በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ጩኮ ወረዳ የገጠር ህብረተሰብ የአማራጭ ኢነርጂ አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን ላይ ነው ተባለ።


በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ጩኮ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት የኤሌክትሪ ኃይል ባልተዳረሰበት አካባቢ የሚኖረውን የገጠር ህብረተሰብ በአማራጭ የኢነርጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ግርማ ዓለሙ እንዳስታወቁት ከክልሉ ባዩ ጋዝ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር  የገጠሩን ህበረተሰብ የባዩ ጋዝ ተጠቃሚ ማድረግ ጀምረዋል፡፡
ከዚህ ሌላ የጽህፈት ቤታቸው ባልደረባ የሆነ አንድ ወጣት ባለሙያ የግል ፈጠራውን ተጠቅሞ በፀሐይ ሃይል የሚሰራና ለምግብ ማብሰያነት የሚያገለግል መሳሪያ ሰርቶ ለሙከራ አገልግሎት ማብቃቱን ገልጸዋል፡፡
ከመቀሌ ዩንቨርስቲ ከሜካኒካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ትምህርቱን አጠናቆ በጽህፈት ቤቱ የአንድ የሥራ ሂደት አስተባባሪ በመሆን እያገለገለ ያለው ወጣት ሰርካለም ሰለሞን የዲግሪ ማሟያ ጽሑፉን በፀሐይ ሃይል በሚሰራ መሳሪያ ዙያ እንደፃፈና ከዚህ በመነሳት መሳሪያውን የራሱን ፈጠራ ተጠቅሞ እንደሰራ አስረድቷል፡፡
የባዩ ጋዝ ቴክኖሎጂ ምግብ ለማብሰልና የብርሃን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር በጤና በኩልም ወጪን ለመቀነስና ለአካባቢ ጥበቃ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
 
በወረዳው ሩፎ ጫንጮ ቀበሌ የባዩ ጋዝ ተጠቃሚዎች አንዱ የሆኑት አርሶ አደር ተስፋዬ ሔሊሶ እንዳሉት ተጠቃሚ መሆን ከጀመሩ ወዲህ ኩራዝና ፋኖስ መጠቀም በመተዋቸው በየጊዜው ዋጋው ከሚያሻቅበው ከጋዝ ግዥ ድነዋል፡፡
በተጨማሪም ባለቤታቸው ምግብ ሲያበስሉ ዓይናቸውን ከሚያቃጥላቸው ጢስ መትረፋቸውንና ልጆቻቸው ደግሞ ለማገዶ እንጨት ለቀማ የሚያጠፉትን ጊዜ ለትምህርታቸው ማዋል መጀመራቸውንና ማታም እስከቻሉበት ድረስ እንደሚያጠኑ መናገራቸውን የሲዳማ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር