የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት ባወጣው መርሃ-ግብር መሰረት በሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ወረዳ በ14ቱም ቀበሌያት ምርጫው እንደሚደረግ የዞኑ እና የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡




የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ እንዳስታወቁት ባለፈው ዓመት ግንቦት 15/2002 በተካሄደው ህገራዊ ምርጫ ወቅት በወረዳው በተጓደሉ የቀበሌ፣ የወረዳና የዞን ምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ የማሟያው ምርጫ ማካሄድ አስፈልጓል፡፡
በመሆኑም በወረዳው የማሟያ ምርጫ ለማካሄድ 50 የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡
የምርጫ አስፈጻሚዎችና ታዛቢዎች በህዝብ መመረጣቸውንና የምርጫ ቁሳቁሶችንም ወደ የምርጫ ጣቢያዎቹ ለማሰራጨት ዝግጅቱ  መጠናቀቁንም እንዲሁ፡፡
ከጥር 18 ጀምሮም ስለማሟያው ምርጫ፣ ስለመራጮች ምዝገባና ድምጽ አሰጣጥ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ትምህርት በመሰጠት ላይ መሆኑንም አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡
ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት ባወጣው መርሃ-ግብር መሰረትም ከጥር 20 እስከ ጥር 29 የመራጮች እንዲሁም የተወዳዳሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች ምዝገባ እንደሚካሄድም አስታውቀዋል፡፡
በወረዳው የኢህአዴግ ፓለቲካ  ፓርቲ እጩዎችን ጨምሮ ከ3 የሚያንሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች በማሟያው ምርጫው ይወዳደራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለጹት የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ የግል ተወዳዳሪዎች ደግሞ ከጥር 14 እስከ 20 ከየቀበሌው አስተዳደር የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባስቡ የወጣው ፕሮግራም እንደሚገልጽ ማስረዳታቸውን የሲዳማ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር