“ቡና ኃይለኛ የቆዳ ካንሰር ሊከላከል ይችላል”
ብሔራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚለው ከሆነ ቡና ሜላኖማን የመከላከል ኃይል አለው፡፡ 447 ሺህ 357 ሰዎችን ያሳተፈውና በአማካይ ለ10 ዓመታት የዘለቀው ይህ ጥናት ቡና በብዛት የሚጠጡ ሰዎች ለበሽታው ያላቸው ተጋላጭነት አነስተኛ መሆኑን አመላክቷል። በመሆኑም በቀን አራት ስኒ ቡና ወይም ከዚያ በላይ የሚጠጡ ሰዎች ለሜላኖማ የመጋለጥ ዕድላቸው ቡና ከማይጠጡ ሰዎች በ20 በመቶ ያነሰ መሆኑን ጠቁሟል። ይሁንና የጥናቱ ውጤት ያንኑ ናሙናው የተወሰደበትን ማህበረሰብ እንጂ ሌሎችን እንደማይወክልና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ ተመራማሪዎቹ አልሸሸጉም። ምንጭ፡- ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