Posts

የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሸጉጤ በወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ለመምከርና ጥሩ የሥራ አፈጻጸም ያላቸውን ኢንቨስተሮች ለማበረታታት በጠሩት ስብሰባ ላይ፣ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መማረራቸውን አስታውቀዋል፡፡

Image
ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተማረሩ -  ልማት ባንክ ቅሬታቸውን አልተቀበለም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከአዲስ አበባ 275 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሐዋሳ ከተማ የተሰበሰቡ ኢንቨስተሮች፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ብድር እየሰጠ አይደለም ሲሉ አማረሩ፡፡  ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2005 ዓ.ም. የትምህርት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሸጉጤ በወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ለመምከርና ጥሩ የሥራ አፈጻጸም ያላቸውን ኢንቨስተሮች ለማበረታታት በጠሩት ስብሰባ ላይ፣ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መማረራቸውን አስታውቀዋል፡፡  ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ‹‹በትራንስፎርመር እጥረት›› በሚል ምክንያት የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር እየገጠማቸው መሆኑን በመጥቀስ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡  በተወሰነ ደረጃ በኢትዮ ቴሌኮም በኩልም ችግር መኖሩን የሚጠቅሱት ኢንቨስተሮች በክልሉ በኩልም የመሬት አቅርቦት፣ በዞኖችና ወረዳዎች የመልካም አስተዳደር እጦትና የወሰን ማስከበር ችግሮች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡  በደቡብ ክልል ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ 6,150 ኢንቨስተሮች ፈቃድ አውጥተው ቦታ ወስደዋል፡፡ ለስብሰባ የተጠሩት ውጤታማ ናቸው የተባሉ 1,500 የአገር ውስጥና የውጭ አገር ኢንቨስተሮች ናቸው፡፡  ኢንቨስተሮቹ የተሰማሩት በእርሻ፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት መስጫዎችና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ነው፡፡ እነዚህ ኢንቨስተሮች ሥራቸውን ለማስፋፋት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ቢጠይቁም ሊሰጣቸው እንዳልቻለ፣ በአንፃሩ ባንኩ ለውጭ ኩባንያዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ሲሰጥ መታዘባቸውን በመናገር ምሬታቸውን ገል

በሃዋሳ ከተማ ከ11 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የትራፊክ ኮምፕሌክስ ህንፃ እየተገነባ ነው

ሃዋሳ ሐምሌ 2/2005 በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማ ከ11 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የአሽክርካሪ ብቃት ምዘና የሚደረግበት ዘመናዊ የትራፊክ ኮምፕሌክስ ህንፃ ግንባታ ከ85 በመቶ በላይ መጠናቀቁን የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡ በአርባምንጭ፣ በሆሳዕናና በሚዛን አማን ከተሞች ከ30 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ተጨማሪ የትራፊክ ኮምፕሌክስ ግንባታ ለማካሄድ አሰፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁም ተገልጿል፡፡ በቢሮ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዋና የስራ ሂደት አስተባበሪ አቶ ውቤ ለሳ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በመደበው ወጪ የተጀመረው የተቋሙ ግንባታ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ ግንባታው ከሶስት ወር በኋላ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል፡፡ በክልሉ በየጊዜው የሚከሰተው የትራፊክ አደጋ በአብዛኛው የአሽክርካሪዎች ብቃት ማነስ ነው ያሉት አስተባባሪው ይህንና የቀድሞውን የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ችግር በመቅረፍ ቀልጣፋ የአሽከርካሪዎች ምዘናን የሚያረጋግጥ ግልፅና ውጤታማ አሰራር ለመዘርጋት እንደሚያስችል የስራ ሂደቱ ባለቤት ተናግረዋል፡፡ በሃዋሳ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የአሽከርካሪዎች ምዘና የትራፊክ ኮምፕሌክስ ተቋም በኮምፒውተር መረጃ ኔትወርክ የተገናኙ የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎችና ዘመናዊና አዲስ የመፈተሻ ቴክኖሎጂ ይገኙበታል ብለዋል፡፡ አሰራሩን በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ የክልሉ መንግስት በመደበው 30 ሚሊዮን ብር በአርባምንጭ፣ በሆሳዕናና በሚዛን አማን ከተሞች የአሽከርካሪ ብቃት ምዘና የሚደረግባቸው ዘመናዊ የትራፊክ ኮምፕሌክስ ግንባታ ለማስጀመር ዝግጅቱ መጠናቀቁንና በሁለቱ ከተሞች ከያዝነው ወር ጀምሮ ስራው መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

የ121 ዓመት አድሜ ባለጸጋ የሆኑት የአቶ ጠቀቦ ሾታ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ::

ዲላ ሐምሌ 02/2005 የጌዴኦ አርሶ-አደር በነፍጠኛው ስርዓት ላይ ባካሄደው ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት እና የ121 ዓመት አድሜ ባለጸጋ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ። የአቶ ጠቀቦ ሾታ ቀብር በጌዴኦ ባህላዊ ስነ-ዓስርዓት በዲላ ዙሪያ ወረዳ ዛሬ ተፈጸመ ። አቶ ጠቀቦ ሾታ ከአስራ ሁለት ሚስቶቻቸው ሰማንያ ሰባት ልጆች እና ከአንድ ሺህ በላይ የልጅ ልጅ ያፈሩ እንደነበሩም በቀብር ስነስረአቱ ላይ በተነበበዉ የህይወት ታሪካቸው ላይ ተገልጿል ። አቶ ጠቀቦ ሾታ በ1884 ዓመተ ምህረት በዲላ ዙሪያ ወረዳ ሚቺሌ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መወለዳቸዉን ቀብር ስነ-ስርዓታቸው ላይ የተነበበው የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል ። በጌዴኦ አርሶ አደር ላይ ይደርስ የነበረውን የጭቆና አገዛዘ በጽኑ በመቃወም በ1952 ዓመተ ምህረት በነፍጠኛው ስርዓት ላይ ከፍተኛ ጥቃት በመሰንዘር የሚቺሌን ድል ካስመዘገቡ አባቶች መካከል አንዱ ነበሩ ። አቶ ጠቀቦ ሾታ ከዚህ የትጥቅ ትግል በመለስ በጌዴኦ ብሄርና በአጎራባች ወረዳዎች እና ክልል ህዝቦች መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲሰፍን በማድረግና ግጭቶች እንዳይከሰቱ የበኩላቸውን ከመወጣታቸውም ባሻገር የጌዴኦ ባህልን ለማሳደግ የዞኑን ልማት ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ተጠቁሟል ። በህዝባዊ ውይይቶች ህብረተሰቡን በመወከል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ በመሆን ለጌዴኦ ህዝብ እድገት የበኩላቸውን መወጣታቸውንና ለፈጸሙት መልካም ተግባር በጌዴኦ ባህል ለጀግና የሚሰጠውን የሀይቻነት ማእረግም ማግኘታቸውም ተመልክቷል ። የረጅም እድሜ ባለጸጋ የሆኑት አቶ ጠቀቦ ሾታ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ የደቡብ ብሄር ብሄርሰቦችና ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የጌዴኦ ዞን ካቢኔ አባላት የስድስቱም ወረዳና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁ

የቀድሞው የሃዋሳ ከተማ ስራ ኣስኪያጂ የነበሩት እና በኃላ ላይ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ዳይሬክተር የሆኑትን ኣቶ ተፈሪ ፍቅሬ ጨምሮ ሌሎች ሁለት ዳይሬክተሮች በኪራይ ሰብሳቢነት ተገምግመው ከስራ ሃላፊነታቸው ተነሱ::

የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ተፈሪ ፍቅሬና ሁለት ምክትል ዳይሬክተሮች በኪራይ ሰብሳቢነት ተገምግመው ከስራ ሃላፊነታቸው እንደተነሱ ተገለፀ፡፡ ተጠሪነቱ ለስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የሆነው የቤቶች ኤጀንሲ ከትላንት በስቲያ ሶስቱን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ከሥራ ሃላፊነታቸው ያነሳው በተለያየ ደረጃ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽንም ከአንድ ዓመት በላይ በሥራ ሃላፊዎቹ ላይ ምርመራ ሲያደርግ እንደቆየ የጠቀሱ ምንጮች፤ ሃላፊዎቹ በኪራይ ሰብሳቢነትና ሃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት ተገምግመው ነው ከሥራ ሃላፊነታቸው የተነሱት ብለዋል። http://dezetube.com/article_read.php?a=451

የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ፌዴራል መንግሥት ሚኒስትርነት መምጣት በደቡብ ክልል ላይ ጊዜያዊ ክፍተት የፈጠረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለክልሉ ፕሬዚዳንትነት የስድስት ግለሰቦች ስሞች እየተነሱ ነው፡፡

የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ፌዴራል መንግሥት ሚኒስትርነት መምጣት በደቡብ ክልል ላይ ጊዜያዊ ክፍተት የፈጠረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለክልሉ ፕሬዚዳንትነት የስድስት ግለሰቦች ስሞች እየተነሱ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርነታቸው በመነሳት በኦሮሚያ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ደሚቱ ሃንቢሳ የተተኩት አቶ ደሴ ዳልኬ አንደኛው ናቸው፡፡ ሌሎቹ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ማርቆስ ተክሌና በአሁኑ ወቅት የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን የሚያገለግሉት አራት ግለሰቦች ናቸው፡፡  እነሱም አቶ ታገሰ ጫፎ፣ አቶ ዓለማየሁ አሰፋ፣ አቶ ሳኒ ረዲና አቶ ደበበ አሰፋ ናቸው፡፡ ግምት ከተሰጣቸው መካከል የበለጠ ከፕሬዚዳንትነት ሥልጣኑ ጋር በተደጋጋሚ ስማቸው እየተጠራ የሚገኘው አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ሲሆኑ፣ በሁለተኛ ደረጃ አቶ ደሴ ዳልኬ ሊሆኑ ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡ ባለፈው ሐሙስ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የከፍተኛ መንግሥት ባለሥልጣናትን ሹመት በፓርላማ አፀድቀዋል፡፡ የአሥሩ አዲስ ተሿሚዎች ሹመት የፀደቀው በአንድ ድምፅ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ ነው፡፡ ተሿሚዎቹ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካይነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ባለፈው ረቡዕ አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ኩማ ደመቅሳ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊስ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው መመደባቸው ተገልጿል፡፡  በቅርቡ በፓርላማ የትምህርት ሚኒስቴርን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ በዘርፉ ለሚታዩ ችግሮች ከሚኒስትር ጀምሮ እስከታች ያሉ አመራሮችን የወቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ በአቶ ኃይለ ማርያም አዲስ ሹመትና ሽግሽግ ከትምህርት ሚኒስትርነታቸው ተነስተዋ

የኢትዮጵያ ቡና ከዓለም ገበያ እየራቀ መሆኑ ሥጋት ፈጥሯል

Image
የኢትዮጵያ ቡና ከዓለም አቀፍ ገበያ እየራቀ መጥቶ፣ ከነጭራሹ ሊወጣ የተቃረበበት ጊዜ ላይ እንደሚገኝ ለዘርፉ ቅርብ የሆኑ ተዋንያዎች የሚስማሙበት ሀቅ ነው፡፡  ኢትዮጵያ ለዓለም ቡናን ያበረከተች አገር ከመሆኗ ባሻገር እጅግ ተወዳጅ የሆነ ቡና የምታመርት አገር ናት፡፡ ዓለም አቀፍ የቡና ገዥዎች ይህንኑ የጣዕም ልዩነት በመረዳት የኢትዮጵያን ቡና ለመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ በቢሮክራሲ ውጥንቅጦች ምክንያት ቡናውን ማግኘት እንዳልቻሉ እየተናገሩ ነው፡፡  በቡና ግብይት ላይ ያለው ውጣ ውረድ ከፍተኛና ገዥዎች የማይተማመኑበት ደረጃ ላይ እየደረሰ በመሆኑ፣ በዓለም አቀፍ ገበያ በጣዕሙ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የኢትዮጵያ ቡና ዋጋ እያጣ መምጣቱ የሚያስቆጭ ወቅታዊ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የችግሩ ምንጮች በዋነኛነት የመንግሥት የቡና ግብይት አቀንቃኞቹ የንግድ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት እንደሆኑ የዘርፉ ተዋናዮች ያምናሉ፡፡  የቡና ግብይት ተዋናዮች እንደሚሉት፣ የችግሩ ምንጮች በእነዚህ ሁለት መንግሥታዊ ተቋማት የተወለዱ ችግሮች ናቸው፡፡ በመጀመሪያ የንግድ ሚኒስቴር የቡና ግብይት ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች የቡና ግብይት ሁኔታን በሚገባ አለመረዳታቸው ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የሥራ ኃላፊዎች የግብይት ሁኔታውን ቢያውቁም፣ የመወሰን አቅም የሌላቸው በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹እነዚህ አካላት ግን ያሉባቸውን የተወሰኑ ችግሮች ለማረም አልሞከሩም፤›› ይላሉ የተበሳጩት የቡና ግብይት ተዋናዮች፡፡ በምርት ገበያ በኩል አሉ ከሚባሉት ችግሮች መካከል አንዱ የቡና ልኬት (ሚዛን) ችግር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቀደም ባሉት ዓመታት በቡና ግዥ ሒደት የቡና ገለፋት በ20 በመቶ ታሳቢ ተደርጎ በግዥ ሒደት ቅናሽ ይደረግ ነበር፡፡ አሁን ባለው የምርት ገበያ

የቀድሞው የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ይሾማሉ

Image
ላለፉት ሶስት ዓመታት የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን የሰሩት አቶ ደሴ ዳልኬ፤ የደቡብ ክልል ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ሆነው እንደሚሾሙ ምንጮች ገለፁ፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ያገለገሉት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከትላንት በስቲያ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን፤ እሳቸውን በመተካት አቶ ደሴ ዳልኬ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው ይሾማሉ ተብሏል፡፡ ባለፈው ሐሙስ በፓርላማ በተካሄደው የካቢኔ ሹመት ወ/ሮ ዳሚቱ ሐሚሳ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል፡፡ በመጪው ሳምንት የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባለፈው ሳምንት ከአስር በላይ የሚኒስትሮች ሹመት በፓርላማ መጽደቁ ይታወቃል፡፡ http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=12564:%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8B%B5%E1%88%9E%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%88%A3%E1%8B%AD%E1%8A%95%E1%88%B5-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%89%B4%E1%8A%AD%E1%8A%96%E1%88%8E%E1%8C%82-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%8B%B0%E1%89%A1%E1%89%A5-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D-%E1%8D%95%E1%88%AC%E1%8B%9A%E1%8B%B3%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%88%86%E1%8A%90%E1%8B%8D-%E1%8B%AD%E1%88%BE%E1%88%9B%E1%88%89&Itemid=180

ትምህርት ሚኒስቴርነት፤ በማማረር ወይስ በማባረር…! ?

ትምህርት ሚኒስቴርነት፤ በማማረር ወይስ በማባረር…! ? መንጌ የነገረኝ ቀልድ ትቅደም፤ መንጌ ማለት አሉኝ ከምላቸው ጓደኞቼ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እሳት የላሰ የአራዳ ልጅ ነው፡፡ “ካራዳ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱ፤ ባይበሉም ባይጠጡ ስንቅ ይሆናል ቀልዱ”  የተባለለት ጨዋታ አዋቂ! አንድ ሙዝ ነጋዴ ነበር አለኝ መንጌ… እሺ… ሙዙ ገበያ ሲያጣ ምን ያደርጋል መሰለህ… እ… የተሰቀለውን ያወርደዋል፡፡ መሬት የነበረውን መስቀያው ላይ ያንጠለጥለዋል፡፡ እንደርሱ ብቻ አይደለም፤ “ሙዝ አትፍዘዝ ተንቀሳቀስ…” ሲልም ያበረታታዋል… አለኝ፡፡ እኔ ፋራው የምጠይቀው ጥያቄ ነው እንጂ የሚገርመው… ከዛስ…  አልሸጥ ያለው ሙዝ ይሻጣል….  ወይስ ይንቀሳቀሳል…? መንጌ ይስቃል… እርስዎም ይሳቁ፡፡ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሙዙ ነጋዴ ናቸው፡፡ የሱቁ ባለቤቶች “እስቲ ደግሞ ለአኬር፤ ሙዝ አትፍዘዝ ተንቀሳቀስ” ይበሉ … ብለዋችው ይሁን; በራሳቸው ተነሳሽነት እንጃ ሞዛዞቻቸውን ቦታ አቀያይረዋቸዋል፡፡ (ሙዛ ሙዞቻቸውን ማለቴ ነው….) አቶ ሬድዋን የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር… ተደርገዋል፡፡ የምርም ስለ ኢህአዴግዬ ዋይ ዋይ ለማለት እርሳቸው ሳይሻሏት አይቀሩም፡፡  ምክንያቱም አቶ በረከት ስምዖን ቻርጅ እንዳለቃቸው በጣም ያስታውቃሉ፡፡ (ጢን… ጢን.. ማለት ከጀመሩ ቆይተዋል) ስለዚህ ነጋ ጠባ ስለ ድርጅታቸው በየአደባባዩ እየተከሰቱ “በላውድ ስፒከር” ሊጮሁላት አይቻላቸውም፡፡ እናም፤ ባትሪ ፉሉ አቶ ሬድዋን መተካታቸው ለዚህ ቦታ ትክክል ይመስለኛል፡፡ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስቴር… ይሄኛው ያስቃል፡፡  የሰውዬው የስራ ልምድ እኮ አስተኳሽነት ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ የስራ ልምዳቸው እንደ ጥይት የሚተኳኮስ የትራንስፖርት ስርዓት ይዘረጉልናል፡፡ ብ

Ethiopia: Parliament Approves PM's Appointment of New Ministers_Hailemariam appointed Shiferaw Shigute as minister of education.

Image
House of Peoples Representatives today approved the appointment of ten ministers nominated by Prime Minister Hailmeriam Desalegn. Before announcing his appointments, PM Hailemariam told parliamentarians that Deputy Prime Minister Demeke Mekonnen is relieved of his post as minister of education. Hailemariam appointed Shiferaw Shigute as minister of education. Shiferaw has been serving as Chief Administrator of Southern Nations, Nationalities and Peoples' Region (SNNPR) since March 2006. Redwan Hussien, who was public mobilization and participation advisor minister to the PM and head of EPRDF Secretariat, has replaced Bereket Simon as Minister of Government Communications Affairs Office. Bereket and outgoing Addis Ababa City mayor Kuma Demeksa yesterday were appointed as policy and research advisor ministers to the Prime Minister. Workneh Gebeyehu, who was commissioner of the Federal Police Commission, is appointed as Minister of Transport replacing Diriba Kuma. Mekonnen

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ - የትምህርት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ የመንግስት ሚኒስትሮችን እና የስራ ሃላፊዎችን ሹመት አጸደቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሰላኝ የቀረቡ እጩዎችን ሹመት በ1 ድምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል። በዚህም መሰረት አቶ ደመቀ መኮንን - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ - የትምህርት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ-  የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር አቶ አህመድ አብተው አስፋው - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ - የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ መሸሻ - በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ ቦንሳ - የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው አምባዬ በለው - የፍትህ ሚኒስትር አቶ በከር ሻሌ ዱሌ - የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ - የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደሻው - የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን የተሾሙ ሲሆን ፥ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል።

የስምንት ሚኒስትሮች ሹመት ሰሞኑን ይፀድቃል

የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ዛሬ ግምገማ ያካሂዳል የኢህአዴግ 36 ከፍተኛ መሪዎችን ያካተተው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመታዊ ግምገማ ለማካሄድ ዛሬ የሚሰበሰብ ሲሆን የስምንት ሚኒስትሮች ሹም ሽርና ሽግሽግ በሚቀጥለው ሳምንት ለፓርላማ ቀርቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል፡፡ ለሹመት የሚቀርቡት ባለስልጣናት፤ የፍትህ ሚኒስትር፣ የከተማና ኮንስትራክሽን ልማት ሚኒስትር፣ የግብርና ሚኒስትር፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር፣ የገቢዎች ሚኒስትር የደህንነትና መረጃ ሚኒስትር፣ የደንና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር እንዲሁም በፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ናቸው ተብሏል፡፡ አንዳንዶቹ ሹምሽር እርምጃዎች ሲሆኑ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር እንዲዛወሩ በተደረጉ ባለስልጣናት ምትክ የሚካሄድ ሽግሽግ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የእጩ ተሿሚዎችን ማንነት ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡ ዛሬ የሚካሄደው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከሹምሽሩ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ቢታሰብም፣ የሰብስባው ዋና ርዕሰ ጉዳይ አመታዊ ግምገማና አመታዊ እቅድ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት አስፈፃሚ አካል የመቆጣጠር ስልጣን ያለው የአገሪቱ ፓርላማ ጠንካራ የቁጥጥር ሃላፊነቱን በተግባር ማሳየት እንደጀመረ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጭምር ቢናገሩም፤ በሚኒስትሮች ሹመት ዙሪያ ግን የቀድሞው አሰራር አልተሻሻለም፡፡ በተለያዩ ዲሞክራሲያዊ አገራት ውስጥ የእጩ ሚኒስትሮች ማንነት በይፋ ታውቆ ለበርካታ ሳምንታት በፓርላማና በዜጐች ዘንድ ውይይት የሚካሄድበት ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ግን የተሿሚዎች ማንነት የሚገለፀው ሹመታቸው በሚፀድቅበት እለት ነው፡፡ የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባ እንደሚያካሂድ የገለፁት የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን፤ የስብሰባው ዓላማ የዓመቱን የስራ አፈፃፀም

