አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ ለተያዘው የልማት እድገት መፋጠን የጐላ ሚና እንደሚኖረው የሃዋሳ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ እንደገለጹት መምሪያው በመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ አገልግሎት በከተማዋ ለሚገኙ 27 ሴክተር መስሪያ ቤቶች በአመራር ሚና፣ በስነ-ምግባርና በፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የመንግስት ሰራተኛው ግንዛቤ እንዲያድግ በማድረግ ወደ ሙሉ ትግበራ መግባት ተችሏል፡፡




ቀድሞ የነበረውን የተንዛዛ አሰራር በተቀላጠፈና ተደራሽነት ባለው መልኩ በማሳለጥ BPRን በአግባቡ በመተግበር ህበረተሰቡን በተሻለ መልኩ ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም ተናግረዋል፡፡
ከህብረተሰቡ አስተያየት ለማወቅ እንደተቻለው ከክልል እስከ ክፍለ ከተማ በወረደው የBPR መዋቅር ሳምንታት ይወሰዱ የነበሩ ሥራዎች በሰዓታት መፈጸም ከመቻላቸውም በላይ ያለምንም መጉላላት በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ተጠቃሚ ሆነዋል ሲል የሃዋሳ ከተማ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር