የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ህገ-ወጥ የመሬት ሽያጭና ግንባታ ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ በህገ-ወጥ የመሬት ወረራ፣ በአዲሱ የንግድ አሰራር አዋጅና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ላይ አስተዳደሩ እየመከረ ነው፡፡




በሃገሪቱ ህገ-መንግስት ላይ እንደተጠቀሰው መሬት የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ሃብት በመሆኑ መሸጥ መለወጥ አይቻልም፡፡
የህገ-መንግስቱን መርህ ተከትሎ ሌሎች ደንቦችና መመሪያዎች የወጡ ቢሆንም በሃዋሳ ከተማ በመሬት ደላሎች በሚናፈስ የተሳሳተ መረጃ ህገ-ወጥ የመሬት ሽያጭ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባብሷል፡፡
የከተማው ከንቲባ አቶ ሽብቁ መገኔ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ፣ አመራሮች በተገኙበት መድረክ ላይ እንደገለጹት በከተማው ካሉት 8 ክፍለ ከተሞች አንደኛው ከ100ሺህ በላይ ሰዎች የሚኖሩበት አካባቢ የህብረተሰቡ መተዳደሪያ እርሻ ነው፡፡
መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ መሆኑን እያወቁ ደላሎች አርሶ አደሩን በገንዘብ እያባበሉ መሬቱን ሽጦ ገንዘቡ ካለቀ በኋላ ልጆቹን ማስተዳደር ባለመቻሉ ወደ ጐዳና ወጥተዋል፡፡
ቢሆንም ዛሬም ህገ-ወጥ ሽያጭና ግንባታው ያልቆመ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ለእርምጃው እንዲረዳው የመጀመሪያውን የምክክር ጀምሯል፡፡
በሂደቱም መሬት የሸጠውን አርሶ አደር ግንዛቤ ካስጨበጠ በኋላ በመሬት ሽያጩ የተሳተፉትን አመራሮችና ፖሊሶችን የቀበሌ አካላትን ገምግሞ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ይደረጋል፡፡
ቀጥሎም በህገ-ወጥ ግንባታ የተሳተፉ ግለሰቦች ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ትዕዛዝ ይተላለፋል፡፡ የተቀመጠውን መርህ የማይቀበሉ ካሉ አስተዳደር ማፍረሱን ይቀጥላል፡፡
መሬቱ የአርሶ አደር መሆኑ እየታወቀ ወደ ኋላ የ10 ዓመትና ከዚያ በላይ ካርኒ በመስጠት ህጋዊ ለማድረግ በህገ-ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
ወደ ኋላ ሄዶ ካርኒ በመቁረጥ የህገ-መንግስቱ አዋጅ ስለማይሻር የገዙ ሰዎች በኪሳራ ቦታቸውን ለአርሶ አደሩ ለቀው ይወጣሉ፡፡
ነባሩ አርሶ አደር ቦታው ተመልሶለት በተለካ መሬት ላይ የተረጋጋ እርሻውን አርሶ ልጆቹን እንዲያሳድግ ይደረጋል፡፡
በሂደት ግን አስተዳደሩ ቦታውን ከፈለገ በሊዝ በህጋዊ መንገድ ለአርሶ አደሩ የሚገባውን ከልሎ ሊጠቀመው እንደሚችል ከንቲባው ገልጸዋል፡፡
ህገ-ወጥ የንግድ ሥራዓቶችንም ፈር ለማስያዝ ነጋዴውና ሸማቹ በህጋዊ ገበያ መስመር እንዲገበያዩ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ እንዲሁ በንግድ አሰራርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተጀምሯል፡፡
በከተማው የሚከናወኑ ማናቸውንም ህገ-ወጥ ተግባራትን ለማቆምና ለአፈጻጸም አመራሮች እራሳቸውን ዝግጁ ለማድረግም መምከራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር