በሀዋሳ ከተማ የተገነባው አዳሬ ሆስቲፓል ተመረቀ

ኢትዮጵያ የምዕተ ዓመቱን የጤና ግቦች ለማሳካት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገች ነው - ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም

 


አዲስአበባ፣የካቲት 13፣ 2003 (ፋና ብሮድካስቲንግኮርፖሬት
ኢትዮጵያየምዕተ ዓመቱን የጤና ግቦች ለማሳካት አበረታች እንቅሰቃሴዎችን
እያደረገች ነው አሉ  የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ።
ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በሐዋሳ ከተማ 
የተገነባውን የአዳሬ ሆስፒታል መርቀውሲከፍቱ እንዳሉት
ሀገሪቱ በጤናው ዘርፍ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት የህጸናትና
የእናቶች ሞት ጨምሮ የወባ፣የኤች አይ ቪ ኤድስናየቲቪ 
በሽታዎች ቀንሰዋል፡፡
በተለይ የእናቶችን ሞት እ ኤ አ አቆጣጠር በ1990
ከነበረበት 1 ሺ 40 በአሁኑ ወቅትወደ 470 ዝቅ ማለቱን 
የዓለም ጤና ድርጅት በቅርቡ ይፋ ያደረገው ሪፖርት አመልክቷል፡፡
ወባ፣ኤች አይ ቪ ኤድስና የቲቢ በሽታዎች ስርጭትም 
ከ50 በመቶ በላይ መቀነሱን አመልክተዋል ዶክተር ቴዎድሮስ።
ለዚህም ስኬት በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
የጤና ባለሙያዎች ማህበራትና አባላትአስተዋጽኦ በአርአያነት
የሚጠቀስ ነው ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር