በሀዋሳ ከተማ ከ34 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነቡ ነው
የወሬው ምንጭ ኢዜ ኣ ነው በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ማዕከል በሆነው ሀዋሳ ከተማ ከ34 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንደሚገነቡ የክልሉ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ሰፋፊ ይዞታ ያላቸውና ለኪራይ የሚሆን ቤት ለሚገነቡ ግለሰቦች የብድር አገልግሎት የሚውል ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ መመቻቸቱም ተመልክቷል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አስቻለው ካሳዬ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት በከተማዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል ግንባታው የሚካሄደው ከመጪው ዓመት ጀምሮ ነው፡፡ "የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የገቢ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚገነቡ ሲሆን ከ34 ሺህ ቤቶች ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት በአስር ዘጠና መርሀ ግብር የሚገነቡ ናቸው" ብለዋል፡፡ በአስር ዘጠና መርሀ ግብር ለሚገነቡት ስቱዲዮ ቤቶች የሚመዘገቡ ቤት ፈላጊዎች በወር 199 ብር ሄሳብ ለሶስት ዓመት መቆጠብ አለባቸው፡፡ " ለባለ አንድ መኝታ ቤት 368 ብር ለባለ ሁለት መኝታ 575 ብር እና ለባለሶሰት መኝታ ቤት ደግሞ 739 ብር በወር ለሰባት ዓመት የቆጠበ የቤት ባለቤት መሆን ይችላል " ሲሉ ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡ ለግንባታው የቦታ ፣ የገንዘብና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ጠቁመው ለቤት ፈላጊዎች ምዝገባው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡ ተመዝጋቢዎች ከተመዘገቡበት ጊዜ ጀምሮ በየወሩ መቆጠብ ያለባቸውን ገንዘብ እየቆጠቡ 10 እና 20 በመቶ የሚሆነውን ቆጥበው እንዳጠናቀቁ ቤቱን በዕጣ እንደሚያገኙና በአንድ ጊዜም መክፈል እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ " የመኖሪያ ቤት እጣው በሚወጣበት ጊዜ መንግስት በሰጠ