የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የተፋሰስ ልማትን ለማጠናከር በውሃ ሀብት ላይ ያተኮሩ ሶስት የምርምር ፕሮጀክቶችን እያካሄደ ነዉ



አዋሳ, መጋቢት 14 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የተፋሰስ ልማት ለማጠናከር በውሃ ሀብት ላይ ያተኮሩ ሶስት የምርምር ፕሮጀክቶችን እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ ።
አለም አቀፍ የውሃ ቀን " ውሀና ምግብ ዋስትና ለሁሉም " በሚል መሪ ቃል ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት በዩኒቨርስቲው ዋናው ግቢ በፓናል ውይይትና በፎቶ ግራፍ አውደ ርእይ ተከብሯል፡፡
የዩኒቨርስቲው ምሁራን በፓናል ውይይቱ ላይ እንዳስረዱት በሀገራችን የተጀመረው የተፋሰስ ልማት ውሃን በአግባቡ ለመጠበቅና ለመጠቀም በተለይም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያለዉ አስተዋጾኦ ከፍተኛ ነዉ ።
በዩኒቨርስቲው የመስኖና ውሃ ሀብት ምህንድስና ትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ ሄኖክ ጥላሁን እንደገለጹት የተጀመሩትን አበረታች የተፋሰስ ልማት ስራዎች ይበልጥ ለማጠናከር የርምር ፕሮጀክቶቹ እየተካሄዱ ያሉት በደቡብ ክልል በሀዋሳ ሀይቅ ፣ በብላቴ ወንዝና ሌሎች የተፋሰስ አካባቢዎች
ላይ ነዉ ።
ከምርምሮቹም መካከል በሀዋሳ ሀይቅ ላይ ከከተማው የተለያዩ አቅጣጫዎች ከሚለቀቁ ዝቃጭ ቆሻሻዎች ለመታደግና የሃይቁን ደህንነቱ ለመጠበቅ ብሎም ለልማት እንዲውል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰሩና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
በደቡብ ክልል ከሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚያካሄዳቸው የምርምር ስራዎች ወደሌሎችም የሀገራችን አካባቢዎች በማስፋፋት የድርሻውን እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርስቲው የባዮ ሲስተምና ኢንቫይሮሜንታል ምህንድስና ዲፓርተመንት መምህር አቶ አሰግድ ቸርነት በበኩላቸው በተለይ ተማሪዎችንና ወጣቶች የውሃን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በውል ተገንዝበው እንዳይባክንና እንዳይበከል ዕውቀታቸውንም ለሌላው ህብረተሰብ በማስተላለፍ ግንባር ቀደም ሀላፊነተቻወን እንዲወጡ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱበት ክለብ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም ዩኒቨርስቲውና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያቀፈ አስተባበሪ ኮሚቴ በማቋቋም ጭምር በውሃ ሀብት ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆናቸው አስረድተዋል፡፡
የዩኒቨርስቲው የመስኖና ውሃ ሀብት ምህንድስና ክበብ ሰብሳቢ ተማሪ መስፍን ማቲዎስና የክበቡ አባል ተማሪ ሀብታሙ ዘነበ በየበኩላቸው ከ470 በላይ ተማሪዎችን በአባልነት ያቀፈዉ ክብብ በውሃ ሀብት ዙሪያ የፈጠራ ስራዎችን ከማበረታታ በሻገር ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች በማከናወን ተመርቀው ሲወጡም የዘርፉን ልማት ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የደቡብ ክልል ውሃ ሀብት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ውብሸት ጸጋዬ በበበኩላቸዉ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አመት መጨረሻ የክልሉን የውሃ ልማትና ለህብረተሰቡ የሚኖረው ተደራሽነት አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማነጻጸር ገለጻ አድርገዋል፡፡
በበዓሉ ላይ ዩኒቨርስቲው ከክልሉ ውሃ ሀብት ቢሮና የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር በመተባበር የውሃና የመስኖ ተቋማት ግንባታዎች እንቅስቃሴ አስመልከቶ ያዘጋጀው የፎቶ ግራፍ አውደ ርእይ ቀርቦ በእንግዶች ተጐብኝቷል ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር