የከተሞች ቀን በዓልን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ተጠናቀቀ


አዲስ አበባ፣ ህዳር 15 2003 (ሬዲዮ ፋና) በነገው ዕለት በሃዋሳ ከተማ ለሚከበረው2ኛው ሃገር አቀፍ የከተሞች
ቀን በዓል ለማክበር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የከተማዋ ከንቲባ ተናገሩ።

ባለፈው ዓመት አንደኛው የከተሞች ቀን በአዲስ አበባ ሲከበር የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር
ባዘጋጀው የ40 ከተሞች ውድድር ላይ የሃዋሳ ከተማ በገፅታ ግንባታና በልማታዊ ስራዎች አንደኛ በመውጣቷ
 2ኛውን የከተሞች ቀንእንድታዘጋጅ መርጧታል።

ከተማዋ ይህን በዓል ከማዘጋጀት ጎን ለጎንም የተቆረቆረችበትን 50ኛ የወርቅ ኢዮቤልዮበዓል በጥምረት ለማክበር
ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ስታከናውን ቆይታለች።
ይህን ድርብ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበርም የተለያዩ ዝግጅቶች መደረጋቸውን የከተማዋከንቲባ 
አቶ ሽብቁ ማደኔ ተናግረዋል።
በዓሉ በከተማዋ መከበሩ የከተማዋን ገጽታ ለማስተዋወቅና በከተማዋ ያሉ የኢንቨስትመንትአማራጮችን ለመላው 
ኢትዮጵያውያን ለማስተዋወቅ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል።
ባለፉት ዓመታት የተገኙትን ስኬታማ የገፅታ ግንባታ ስራዎችን በማስቀጠልም ከተማዋን የኢንቨስትመንትና 
የቱሪስት መስህብ ማዕከል ለማድረግ በዓሉ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
አያይዘውም ከተሞች የተሻሉ የልምድ ልውውጦች የሚያደርጉበትና ለ5 አመቱ የዕድገትናየትራንስፎርሜሽን
ዕቅድ መሳካት የሚያደርጉትን ትግል ለመማማር እንደሚያግዝም አስረድተዋል።

ወደ ከተማዋ በርካታ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ ከውጭና  በሃገር ውስጥ የሚገኙ የከተማዋ 
ተወላጆች እንዲሁም ከተለያዩ የሃገራችንከተሞች በዓሉን ለማድመቅ የሚመጡ በርካታ ዕንግዶች በመግባት
ላይ ይገኛሉ።

እነዚህን ዕንግዶች በአክብሮት በመቀበልና በማስተናገድ የከተማዋ ነዋሪዎች የተለመደውንየዕንግዳ ተቀባይነት 
ባህል እንዲያሳዩም ከንቲባው ጠይቀዋል።
በበዓሉ ላይ 82 ከተሞች ቀጣዩን በዓል ለማዘጋጀት የሚያስችል ከፍተኛ ውድድር በተለያዩ ዘርፎች 
እንደሚያደርጉም ታውቋል።


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር