Posts

በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የፍጻሜ ጫዋታ ሀዋሳ ከነማ ድል ኣልቀናውም

Image
በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ጨዋታ ዛሬ 10 ሰአት ላይ መከላከያና ሀዋሳ ከተማ የፍጻሜ ጨዋታቸውን አድርገዋል። በጨዋታውም መከላከያ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል። መከላከያ በመጀመሪያው አጋማሽ ምንይሉህ ወንድሙ እንዲሁም በሁለተኛው ግማሽ ፍሬው ሰለሞን ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች ነው ማሸነፍ የቻለው። በዚህም ክለቡ በሶስት አመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ አሸናፊ ሲሆን፥ በአጠቃላይም ለ12ኛ ጊዜ የጥሎ ማለፉን ዋንጫ ማሸነፍ ችሏል። ይህም የጥሎ ማለፉን ዋንጫ ብዙ ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚ ክለብ ያደርገዋል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ 11 ጊዜ በማሸነፍ ይከተላል። መከላከያ የጨዋታው አሸናፊ በመሆኑ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ ይፎካከራል። በመጭው መስከረም 23 ቀን ከአምናው የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታውን ያደርጋል። ጨዋታውን ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኛነት መርተውታል። - See more at: http://www.fanabc.com/index.php/fbc-sport/item/10525-%E1%88%98%E1%8A%A8%E1%88%8B%E1%8A%A8%E1%8B%AB-%E1%8B%A82007-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8C%A5%E1%88%8E-%E1%88%9B%E1%88%88%E1%8D%8D-%E1%8A%A0%E1%88%B8%E1%8A%93%E1%8D%8A-%E1%88%86%E1%8A%90.html#sthash.PIkEK4LD.dpuf

ሂልተን ሀዋሳ ሪዞርትና ስፓን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

Image
( ኤፍ.ቢ.ሲ ) ሂልተን ሀዋሳ ሪዞርትና ስፓን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ። ስምምነቱን ሂልተን አለም አቀፍ እና ሰንሻይን ቢዝነስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ናቸው ዛሬ የተፈራረሙት። በሃዋሳ ሀይቅ ዳርጃ በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈው ሂልተን ሃዋሳ ሪዞርትና ስፓ፥ ግንባታው በዚህ አመት ነው የሚጀመረው። ለግንባታውም 42 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት እንደተያዘለት ነው የሂልተን አለም አቀፍ የአውሮፓና የአፍሪካ የልማት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ፓትሪክ ሲትዝዲቦን የተናገሩት። የሰንሻይን ቢዝነስ ሀላፊነት የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤትና ፕሬዚዳንት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በበኩላቸው፥ መንግስት በክልሉ የሚያካሂዳቸው ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ሰንሻይንን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችን በተለያዩ የገበያ ዘርፎች እንዲሳተፍ ያግዛል ብለዋል። ሂልተን ሃዋሳ ሪዞርትና ስፓ 169 ክፍሎች እና ቪላዎችን እንዲሁም 6 የስብሰባ አዳራሾችን የሚያካትት ሲሆን፥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020 እንግዶች የመቀበል ስራውን ይጀምራል።

PurpleLily in Africa (Sidama) – empowering girls and women

Image
Sidama, Southern Ethiopia For this work, I partnered with 2 Non-governmental Organisations (NGOs). The first was in the Southern Ethiopia region of Sidama, where I partnered with an NGO that focuses on teaching women literacy and numeracy. Although the Sidama region is rich in natural resources such as coffee, avocado, fruits and vegetables, poverty is rampant. The women that we worked with earn their living from the land. They sell their vegetables or coffee to support their families and earn an average of USD$10.00 / month. It appears that many are financially responsible for bringing up their children and I quickly identified the importance of financial literacy skills. Most of these women didn’t go to school as they needed to help their mothers while growing up and the expectation was that they would marry young, at about 14 years old. A majority of the workshop participants were 25 years old with 3 to 7 children. The aim of this project was to offer Life Skills and Financial

የሲዳማ ቡና የህብረት ስራ ኣምራቾች ምን ይላሉ?

