በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመታዊ ገቢውን በእጥፍ በማሳደግ 1መቶ 94 ነጥብ 2 ሚሊዩን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታገሰ ጫፎ ቢል ቦርዱን መርቀው ከከፈቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር ግብር በወቅቱ መከፈል በሀገር ደረጃ ለሚከናወኑ መሰረተ ልማቶች ስኬት ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡
ግብር በመክፈሉ የተሰሩ የልማት ስራዎች ለከተማው ህብረተሰብ ማሳየት የተጀመረው አሰራር በተለያዩ መንገዶች እስከ ገጠር ቀበሌ የሚቀጥል መሆኑን አቶ ታገሰ ገልፀዋል፡፡
አርሶ አደሩ ለሚጠቀምበት የእርሻ ይዞታ ያለጎትጓች ግብር የመክፈል ባህል ያለው መሆኑና ይሄው በጎ ልምድ በሌሎች ግብርና ታክስ ከፋዮች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ መኑር ሙዘይን በበኩላቸው በቢልቦርዱ ላይ እንዲታዩ የተደረጉት መሰረተ ልማቶች ግብር በመከፈሉ የተገኙ ውጤቶች መሆናቸውን ለማመላከትና ለወደፊትም በፈቃደኝነት ግብር የመክፈሉ ባህል እንዲጎለብት ለማስቻል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ባለፈው በጀት አመት 80 ነጥብ 2 ሚሊዩን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 120.22 ሚሊዩን መሰብሰብ ችሏል፡፡
የ2003 እቅዱን ከ2002 በእጥፍ በማሳደግ 194.2 ሚሊዮን ብር ለማድረስ ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በተጠናቀቀው ሩብ አመት 34 ነጥብ 47 ሚሊዩን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 42 ነጥብ 13 ሚሊዩን ብር መሰብሰብ እንደተቻለም ተብራርቷል፡፡
በሀዋሳ ከተማ ተመርቆ የተከፈተው ቢልቦርድ በሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች ከተሰሩት አንዱ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር