ወገን ተወያይ!
እንደ ፈረንጆቹ ዘመን ኣቆጣጠር በ 1894 ኣም ማለትም ከመቶ ኣመታት በፊት ከኣዲስ ኣበባ ወደ ጅቡቲ ወደብ በተዘረጋው ባለ ኣንድ የባቡር መስመር ትታወቅ የነበረችው ኢትዮጵያ ኣሮጌውን የኣዲስ ኣበባ _ ጅቡቲ የባቡር መስመር በዘመናዊ መስመር ከመተከቷ ባሻገር በኣምስት ኣመት የትራንስፎርሜሽን ኣቅድ በሺዎች በሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች መላዋን የኣገርቱን ክልሎች ለማገናኘት ፕሮጄክት ነድፋ ከመንቀሳቀሷ ላይ ናት። ኣሁን ኣሁን እንደምሰማው ከሆነ በእቅድ ተይዘው የነበሩ ፕሮጄክቶ ወደ ስራ እየገቡ ያሉ ሲሆን፤ የኣዲስ ኣበባ ከተማ ቀላል የባቡር ፕሮጄክት የሙከራ ስራ ጅምሯል። ከዚህም ባሻገር ሰሞኑን ኣዋሽ _ ኮምቦልቻ _ ወልዲያ _ ሐራ ገበያ የምሽፍነው ባለ 375 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ስራን ጨምሮ በኣጠቃላይ በኣገሪቱ 1 ሺ 500 ኪሎ ሜትር የምሸፍን የባቡር መስመር ስራ በመሰራት ላይ ነው። ይህ የኣገሪቷን ክልሎች ያገናኛል የተባለለት የባቡር መስመር ዝርጋት ፕሮጄክት የትኛውንም የሲዳማን ከተማ እና ኣከባቢን ኣይጨምርም። ለኣብነት ያህል ከኣዲስ ኣበባ ተነስቶ ወደ ሞያሌ የምዘልቀው የባቡር መስመር ሆነ ተብሎ በኣርባምንጭ_ኮንሶ ኣድርጎ እንድሄድ ተደርጓል። ለመሆኑ የባቡር መስመር ዝርታ ፕሮጄክቱ የሲዳማን ኣከባቢዎች ያላከተተበት ምክንያት ምንድነው ? ወገን ተወያይ!