የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በሃዋሳ ከታማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው

ሃዋሳ, ህዳር 11 ቀን 2003 (ሃዋሳ) - የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በሃዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ገለጠ።
የምክር ቤቱ አፈጉባዔ አቶ ለማ ገዙሜ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በዓሉ በመጪው ህዳር 28 እና 29 ቀን 2003 በሃዋሳ ከተማ የክልሉን 13 ዞኖችና ስምንት ልዩ ወረዳዎች ባሳተፈ ሁኔታ በሲምፖዚየምና በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።
በክልሉ የሚገኙ 56 ብሔረሰቦችነ ሕዝቦች ያላቸውን የባህል እሴቶችና ልምድ በበዓሉ እንደሚለዋወጡ ገልጠው በፌደራልዝም ላይ ውይይት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
ከታህሳስ 4 ቀን ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የፌደራሊዝም ኮንፍራንስና የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ላይ 56ቱ የክልሉ ብሔረሰቦች ያሏቸውን እሴቶች እንደሚያቀርቡ አስታውቀው የክልሉን ባህልና ወግ የሚያንጸባርቅ ኤግዚቢሽን እንደሚቀርብም ገልጠዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር