በሀዋሣ ከተማ በሳምንቱ ከነበረው የነጭ ጤፍ የገበያ ውሎ በሀላባ ከተማ የ2ዐዐ ብር ቅናሽ መስተዋሉን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ በላከልን መረጃ አመለከተ ::


በሀዋሣ ከተማ በሳምንቱ ከነበረው የነጭ ጤፍ የገበያ ውሎ በሀላባ ከተማ የ2ዐዐ ብር ቅናሽ መስተዋሉን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ በላከልን መረጃ አመለከተ፡፡በሀላባ ከተማ 1 ኪሎ በርበሬ 42.5ዐ ሳንቲም ዋጋ ሲሸጥ በሀዋሣ ከተማ የ14 ብር ጭማሪ አሳይቷል፡፡በዛሬው የገበያ ውሎ ዳሰሳችን በሳምንቱ የሀዋሣ፣ ሆሣዕናና ሀላባ ከተሞች ገበያ ውሎን እናስቃኛችሁአለን፡፡
በሳምንቱ ከነበረው የገበያ ውሎ ነጭ ጤፍ በሐዋሣ ከተማ ኩነታሉን 1 ሺህ 37ዐ ብር በችርቻሮ የተሸጠ ሲሆን የ7ዐ ብር ቅናሽ በማሳየት በሆሣዕና ከተማ 1ሺህ 3ዐዐ ብር በሀላባ ከተማ 2ዐዐ ብር ቅናሽ በማሳየት ኩንታሉ በችርቻሮ 1ሺህ 17ዐ ብር ሲሸጥ ሰንብቷል፡፡ከብርዕ ሰብል ወደ አገዳ ሰብል ስናመራ በቆሎ በሀላባ ከተማ ኩንታሉን በችርቻሮ 43ዐ ብር ተሽጧል፡፡ በሆሣዕና የ1ዐዐ ብር ጭማሪ በማሳየት 53ዐ ብር እንደዚሁም በሐዋሣ ከተማ 54ዐ ኩንታል በችርቻሮ ንግድ ተሽጧል፡፡
ወደ ጥራጥሬ እህል የገበያ ውሎ ስንሸጋገር ደግሞ አንድ ኩንታል አተር በሐዋሣ ከተማ በችርቻሮ 1ሺህ 62ዐ ብር ሲያወጣ በሆሣዕና ከተማ 12ዐ ብር ቅናሽ በማየት የ1ሺህ 5ዐዐ ዋጋ አውጥቷል፡፡ በሀላባ ገበያ በመሸጥ ከሆሣዕና ገበያ 14ዐ ጭማሪ ተስተውሏል፡፡የአትክልትና የስራስር ተክሎች ሳምንታዊ የገበያ ውሎን ስንመለከት አንድ ኪሎ ቲማቲም በሆሣዕና ከተማ 12 ብር ሲሸጥ የሰነበተ ሲሆን በሀላባ ከተማ የ3.5ዐ ሳንቲም በሀዋሣ ከተማ ደግሞ የ4 ብር ቅናሽ በማሳየት ተሽጧል፡፡
ቀይ ሽንኩር 1 ኪሎ ግራም በሐዋሳ ከተማ በችርቻሮ ተሽጧል፡፡ በሆሣዕናና በሀላባ ከተሞች ደግሞ የ9 ብር ዋጋ አውጥቷል፡፡ ነጭ ሽንኩርት በሆሣዕና ከተማ 1 ኪሎ 5ዐ ብር በሀላባ 46 ብር እንደዚሁም የሀዋሣ ከተማ የ14 ብር ቅናሽ በማሳት በ36 ብር ሲሸጥ ተስተውሏል፡፡ከአትክልትና ከስራስር ተክሎች የገበያ ውሎችን ወደ ቅመማ ቅመም የገበያ ዳሰሳችን ሰነሸጋገር በበርበሬ ምርቷ ታዋቂ በሆነችው ሀላባ ከተማ 1 ኪሎ በርበሬ 42.5ዐ ሳንትም ሲቸበቸብ በሀዋሣ ከተማ የ14 ብር ጭማሪ በማየት 56 ብር በሆሣዕና ከተማ ደግሞ በ55 ብር ተነግዷል፡፡፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር