‹‹የሲዳማ ዘመን መለወጫ በዓል ከብሔረሰቡ ተወላጅ አልፎ የዓለም በዓል መሆኑ አስደስቶናል››
ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ወ/ሮ ምሕረት ገነነው፣ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ቱሪዝምና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሐዋሳ የቱሪስት መዳረሻና የመዝናኛ ከተማ እየሆነች የመጣች ሙደ ነች፡፡ ይህች ከተማ በአገር ውስጥ ቱሪስትም እየጎበኛት ይገኛል፡፡ በ1991 ዓ.ም. የነበረው ጠቅላላ የአገር ውስጥ ጎብኚ 19.136 ሲሆን፣ በ2008 ዓ.ም. እስከ ግንቦት ወር ደግሞ 150,000 ጎብኝተዋታል፡፡ ጠቅላላው የአገር ውስጥም የውጭ ጎብኚ ደግሞ በ1991 ዓ.ም. 21.668 የነበረ ሲሆን በዘንድሮው ዓመት እስከ ግንቦት 2008 ዓ.ም. 195,000 ሆኗል፡፡ ሌላው የሲዳማ የዘመን መለወጫ የጫምባላላ በዓል በዚህ ዓመት በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡ ይህም ለከተማዋ የቱሪስት መዳረሻነት አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ በዚህና በተያያዥ ጉዳዮች የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ቱሪዝምና የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ወ/ሮ ምሕረት ገነነውን ታምራት ጌታቸው አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር ፡- የጨንባላላ በዓል በቅርቡ በዩኔስኮ ተመዝግቧል፡፡ ይህ ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ወ/ሮ ምሕረት ፡- በመጀመሪያ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ የጫንባላላ በዓል የሲዳማ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን ዘንድሮም በአገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል፡፡ ከሌሎች በዓሎች የሚለይበት የራሱ የሆነ ነገሮች አሉት፡፡ ለምሳሌ ቀኑ የፍቅር የመቻቻል ቀን ነው፡፡ በዛን ቀን ከብት የማይመታበት ሕፃን ልጅን እንኳ የማይቆጣበት ሲሆን፣ ሰዎች ቢያስቀይሙህ እንኳን ምንም ዓይነት ዕርምጃ የማትወስድበት፣ የተጣላ የሚታረቅበት ነው፡፡ በበዓሉም ቀን ጉርሳሜ የሚባል ምግብ ነው የሚቀርበው፡፡ ይህ ከብሔሩ ተወላጅ በተጨማሪ ለመላው ዓለም አስተማሪነቱ ትልቅ ነው በዓሉ ጉድ