በመጪዎቹ 10 ቀናት በርካታ ቦታዎችን የሚሸፍን ዝናብ ይኖራል

Image
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2005 (ዋኢማ)  - በመጪዎቹ አሥር ቀናት በመደበኛ ሁኔታ የክረምት ዝናብ ሰጪ ክስተቶች በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመጠናከራቸው ጋር ተያይዞ ብዙ ቦታዎችን የሚሸፍን ዝናብ እንደሚኖር ብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡  በመጪዎቹ ቀናት ዝናብ ሰጪ ክስተቶች በአብዛኛው የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል፡፡  በመሆኑም አብዛኛውን የወቅቱን ዝናብ ተጠቃሚዎች የሚያዳርስ የተስፋፋ ዝናብ እንደሚኖርና አልፎ አልፎም በአንዳንድ ሥፍራዎች ላይ ከባድ ዝናብ ይከሰታል፡፡ በዚሁ መሠረት የትግራይና የአማራ ምዕራባዊ አጋማሽ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የጋምቤላ፣ የምዕራብና የመካከለኛው ኦሮሚያ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አብዛኛው ክፍል መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ፡፡  እንዲሁም የምሥራቅ አማራና ትግራይ፣ የአፋር፣ የምሥራቅ ኦሮሚያ፣ የድሬዳዋ፣ የሐረሪና የሰሜን ሶማሌ አካባቢዎች ከመደበኛው ጋር የተቀራረበ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ በረዶ የቀላቀለና ነጎድጓዳማ ከባድ ዝናብ እንደሚኖር የጠቀሰው የኤጀንሲው መግለጫ ቀሪዎቹ የአገሪቱ አካባቢዎች ደረቅ ሆነው ይሰነብታሉ ብሏል፡፡ በነዚሁ ቀናት መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንዲሁም ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ በሚጠበቅባቸው የአገሪቱ ምሥራቃዊ አካባቢዎች የሚገኘው ዝናብ ለመኸር እርሻ ሥራ እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር የተገኘውን እርጥበት በመጠቀም የወቅቱን እርሻ ለማካሄድ ያስችላል፡፡  በአንዳንድ ሥፍራዎች ላይ የሚጠበቀው ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ በተዳፋትና ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች እርሻ ማሳዎች ላይ የአፈር መሸርሸርና የውሃ መተኛት ሊያጋጥም

ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተጀመረው የ15 ከተሞች የውኃ ፕሮጀክት ተቋረጠ

-    ፕሮጀክቱ የተቋረጠው የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ውሉን በማፍረሱ ነው የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዓመታት በፊት ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የጀመረው የ15 ከተሞች የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተቋረጠ፡፡ የፕሮጀክቱን ወጪ ብድር የሰጠው የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ውሉን ማፍረሱ ለፕሮጀክቱ መቋረጥ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብና በትግራይ ክልሎች ለሚገኙ 15 ከተሞች የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሻሻልና 500 ሺሕ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሦስት ዓመታት በፊት የተጀመረውን ፕሮጀክት በሁለት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞ ነበር፡፡  ፕሮጀክቱ የሚፈጀውን ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወይም 36 ሚሊዮን ዩሮ በብድር የለገሱት የአውሮፓ ኮሚሽንና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በጋራ በመሆን ነበር፡፡  በዚህ ከፍተኛ ገንዘብ ፕሮጀክቱ በ15 ከተሞች ቢጀመርም በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቅ ባለመቻሉ፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የሰጠውን 16 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ውል ለማፍረስ መገደዱን ምንጮች ያስረዳሉ፡፡  በጉዳዩ ላይ የተጠየቁት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ለፕሮጀክቱ መጓተት ኮንትራክተሮችን ወቅሰዋል፡፡ ኮንትራክተሮቹ በባንኩ የጨረታ ሕግ ተገምግመው ሥራው ቢሰጣቸውም ደካማ በመሆናቸው ፕሮጀክቱን በጊዜው መፈጸም አለመቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ ከኮንትራክተሮቹ ላይ ለመንጠቅ በባንኩ አሠራር የተነሳ በመቸገሩ ሥራው መጓተቱን፣ በውሉ መሠረት ፕሮጀክቱ በጊዜው ባለመጠናቀቁ ውሉ ሊቋረጥ ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡ ከዚህ ጉዳት በመነሳትም የውኃ ሥራ ኮንትራክተሮች ከዚህ በኋላ ፈቃዳቸውን ሊያድሱ የሚችሉት ብቃታቸው ተገምግሞ እንደሚሆን፣ በዚህ ፕሮጀክት ላይ ጉዳት ያደረሱትንም

በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ለሙስና ኮሚሽን ጥቆማ ቀረበ ተባለ

ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በደቡክ ክልል ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ በቤተሰቦቻቸው እና በሃዋርያት ቤተክርስቲያን መሪዎች ስም በመሬት ቅርሚያ እና ችብቸባ ስራ ላይ ተሰማርተው ነበር ሲሉ አንድ ከአዋሳ ግለሰብ የመጡ ማስረጃቸውን አያይዘው ለሙስና ኮሚሽን ጥቆማ መስጠታቸውን አንዲት በኮሚሽኑ ውስጥ የሚሰሩ ግለሰብ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::ግለሰቧ እንዳሉት ወደ ኮሚሽኑ የመጡት ሰው የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አማካሪ የነበሩ ሲሆንጥቆማውን እና ማስረጃቸውን የተቀበሏቸው በቀጠሮ ኮሚሽነር አሊ ሲሆኑ ለረዥም ሰአት ተነጋግረዋል:: በአቶ ሃይለማርያም ላይ የመጣው ጥቆማ እንደሚያመለክተው ብስልጣናቸው ተጠቅመው በኢናታቸው እና በአባታቸው ቤተሰቦች ስም እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን መሪዎች ስም ለተለያየ ጊዜ መሬቶችን በመውሰድና በመሸጥ ሰፋፊ እርሻዎችን በመያዝ የቡና እና የፍራፍሬ ተክሎችን ወደ ኬንያ በኮንትሮባንድ በመላክ የኢትዮጵያን ድንበር ተገን በማድረግ በህገወጥ ንግድ እና የመሳሪያ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ከለላ በመስጠት የተለያዩ ስኮላርሺፖችን በማስመጣት እና በመሸጥ እንዲሁም ከትግሬ ጄኔራሎች ጋር በመተባበር የሃሰት ሰንዶችን በማዘጋጀት የመንግስት እና የህዝብ ንብረቶችን ዘርፎ በማዘረፍ የሚሉ እና ተመሳሳይነት ያላቸው ጥቆማዎች እንደተሰጡ ግለሰቧ ገልጸዋል:: አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች በሃዋርያት ቤተክርስቲያን ስም የራሳቸውን ህንጻ ገንብተዋል እየገነቡም ነው ለመገንባትም የታሰቡ ፕሮጀክቶች አሉ የሚል ተደራራቢ የህንጻ ግንባት ጥቆማ ተደርጎባቸዋል:: ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሃዋርያት ቤት ክርስቲያን አቶ ሃይለማርያምን እና ሌሎች ባለስልጣናትን ተገን በማድረግ በሙስና መጨማለቋን እኚሁ ግለሰብ ከሰጡት ጥቆማ ጋር የተገለጸ ሲሆን

Trash talk_Hawassa is a surprisingly and refreshingly clean city

Image
Hawassa is a surprisingly and refreshingly clean city. When we traveled to the south and visited cities of comparable size they more closely resembled my preconceptions of an African city, a bit dirtier than it is here. There are a few methods of trash disposal here, incineration being the most common. Below is an example from the other day on campus. In this case, we were lucky and the female students were unlucky. On other occasions we are the unlucky ones downwind from the burning trash. Unfortunately, plastic makes up much of what is being incinerated, which makes me cringe a little, but I can also see the lack of alternatives. The good news is that Ethiopians have taboos about wasting food, so prudence is taken to not create food waste and, to my knowledge, most food scraps are kept separate from other trash and ultimately composted. Female dorm downwind from burning trash Our trash, along with the trash of the other guesthouse residents, goes in a hole located a short

Signs of health and safety in Hawassa

Image
Busy with packing, goodbye lunches and dinners, etc., etc. So, I’ll quickly share some more public health signage from around campus and downtown Awassa. There are a few variations of this sign located throughout campus, including one with a quote from Helen Keller, “Disability is a reality for me, but a possibility for all.” located at the main entrance of Hawassa University main campus vaccinate! The billboard below emphasizes that ones financial situation should be an important part of family planning. family planning Some of the billboards are very graphic so as to get their point across. anti female genital cutting sign Here’s a sign promoting the use of crosswalks, or zebras as they call them. Unfortunately, it is rare for a car to actually stop for a pedestrian in the crosswalk, so they are less effective than they could be. I always thank my bajaj driver when he actually stops to let a pedestrian pass. Source:  http://awayinawassa.wordpress.com/

HwU hands over a Poultry Center it establishes at Hulla District

Image
It has been two years since HwU established technology villages to manage the research activities in an organized manner, test improved findings down on farmers’ field and smoothen technology transfer to the society. The villages are located in 6 different districts of Sidama Zone. Hulla District is one of these 6 villages where HwU funded poultry center inaugurated on June 22, 2013. The poultry center has been handed over to an association named ‘Birhan’ formed by 24 unemployed youth local residents.  According to a report read on the inaugural ceremony, the poultry center costed HwU more than 350,000ETB without considering the professional and laborious contributions. Therefore, the University provided the center with 1210 hens, feedings for 3 months and 20 cages. HwU also covers a lodging expense of the youth during their stay in Hawassa to receive training in the University and their transportation. Speaking on the occasion, Dr. Tesfaye Abebe, Director Research and Development a

በሀዋሳ ከተማ ዘንድሮ ከ33 ሺህ በላይ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ሆኑ

Image
አዋሳ ሰኔ 24/2005 በሀዋሳ ከተማ በዘንድሮ የበጀት አመት ከ33 ሺህ በላይ ወጣቶችና ሴቶች የቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የኢንተርፕራይዞች ልማት ድጋፍ ማዕቀፍ አፈጻጸምና ክትትል ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኤፍሬም አለማየሁ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ወጣቶችና ሴቶች የሥራ እድል ተጠቃሚ የሆኑት በማኒፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን ፣ በከተማ ግብርና፣ በአገልግሎትና በንግድ ስራ ዘርፎች ተደራጅተው በተደረገላቸው ሁለገብ ድጋፍ ነው፡፡ ከተጠቃሚዎች መካከል 11ሺህ 612 ሴቶች መሆናቸውን አስተባባሪው ገልፀዋል፡፡ የሥራ እድል ተጠቃሚ የሆኑት እነዚሁ ወጣቶችና ሴቶች ከ17 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር በላይ እንዲቆጥቡ መደረጉንም አመልክተዋል፡፡ በመምሪያው የኢንተርፕራይዞች ልማት ዋና የስራ ሂደት አሰተባባሪ አቶ ውቤ ቤላሞ በበኩላቸው ከ18 ሺህ 600 ለሚበልጡ አንቀሳቃሾች የንግድ ስራ አመራር፣ የቴክኒክ ሙያ ፣ የምክር አገልገሎት፣ የተስማሚ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ድጋፍ መሰጠቱን ጠቁመው ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ የብድር ገንዘብ በመከፋፈል እንዲጠናከሩ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ለሌሎች 7 ሺህ 772 አንቀሳቃሾች ደግሞ ከ186 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስሰርና ገቢ እንዲያገኙ መደረጉን በመምሪያ የማምረቻ ማዕከላት ግንባታ ማስተዳደርና የገበያ ልማት ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አለማየሁ አብርሀም አስረድተዋል፡፡ የተፈጠረው የገበያ ትስሰርና ገቢውን ያገኙት ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ባዛርና አውደርኢ በማዘጋጀት፣ በኮብል ስቶንና በሌሎችም የግንባታ ስራዎች ቅድሚያ ዕድል እንዲያገኙ በመደረጉ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም 18 ሺህ 526 ካሬ