Image
በሲዳማ ዞን ፌሮና አከባቢ ገበሬዎች ሁሌ-ገብ የህብረት ስራ ማህበር ሊቀመንበር  አቶ ደስታ መኩካ እንዳሉት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከመንግስትና ባለድርሻ አካላት በሚደረግላቸዉ ድጋፍ የማህበራቸው ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል፡፡ ማህበሩ በ1968 የተመሰረተው በ53 አባላትና 43ሺህ ብር ካፒታል እንደነበር አስታውቀው በአሁኑ ወቅትአራት ሺህ 735 አባላት፣ከ28 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ካፒታል ላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡[...] ማህበሩ ከአባልና ሌሎችም ቡና ተረክቦ በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸጥ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን በመጠቆም ባለፈዉ በጀት ዓመት ብቻ ለማዕከላዊ ገበያ ካቀረበዉ ደረቅና የታጠበ ቡና 12 ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ  ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡ [...]የሲዳማ ኤልቶ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ዮሀንስ ህብረት ስራ ማህበራት የአባሎቻቸውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚደረግላቸዉ እገዛ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ ዩኒየኑ በ1996 ዓ.ም በሰባት ማህበራትና 67 ሺህ መነሻ ካፒታል መመሰረቱን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ አባል ማህበራት 89፣ካፒታላቸው ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡ ዩኒየኑ የአከባቢዉን ስነ ምህዳር መሰረት ዘመናዊ የምርት ማሳደጊያ ግብዓት በማቅረብ ምርትና ምርታማነት የመጨመር ስራ ላይ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው የእንስሳት መኖ በማዘጋጀት ለአርሶ አደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡ የሲዳማ ቡና አብቃይ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ቁጥጥር ኮሚቴ ሀላፊ አቶ ማሞ ለማ ፌሮና አከባቢ ህብረት ስራ ማህበር የአባሎቹንና የአከባቢዉን ህብረተሰብ ችግር ከማስወገድ ባሻገር ለሌሎች ማህበራት የቁሳቁስ፣ የ

በጥሎ ማለፍ ጨዋታ መከላከያና ሀዋሳ ከነማ ለፍጻሜ አለፉ

Image
በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ መከላከያና ሀዋሳ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደረሱ። ወደ ፍጻሜው ለመግባት ትናንት በተደረገው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመከላከያ ወላይታ ዲቻ በሃዋሳ ከነማ ተሸንፈዋል። 9 ሰዓት ላይ በተደረገው የቅዱስ ጊዮርግስና መከላከያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ   በ4ኛው ደቂቃ አዳነ ግርማ  ባስቆጠራት ጎል መምራት ችሎ ነበር። ይሁን እንጂ መከላከያዎች በ38ኛው ደቂቃ በአዲሱ ፈራሚያቸው አዲሱ ተስፋዬ አቻ መሆን ችለዋል። በሁለተኛው አጋማሽ መከላከያ ከጨዋታ ብልጫ ጋር በ60ኛው ደቂቃ በኃይሉ ግርማ ባስቆጠራት ኳስ አሸናፊነቱን አረጋግጧል። የመከላከያው ተከላካይ ቴዎድሮስ በቀለ እጁ ላይ በደረሰበት ጉዳት  ከሜዳ ወጥቷል።   የመከላከያ አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ እንደተናገሩት "በመጀመርያው አጋማሽ በጊዮርጊስ ብልጫ ተወስዶብን ነበር፤ በሁለተኛው አጋማሽ ግን ተጠናክረን ገብተን አሸንፈን ወጥተናል" ብለዋል። የጊዮርጊስ አሰልጣኝ ማርቲን ኩፕማን በበኩላቸው "የዓመቱ መጀመርያ ውድድር ስለሆነ ሽንፈቱ ብዙም አያሳስበኝም፤ በቀጣይ በፕሪሚየር ሊጉና በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል።" በ11፡30  በደቡብ ደረቢ ሀዋሳ ከነማ ከወላይታ ዲቻ ያደረጉት ጨዋታ በሁለቱም ክለቦች ውጤታማ እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻሉም። በ79ኛው ደቂቃ በክረምቱ ዝውውር ደደቢትን ለቆ ሀዋሳን የተቀላቀለው በረከት ይሳቅ ሃዋሳ ወደ ፍጻሜ እንዲያልፍ አድርጎታል። ወላይታ ዲቻዎች ብዙ የጎል አጋጣሚዎች መፍጠር ቢችሉም ጎልና መረብ ማገናኝት አልቻሉም። በፍጻሜ ጨዋታ የሚገናኙት የመከላከያና የሀዋሳ ከነማ አሸናፊ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል። የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ በ1937 ዓ.ም የተጀ