎች የሚጠበቅ ተግባር ነው ማለታቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል::

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር