Posts

ኢትዮጵያ በኢቦላ ለተጠቁ ሀገራት 200 በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎችን ልትልክ ነው፤ በቫይረሱ ለተጠቁ ደግሞ ግማሽ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች ኣሉ

Image
ኢትዮጵያ በኢቦላ ለተጠቁ ሀገራት 200 በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎችን ልትልክ ነው፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ኢትዮጵያ ባለሙያዎቹን የምትልከው የአፍሪካ ህብረት ሀገራት ኢቦላን ለመግታት በጎ ፍቃደኞችን እንዲልኩ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ ነው ብለዋል፡፡ የባለሙያዎቹ ቡድን ሐኪሞችን፣ ነርሶችን፣ የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ባለሙያዎችን፣ የአካባቢ ጤና ባለሙያዎችንና የህብረተሰብ ጤና ስፔሻሊስቶችን ያካተተ ነው፡፡ ሚኒስትሩ እንዳሉት ከዚህ ቀደምም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ባደረገው ጥሪ መሠረት ከህብረቱ ቡድን ጋር የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡  ይህ ድጋፍ አፍሪካዊ አንድነትና ትብብርን ከማጠናከሩም ባሻገር የዓለም አቀፍ ማህበረሰብን ካንዣበበበት አደጋ መታደግ መሆኑንም  ነው ዶክተር ከሰተብርሃን የተናገሩት፡፡ ኢትዮጵያ ቀደም ብሎ በአፍሪካ ህብረት ስር እንደዚህ ዓይነት በሽታዎችና ወረርሽኞች እንዳይከሰቱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ማዕከል እንዲቋቋም ሃሳብ ከማቅረብ ጀምሮ በትጋት እየሰራች ትገኛለችም ነው ያሉት፡፡  ይህ ዓይነት አዲስ የጤና ቡድን ድጋፍ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አንድነትና ጥንካሬ ያላትን የማያቋርጥ ቁርጥ አቋም የሚያሳይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ወደፊትም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ዶክተር ከሰተብርሃን አክለውም ኢትዮጵያ በቫይረሱ ለተጠቁ ሀገራት ግማሽ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቷን ጠቁመዋል፡፡ በምዕራብ አፍሪካ እስካሁን ከ4 ሺህ 500 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ 9 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡ ምንጭ፦  www.fanabc.com

Ethiopia should wake up and smell the coffee

Image
Ethiopia, Africa’s biggest coffee producer, will benefit from unusually dry weather in Brazil that has  lowered the  output and helped lift the price of Arabica beans. Arabica prices surged to a three-year high – to over 200 US cents per pound – in October, which is expected to lift Ethiopia’s coffee export earnings by 25 per cent to $900m this year. But Ethiopia is missing an opportunity to make a lot more money from arabica, which originated in the country’s highlands, and is considered the superior of two main varieties of coffee bean (the other, robusta, is more bitter and tends to be used to make instant coffee). A note from Ecobank said that: Ethiopia could position itself as a low-cost Arabica naturals producer, but it faces constraints, notably an inefficient supply chain and the low productivity of smallholder coffee farmers. Ethiopia dominates east Africa’s coffee production (see chart). After the sector was liberalised in the 1990s its coffee output increased, su

Sidama Homacho Waeno Blue Bottle Coffee is amongst the 2015 Good Food Awards for coffee finalists

Image
Sidama Homacho Waeno Blue Bottle Coffee was c hosen from 1,462 entrants of the 206 companies which are creating vibrant, delicious, sustainable local food economies.  The winners of the Good Food Award for coffee will be distinguished by exemplary flavor – sweet, clean, well developed body, balanced acidity and phenomenal aromatics. To qualify for entry, roasters and coffee farmers must emphasize fairness and transparency from seed to cup.  Worancha information network  corespondent  from San Francisco has learnt that this year’s entry criteria seeks to accommodate the enormous cultural diversity of coffee production while taking a broader approach to environmental sustainability.  It was also said that, winning coffees that are also using certified organic beans will be eligible to receive the Good Food Awards Gold Seal. The winner will be known on Ja nuary 8, 2015. Source: www.goodfoodawards.org

የባለፈው ዓመት የሊጉ ችግሮች አይደገሙም- ፌደሬሽኑ

Image
የባለፈው ዓመት የሊጉ ችግሮች አይደገሙም- ፌደሬሽኑ ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን  ውበት ያሳጡት ችግሮች እንዳይደገሙ  ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡ የ2007 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ጥቅምት 15 መጀመራቸውን ተከትሎ ነው ከወድሁ ፌደሬሽኑ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን እየተናገረ ያለው፡፡ ፌደሬሽኑ በሊጉ ጨዋታዎች ወቅት የሚከሰቱ የዳኝነት ችግሮች፣ የጨዋታዎች ረዘም ላለ ጊዜ መቋረጥና የክልል ስታዲዮሞች ደረጃ ችግርን ለመፍታት ሰፊ ስራ መስራቱን ገልጿል፡፡ የፌደሬሽኑ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ በተለይ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት  የዳኞችንና የኮሚሽነሮችን አቅም ለማሻሻል ሰፊ የሙያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ዳኞችና ኮሚሽነሮች የባለፈውን ዓመት አፈጻጽም በመገምገምም ክፍትቶቻቸውን የሚሞሉበትን ዝግጅት ማድረጋቸውንም ገልፀዋል፡፡ ፌደሬሽኑ የዳኞችን  የስራ ተነሳሽነት ለማሳደግም  ክፍያቸውን አሻሽሏል፡፡ የ2007 የሊጉ የጨዋታ መርሃ ግብር ከዚህ በፊት እንደሚከሰተው በብሔራዊ ቡድን ዝግጅትና በሌሎች ምክንያቶች በመቋረጥ ውበቱን እንዳያጣ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ጨዋታዎችን መነሻ በማድረግ መዘጋጀቱን አቶ ወንድምኩን ገልጸዋል፡፡ በክልሎች የሚገኙ ክለቦች ደረጃውን የጠበቀ ስታዲዮም  እንዲያዘጋጁ  በማሳሰቡ፣ሁሉም የክልል ክለቦች ስታዲዮሞቻቸውን ለማሻሻል እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ እንዳቶ ምንድምኩን ገለፃ ፌደሬሽኑ የ2006 ዓ/ም አፈፃፅምን በመገምገም የነበሩበትን ክፍተቶች ለማሻሻል በመስራቱ የባለፈው ዓመት ችግሮች በዚህ ዓመት እንዳይደገሙ በጥንቃቄ ለመምራት ተዘጋጅቷል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2007 የጨዋታ መርሃ ግብር በመጪው ቅዳ

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጡት ካንስር ህክምና መሰጠት ሊጀመር መሆኑ ተሰማ

Image
የጡት ካንሰር ህክምና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት ሊጀመር ነው የጡት ካንሰር ህክምናን በ5 ዩኒቨርሲቲዎች ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በጡት ካንሰር ዙሪያ የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገለጹ። ይህን ህክምና ለመጀመር የሚያስችል የመሳሪያና የባለሞያ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። ህክምናው የሚሰጠው በጅማ፣ ሃዋሳ፣ መቀሌ፣ ጎንደር እና ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ነው። ዓለም አቀፉ የጡት ካንሰር ቀን ጥቅምት 16 በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበርም አዲስ አበባን ጭምሮ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ እና ትግራይ ክልሎች የእግር ጉዞ በማካሄድ ነው። የዚህ በአል አላማ ህብረተሰቡ የጡት ካንሰርን አስቀድሞ የመከላከል፣ የምርመራና የህክምና አማራጮችን ግንዛቤ ማሳደግ ነው። የጡት ካንሰር ህመምን ሙሉ ለሙሉ አስቀድሞ መከላከል ባይቻልም ህመሙ እንደተከሰት ተገቢው ህክምና ከተሰጠ የመዳን እድሉ  ሰፊ ነው። የዕድሜ መግፋት፣ ከመጠን ያለፍ ክብደት፣ አልኮል መጠጣት፣ ጡት አለመጥባትና መሰል ምክንያቶች ለጡት ካንሰር እንደሚያጋልጥ የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ። ምንጭ፦ EBC

UGANDA, KENYA FALL AS TANZANIA, ETHIOPIA RISE IN LATEST FIFA RANKINGS

Image
Uganda has fallen five places according to the latest Coca Cola FIFA rankings released on Thursday October 24. Uganda;  79th last month  is now ranked 84th in the world and 21st in Africa with 389 points. The fall is attributed to the back-to-back losses to Togo in the  Africa Nations Cup qualifiers  and Uganda Cubs' (U-17)  failure to go past Zambia in the Africa Youth Championship qualifiers . Neighbours Kenya have also fallen five places from 111st to 116; a fall attributed to losses against Morocco and Egypt in international friendlies. However, there was rise for Tanzania and Ethiopia who are now ranked 110 and 111 in the world respectively. Ethiopia were the biggest movers rising 21 places from 132 last month. Uganda’s opponents in  group E of the AFCON qualifiers  Ghana dropped two places to 35th (5), Togo rose 72 places to 52nd (10) whilst Guinea dropped 7 places to 55 (11). World champions Germany maintain top spot followed by Argentina, Colombia, Bel

የቡና ግብይት ስርዓቱ ግልጽ አስተማማኝና ቀልጣፋ ነው ኣሉ

Image
በሃዋሳ እና በሌሎች ከተሞች የተገነቡ የቡና ቅምሻና ጨረታ ማዕከላት የቡና ግብይት ስርዓቱ ላይ ይታይ የነበረውን ችግር በማስቀረት ግብይቱ ግልጽ አስተማማኝና ቀልጣፋ እንዲሆን ኣስችለዋል መባሉ ተሰምቷል፤ ከክልሉ በተያዘው ዓመት ከ134 ሺህ ቶን የሚበልጥ የታጠበና ደረቅ ቡና ለገበያ ይቀርባል እየተባለ ነው። ወሬው የኢዜኣ ነው፦ ከደቡብ ክልል ለገበያ የሚቀርበውን የቡና መጠን በጥራት በመጨመር የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ አስታወቀ፡፡ በቢሮው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከክልሉ በተያዘው ዓመት ከ134 ሺህ ቶን የሚበልጥ የታጠበና ደረቅ ቡና ለገበያ ይቀርባል። ክልሉ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ማምረት የሚችል ቢሆንም ህገወጥ የቡና ግብይትና ዝውውር በገበያው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ለውጪ ምንዛሪ መጠን ማነስ ምክንያት ሆኖ መቆየቱን ጠቁመዋል። ህገወጥ የቡና ዝውውርና ግብይትን ለማስቀረትና በግብይት ስርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ለውጪ ገበያ የሚቀርበውን ቡና ጥራት ለማስጠበቅ የቡና ግብይት ደንብና መመሪያ ተዘጋጅቶ ግባራዊ መሆኑን ገልጸዋል። የቡና ግብይት ስርዓቱ እሴት በማይጨምሩ ደላሎችና ህገወጥ የቡና አዘዋዋሪዎች እጅ የወደቀ በመሆኑ አምራቹ ለምርቱ ተመጣጣኝ ዋጋ እንደማያገኝ ገልጸው በቡናው ላይ የጥራት መጓደል ችግር የሚፈጠር በመሆኑ የሚፈለገውን ያህል ገቢ ማግኘት እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡ የቡና ግብይት ስርዓቱ ግልጽና የአምራቹን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲያስችል የገበያ መሰረተ ልማት የማስፋፋት ስራ መከናወኑን ገልጸው ባለፉት አራት ዓመታት አንድ ሺህ 618 የመጀመሪያ

የጋራ ምክር ቤቱ በኣገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትና ችግሮችን ለመፍታት እድል ፈጥሯል-ፓርቲዎች

Image
የጋራ ምክር ቤቱ በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከገዥው ፓርቲ ጋር በሰከነ መንፈስ ለመወያየትና ችግሮችን ለመፍታት እድል ፈጥሯል-ፓርቲዎች አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከገዥው ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራትና በመካከላቸው የሚከሰቱ ቅሬታዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እድል መፍጠሩን አንዳንድ አባል ፓርቲዎች ገለፁ። በጋራ ምክር ቤቱ ያልተካተቱ ፓርቲዎችም በአገሪቱ የተጀመረው የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዲጠናከር የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ካነጋገራቸው የጋራ ምክር ቤቱ አባል ፓርቲዎች መካከል የአዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው ጌታቸው ከገዥው ፓርቲ ጋር የሚደረገው ውይይት በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በፓርቲዎች መካከል መግባባትን ከመፍጠር ባለፈ የመጪውን ትውልድ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ለማዳበር የጎላ ሚና አለው ብለዋል። ፓርቲዎች በአንድ አገራዊ ጉዳይ ላይ የሰከነ ውይይት ማድረጋቸው በመካከላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በቀላሉ እልባት ከመስጠቱም ባሻገር ለመደብለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓቱ መጠናከር የማይተካ ድርሻ አለው። በምክር ቤቱ ውስጥም የሁሉም አባል ፖለቲካ ፓርቲዎች አገራዊና ድርጅታዊ አጀንዳዎች እንደሚስተናገዱ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ጠንካራ ክርክሮችን በማድረግ ለህዝብ የሚቀርቡ አማራጭ ሃሳቦች ጎልተው እንዲወጡ ይደረጋል ብለዋል። አቶ አስፋው እንዳሉት እስከታችኛው የስልጣን እርከን ድረስ የምክር ቤቱ አባላት ለሚያነሷቸው ችግሮች ከሁሉም ፓርቲዎች የተውጣጡ አጣሪ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ዘላቂ እልባት እንዲኖር እድል መስጠቱንም ጠቅሰዋል። በጋራ ምክር ቤቱ የተቋቋመው ኮሚቴ በተከሰቱ ችግሮች ዙሪያ የሚያቀርበው ሪፖርት በመነሳት ገዥ

8th Bi-Annual Microfinance Conference kicked off in Hawassa

Image
8th Bi-Annual Microfinance Conference 22.10.2014 - 24.10.2014, Hawassa, Ethiopia Inclusive Finance for Expanding Opportunities to the Financially Excluded Population This conference aims to share good practices and innovative ideas in Microfinance, by providing participants with a forum to exchange ideas aimed at contributing to the development of the microfinance industry and financial cooperatives, and to further strengthening the policy at a national level. Topics will include: Savings mobilization of MFIs; Financial inclusion; SACCOs development and their role in promoting financial inclusion; Value chain financing and MFIs; and Agricultural finance, amongst others. For more information, please visit the  8th Bi-Annual Microfinance Conference website . Source: http://www.mfw4a.org/events/event-details/article/2/8th-bi-annual-microfinance-conference.html

የጅቡቲው የኢንተርኔት ዳታ ሴንተር የኣገሪቱ የኢንተርኔት ፍጥነት ያሻሽለዋል ተባለ

Image
Djibouti internet start-up to boost broadband Internet access in east Africa is still relatively slow and costly but a Djibouti-based technology start-up company has ambitions to help change that. Djibouti Data Centre (DDC), set up by a group of local and international investors 18 months ago, is the first data centre and internet exchange in east Africa connected to eight fibre optic cables that are part of the main internet route from Europe to Asia. The internet route travels through the Mediterranean, Red Sea and into the Indian Ocean, passing by tiny Djibouti, which is sandwiched between Eritrea, Somalia and Ethiopia. African internet users have typically enjoyed little benefit from these cables passing along its coast because connectivity to them has been limited, something the DDC aims to correct as it plans to expand from its home base into Kenya, Ethiopia, South Sudan and Somalia, which are all at varying stages of internet development. “The Djibouti market itself may be

Doctors without Borders transferring successfully its Mother and Child Project in Sidama

Image
Photo: en.alkuwaityah.com Doctors without Borders transferring successfully its Mother and Child Project in Ethiopia Doctors without Borders (MSF) announced the beginning of transferring the successful Mother and Child Healthcare project in Sidama Zone to the Ministry of Health at the end of this month, Ethiopian News Agency (ENA) reported. The philanthropist group has been implementing a Mother and Child Healthcare project providing free medical service for mothers and children in Aroressa and Chire Woredas of Sidama Zone, SNNP regional state, since 2012, the MSF released reported. The MSF have been providing consultations for at least 12027 prenatal and postnatal cases as well as over 2,000 deliveries registered since the initiation of the intervention.  Source:  en.alkuwaityah.com

በዚህ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕ/ ሊግ ውድድር ሲዳማ ቡና እና ሃዋሳ ሲቲ በሜዳቸው ይጫዎታሉ

Image
በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕ/ ሊግ ውድድር መጪው እሁድ ጥቅምት 16፣2007 የሲዳማ ቡና ከሙገር ሲሚንቶ በይርጋለም ስታድዬም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ የምጋጠሙ ሲሆን፤ ሌላው የሲዳማ ክለብ የሆነው ሃዋሳ ሲቲ  በተመሳሳይ ቀን እና ሰዓት በመዳው ኣርባምንጭ ከነማን ይገጥማል።  ለሁለቱም የሲዳማ ክለቦች መልካም እድል ወራንቻ ብሎግ ይመኛል።

From kites to coffee, global cultures on display

Image
Rhythmic drum beats echoed for blocks, and tantalizing smells of made-to-order dumplings and freshly stuffed pupusas welcomed guests to the sixth annual World of Montgomery Festival on Sunday. Westfield Wheaton’s parking lot was transformed into a brilliantly colored display of cultural diversity. Thousands enjoyed the free event showcasing Montgomery County’s rich diversity. The festival was sponsored by Fund for Montgomery and organized by KID (Kids International Discovery) Museum. The museum, which will have a grand opening on Sunday in Bethesda, led many hands-on, kid-friendly activities, such as making, decorating, and flying kites. Parents joined children in directing newly made kites through the windy weekend sky. The museum also organized a festival passport for children, with a scavenger hunt, fun facts about cultures, and a spot for stamps from each country’s booth. “I love this event,” said Amanda West, a mother of two from Silver Spring. “My kids interact with t

የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ ያዘጋጀውን የደኅንነት ማኔጅመንት ፈንድ አቋረጠ

‹‹ፈንዱ የተቋረጠው ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በተገናኘ አይደለም››  ዲኤፍአይዲ በእንግሊዝ መንግሥት ገንዘብ ለኢትዮጵያ የደኅንነት ኃላፊዎች ይሰጥ የነበረው የደኅንነት ማኔጅመንት ፕሮግራም ተቋረጠ፡፡ ሪፕሪቭ የተባለ ነፃ የሕግ አገልግሎት የሚሰጥ የእንግሊዝ ኩባንያና ሌሎች የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞች፣ ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የእንግሊዝ መንግሥት ይህንን ፕሮግራም እንዲያቋርጥ ግፊት ሲያደርጉ ነበር፡፡  እነዚህ ወገኖች ይህንን ግፊት የጀመሩት የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ምክንያት ዜጐችን ከመኖሪያ አካባቢያቸው ያፈናቅላል በሚል ክስ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የግንቦት ሰባት ጸሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመንና በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች፣ ባለፈው ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኤርትራ ለመጓዝ የመን ሰንአ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ውለው ወዲያውኑ ለኢትዮጵያ መንግሥት ከተላለፉ በኋላ፣ በእንግሊዝ መንግሥት ላይ ጫናው እንዲጠናከር ሲጥሩ ነበር፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይልም ሆነ በተገኘው አማራጭ ለመለወጥ የሚታገለው የግንቦት ሰባት አመራር ይሁኑ እንጂ፣ ዜግነታቸው እንግሊዛዊ መሆኑ ተጨማሪ ግፊት ይፈጥራል ብለውም ነበር፡፡ እሳቸው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በእንግሊዝ መንግሥት ላይም ሆነ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ግፊት ከሚያደርጉት መካከል፣ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው ነፃ የሕግ አገልግሎት የሚሰጠው ተቋም የሆነው ሪፕሪቭና የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ ይገኙበታል፡፡ የሪፕሪቭ የሕግ ዳይሬክተር ቲኔክ ሀሪስ በነሐሴ ወር ለእንግሊዝ መንግሥት ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጀስቲገን ግሪንግ በጻፉት ደብዳቤ፣ ‹‹የእንግሊዝ ዜግነት ያለውን ግለሰብ ላገተውና ቶርቸር በማድረግ

በሀዋሳ ከተማ በህይወት ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው የብሉ ናይል ሆቴል ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋለ

Image
በሀዋሳ ከተማ ከአስር ቀን በፊት የሰው ህይወት አጥፍቷል ተብሎ በተጠረጠረበት ወንጀል ሲፈለግ የነበረው የብሉ ናይል ሆቴል ባለቤት አቶ ታምራት ሙሉ ሰሞኑን ከቁጥጥር ስር ውለዋል። ግለሰቡ መስከረም 28 ረቡዕ ጠዋት ሁለት ሰአት ከ15 ገደማ በሀዋሳ መሀል ከተማ አንድ ጠበቃ ሽጉጥ ተኩሶ ህይወቱን በማጥፋትና ሌላኛውን አቁስሏል በሚል ነው የተጠረጠረው። ወንጀሉን ፈጽሞ ተሸሽጎ ነበር የተባለው ተጠርጣሪ ከከተማው መሰወሩን ተከትሎ የክልሉ ፖሊስ ከአዲስ አበባ፣ ከፌደራልና ከክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመተባበር ፍለጋ ሲያካሂድ ቆይቶ ነው፤ ሰሞኑን በቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሀ ጋረደው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት። ግለሰቡ ከሀዋሳ ከወጣ በኋላ አዲስ አበባ፣ባህር ዳር ፣ሚሌና ወሎን አቋርጦ ከሀገር ለመውጣት ሞክሮ ሳይሳካለት ቀርቷል። በዚህም ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ሌላ የማምለጫ መንገድ ሲፈልግ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው። የትኛውም ግለሰብ ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር ለመኮብለል ቢሞክር በጸጥታ ሀይል ቁጥጥር ስር እንደሚውል ከተጠርጣሪው ታምራት ሙሉ ሊማር ይገባልም ብለዋል ኮሚሽነሩ። ግለሰቡ መያዙን ተከትሎም ምርመራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል። የወሬው ምንጭ ኤፍ.ቢ.ሲ ነው

Ethiopia to Host International Coffee Symposium

Image
Ethiopia is to prepare international coffee conference aiming at promoting its brands, said on Monday, the Ethiopian Coffee Exporters Association (ECEA). Accordingly, the conference will take place from 6-7 November 2014 in Addis Ababa. ECEA board chair Hussein Agiraw said that the conference helps the country find better international markets, especially in such countries as China, India, and South Africa with high coffee demand. The coffee yield of Ethiopia, in this year, is expected to have the increase from 20-25 percents from the previous one, he added. The conference is expected to entertain international experiences and papers in the area. Source: allAfrica.com

በማንኛውም ቦታ የሚለበስ የሲዳማ ባህላዊ ልብስ

Image
 የፋሽን ኢንዱስትሪ እየተስፋፋ ከመጣበት ዘመን አንስቶ በርካታ የአለባበስ ልምዶችም አብረው ተፈጥረዋል። በተለይ በአውሮፓውያኑ አካባቢ አንድን ልብስ ከመምረጣቸው በፊት ለምን ጉዳይ እንደሚለብሱትና በምን ወቅት እንደሚያዘወትሩት ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአገራችን የሚዘጋጁ ባህላዊ አልባሳት ጊዜና ቦታ ተመርጦላቸው እንዲለብሱ እየሆነ ነው። ብዙ ጊዜ የባህላዊ አልባሳት በበዓላት ቀን ላይ ብቻ እንዲለበሱ የተወሰኑ ነበሩ። አሁን አሁን ግን የባህላዊ አልባሳትን በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት በተለያዩ ወቅቶች በማንኛውም ቦታ እንዲለበሱ እየደተረገ ነው። በሐዋሳ ከተማ የሚገኘው አበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ማምረቻና ማከፋፈያም ከአገራችን አልፎ እስከ ውጭ አገር ድረስ ባህላዊውን አልባሳት በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት ዕውቅናን እያተረፈ መጥቷል፡፡  ለተጨማሪ ንባብ

ለአካል ጉዳተኛ ህፃናት ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢ የእግር ጉዞ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 10/2007 የአካል ጉዳተኞች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመቅረፍ እኩል እድል፣ ተጠቃሚነትና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡  “የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ  እናድርግ” በሚል መሪ ቃል ለአካል ጉዳተኛ ህፃናት ድጋፍ እንዲውል ቸሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ ሃዋሳ ቅርንጫፍ ለሰባተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰብ የእግር ጉዞ ትናንት በሃዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡ የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተሾመ ታደሰ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት አካል ጉዳተኞች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት  ሙሉ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚረዱ ፖሊስዎችና ስትራቴጅዎች ወጥተው ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ የአካል ጉዳተኝነት መንስኤዎችንና ከሚያስከትሉት ችግር ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ፣ አካል ጉዳተኛና ቤተሰቦቻቸው ከድህነት የሚላቀቁባቸውን ፕሮግራሞችን የመቀየስ እንዲሁም አድሏዊ አመለካከቶችን የመቀየር ስራዎች ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ከ190 ሺህ በላይ አካል ጉዳተኞች እንደሚገኙ ገልፀው ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጡ አካላዊ የተሃድሶ አገልግሎቶችን ሊያሳደጉ የሚችሉ ተቋማትን በሰው ሀይል፣ በፋይናንስና በቁሳቁስ የማደራጀት  ስራዎችም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡ በተለይም በህዝብ መገልገያና መዝናኛ ሥፍራዎች፣ በማህበራዊ መስጫ ተቋማት፣ በህንፃዎች፣ በመንገዶችና በህዝብ መጓጓዣዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሰሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ ስራዎችም ተጠናክሮ ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ ቸሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ የሃዋሳ ቅርንጫፍ  ስራ አስኪያጅ አቶ መሰረት ኪዳኔ በበኩላቸው የእግር ጉዞው ዓላማ

Organic Ethiopian Sidama Fero: Good Food awards finalist 2014

Image
We’re psyched to release one of our seasonal favorites from the Fero Cooperative in Sidama, Ethiopia. Ethiopia is the birthplace of coffee and the Sidama Union of Growers, comprising of 80,000 individual farmers, put the region’s traditional knowledge into practice through nearly 50 regional base co-ops.  We’ve tasted coffee from many of these groups, but over time have zeroed in on the Fero Cooperative. Their coffee shines due to their particular locale, which is vaulted high in the mountains above the Rift Valley at nearly 2,000 meters. This impressive elevation causes the coffee cherries to mature slowly, developing a physically dense bean, filled with nuanced and complex flavors.  We also love the fact that Fero uses washed processing: immediately after harvest, the pulp of the coffee cherry fruit is removed by milling. After that, the bean is fermented, washed and then dried on raised beds. Washed processing results in a cleaner, brighter, more consistent coffee.  In a busin

12 ፓርቲዎች መጪውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ ቅሬታዎቻቸውን በጋራ ለምርጫ ቦርድ አቀረቡ

Image
በ2005 ዓ.ም በትብብር ሲሰሩ የቆዩ 12 ፓርቲዎች ከአሁን ቀደም የጠየቅናቸው ጥያቄዎች ባልተመለሱበት ሁኔታና አሁንም ከአሁን ቀደም የተነሱትን ጥያቄዎች የሚያጠናክሩ ተግባራት እየተፈጸሙ በመሆኑ ከሀገራዊ ምርጫው በፊት ሊፈቱ ይገባቸዋል ያሏቸው ጉዳዮችን በተመለከተ ምርጫ ቦርድም ኃላፊነቱን  እንዲወጣ በጋራ በጻፉት ደብዳቤ ጠየቁ፡፡ ፓርቲዎቹ ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም. በጻፉትና ዛሬ ለቦረወዱ ባስገቡት ደብዳቤ ላይ እንዳመለከቱት በመንግስት/ገዢው ፓርቲ በማንአለብኝነት የተወሰዱ ህገ-ወጥ እርምጃዎች ዘላቂ ልማትና ሠላም፣ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ፣ ህገ-መንግስታዊ፣ ሰብዐዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አከባበርና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ ፓርቲዎቹ በጋራ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል፡- 1ኛ/ በተለያየ የመዋቅር ደረጃ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ማስፈራራት፣ የአካላዊና የንብረት ጉዳት ማድረስ፣ በሃሰት ውንጀላና የፈጠራ ክስ ማሰር፣ እየተጠናከረ መምጣትና በዚህም የፓርቲዎችን በዕቅዳቸው መሰረት የመሥራትና የዕለት ተዕለት ነጻ ህጋዊ እንቅስቃሴ መገደብ፤ 2ኛ/ በአንድ በኩል የሠላማዊ ትግል ስልቶች ተግባራዊ የሚሆኑበትን መንገድ በመዝጋት፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከህዝብ ጋር እዳይገናኙና ዓላማቸውን፣ ፕሮግራማቸውንና አማራጭ ፖሊሲዎቻቸውን ለህዝብ እንዳያደርሱ በማድረግ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ገዢው ፓርቲ ከምርጫ የጊዜ ሰሌዳ በፊት በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን፣ መንግስታዊ መዋቅርና ሃብት በመጠቀም ለት ተለት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እየጠመቀ የምርጫ ቅስቀሳ ያደረገበትና እያደረገ ያለበት ሁኔታ ግልጽ መሆኑ፤ 3ኛ/ ገዢው ፓርቲ ከመንግስት ካዝና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ተቀብሎ ያለምንም መስፈርት ለሚፈ