ሃዋሳ ከነማ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ የ2ኛ ዙር የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታውን በአየር ሀይል ሜዳ ይጀምራል



በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ መጋቢት 12/2004 ዓ.ም 9 ሰዓት ቢሾፍቱ ላይ አየር ሀይል እና የሀዋሳ ከነማ ይጫወታሉ፡፡

ባለፈው ቅዳሜ በፕሪምየር ሊግ ቀሪ ተስተካከይ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት የተሸነፈው አየር ሀይል የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታውን በሜዳው ሀዋሳ ከነማን በማስተናገድ ይጀምራል፡፡

አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናን በማሰናበት አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታን የቀጠረው አየር ሀይል በፕሪምየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ9 ነጥብ እና 10 የግብ እዳ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ በ2ኛው ዙር በመጀመሪያ ሳምንት ዛሬ መጋቢት 12/2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታድየም የሚያካሂዱት ጨዋታ ለሰኔ 12/2004 ዓ.ም እንደተላለፈ የኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ፕሪምየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ30 ነጥብ ይመራል መብራት ሀይል በ28 ነጥብ ይከተላል፡፡

ደደቢት በ26 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡የኮከብ ጎል አግቢነቱን ጌታነህ ከበደ ከደደቢት በ13 ጎል ይመራል፡፡መድሀኔ ታደሰ ከኢትዮጵያ ቡና በ11 ጎል ይከተላል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር