Posts

በጥሎ ማለፉ ውድድር ሲዳማ ቡና ወልዲያ ከነማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ረታ

Image
በጥሎ ማለፉ ሙገር ስሚንቶ እና አርባ ምንጭ ከነማ ድል ቀናቸው ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄዱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ሙገር ስሚንቶ እና አርባ ምንጭ ከነማ ድል ቀናቸው። በ8 ሰዓት ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከአርባ ምንጭ ከነማ ተገናኝተው 1 ለ 1 በመለያየታቸው፥ በተሰጡ መለያ ምቶች አርባ ምንጭ ከነማ 5ለ 4 አሸንፏል። ሲዳማ ቡና በበኩሉ ወልዲያ ከነማን 3 ለ0 በሆነ ውጤት ረቷል። ኢትዮጵያ ቡና ከመብራት ሃይል ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የፕሪሚየር ሊግ ቀሪ ጨዋታውን ሲያካሂድ ፥ ወላይታ ዲቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሀዋሳ ከነማ ከደደቢት አንድዚሁ ቀሪ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። በሌላ በኩል 23ተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይቀጥላል። የሊጉ መሪ ቼልሲ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ነገ  አርሰናል በኤሜሬትስ አስቶን ቪላን 10 ሰዓት ከ30 ላይ ያስተናግዳል።

መድረክ በሃድያ ዞን ሁለት ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ

Image
  የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ በሃድያ ዞን ሁለት ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ። ፓርቲው ትናንት እና ዛሬ ሰለማዊ ሰልፉን ያካሄደው በሆሳእና ከተማ እና በምስራቅ ባዳዋቾ ሾኔ ከተሞች ነው። የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በሁለቱ ከተሞች በተካሄደው ሰልፍ የፓርቲው አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ተገኝተዋል። ሊቀመንበሩ ሰልፉ በፀጥታ ኃይሎች ትብብር ያለምንም ችግር መከናወኑን ተናግረዋል። Read more:  ኤፍ.ቢ.ሲ

የምርት ዘመኑን ቡና ወደ ውጭ መላከ እንዳልቻሉ ቡና ላኪዎች ገለጹ

Image
በምርት ዘመኑ የተገኘው አዲስ ቡና ወደ ውጭ እየተላከ እንዳልሆነ ቡና ላኪዎች ገለጹ፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ሁለት የቡና ላኪዎች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፉ ስድስት ወራት የተሸጠው ቡና ከአገር የወጣው በክረምት ወራት ነው፡፡ የሽያጭ ስምምነቱ ባለፈው ዓመት ቢደረግም በዚያው ዓመት መውጣት ባለመቻሉ፣ በዚህ ጊዜ መውጣት ያለበት አዲስ ቡና ግን መውጣት አልቻለም፡፡ ወቅቱ የታጠበ ቡና ወጥቶ አልቆ የደረቀ ቡና የሚላክበት ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች አፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆኑን ነጋዴዎች አመልክተዋል፡፡ ሽያጩ ሳይፈጸም የቀረው የተቀመጠው የቡና ዋጋ ሊወርድ ይችላል በሚል የቡና ገዥዎች ግብይት ለመፈጸም ባለመፈለጋቸው መሆኑን ሪፖርተር ያነጋገራቸው ነጋዴዎች ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አገር ውስጥ የሚገኙ ቡና አምራቾች የብራዚል ቡና በድርቅ በመመታቱ የዓለም የቡና ዋጋ ከፍ ሊል ስለሚችል፣ የሚያመርቱትን ቡና ለገበያ እያቀረቡ አይደለም በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የንግድ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አዲሱ ቡና በሚፈለገው ደረጃ መውጣት ያልቻለው ቡና ላኪዎቹ በገለጿቸው ሁለት ምክንያቶች እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡  የመጀመርያ የዓለም ገበያ ከፍተኛ የዋጋ መዋዠቅ ውስጥ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ትላልቅ ገዥዎች ግዥ ከመፈጸም ተቆጥበዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የብራዚል ቡና በድርቅ በመመታቱና ብራዚል ምን ያህል ቡና ለገበያ እንደምታቀርብ በውል ባለመታወቁ፣ ገዥውም አቅራቢውም ወደ ቡና ግብይት ለመግባት ቁጥብ በመሆናቸው ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ በሌላ በኩል ንግድ ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ ከዕቅዱ በላይ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ውጤቱ የተገኘው የከረመ ቡ

በሐዋሳ የሚቋቋመው ኢንዱስትሪ ዞን የውጭ ኩባንያዎችን ትኩረት ስቧል

የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ በሆነችው ሐዋሳ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ኢንዱስትሪ ዞን የበርካታ ኩባንያዎችን ትኩረት በመሳቡ፣ በዚህ የኢንዱስትሪ ዞን ኢንቨስት ለማድረግ የቻይና፣ የህንድና የሲሪላንካ ኩባንያዎች ቦታ እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ዋና አማካሪና ልዩ ረዳት አቶ አኒሳ መልኮ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የእነዚህ ኩባንያዎች ጥያቄ እየታየ ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥት በቅርብ አራት ከተሞችን የኢንዱስትሪ ቀጣናዎች አድርጎ መርጧል፡፡ እነዚህ ከተሞች አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ኮምቦልቻና ሐዋሳ ናቸው፡፡  በሐዋሳ አንድ ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ ሁሉም ነገር የተሟላለት የኢንዱስትሪ ዞን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ከአዲስ አበባ በ275 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሐዋሳ ከተማ በቅርቡ የአውሮፕላን ማረፊያ እንዲገነባ በመወሰኑ፣ በርካታ ኢንቨስተሮች ትኩረት እንዲያደርጉ ምክንያት መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡  አቶ አኒሳ እንዳሉት ከአውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እስከ ሐዋሳ ከተማ ድረስ፣ እንዲሁም ከሐዋሳ አልፎ እስከ ኬንያ ድረስ የባቡር መስመር ይዘረጋል፡፡ የባቡር መስመር የሚዘረጋ ከሆነ በርካታ ኩባንያዎች በሐዋሳ ኢንቨስት ለማድረግ ከወዲሁ ፍላጎታቸውን እንደገለጹም ታውቋል፡፡ በሐዋሳ የሚገነባው ኢንዱስትሪ ዞን በተለይ አግሮ ፕሮሰሲንግ ላይ እንደሚያተኩር አቶ አኒሳ ገልጸው፣ አካባቢው የግብርና ምርቶች በሰፊው የሚገኙበት በመሆኑ የኢንዱስትሪ ዞኑ ጠቀሜታ የጎላ ነው ብለዋል፡፡ በሐዋሳ ከተማ ቀደም ብሎ ለኢንዱስትሪ የተከለለው ቦታ ላይ ቢጂአይ ኢትዮጵያ፣ ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ፣ ጋትስ አግሮ ኢንዱስትሪና የመሳሰሉት ኩባንያዎች ምግብና መጠጦችን በማምረት ላይ

ጊዜ ያልገደበው የሰላማዊ ሠልፍ ንትርክ

Image
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወጣ ገባ ከሚሉባቸው የመንግሥት ቢሮዎች መካከል የአዲስ አበባ አስተዳደር የፈቃድና የማስታወቂያ ክፍል ዋነኛው ነው፡፡ ዓመቱ ጠቅላላ ምርጫ የሚደረግበት እንደመሆኑ ፓርቲዎቹ ቢሮውን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይበልጥ አዘውትረው እንደሚጎበኙት ይጠበቃል፡፡ በከንቲባው ጽሕፈት ቤት ሥር የሚገኘው ክፍል ዋነኛ ዓላማ ስለሰላማዊ ሠልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 3/1983 በአዲስ አበባ ማስፈጸም ነው፡፡ የክፍሉ መጠሪያ በራሱ ባለፉት 24 ዓመታት ሰላማዊ ሠልፍንና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባን አስመልክቶ ገዥው ፓርቲና መንግሥት በአንድ ወገን፣ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ በሌላ ወገን የሚያደርጉትን ክርክር የሚያሳይ ነው፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ ፈቃድ ሳይሆን ማስታወቅን ብቻ እንደሚያስቀምጥ ይጠቁማሉ፡፡ መንግሥት በበኩሉ በግልጽ ፈቃድ ያስፈልጋል ብሎ አይከራከር እንጂ፣ በተለያዩ መግለጫዎቹ ‘ያለፈቃድ የተደረጉ ሰላማዊ ሠልፎች’ ሲል ይጠቅሳል፡፡ ይበልጥ አተኩሮ የሚከራከረው ሰላማዊ ሠልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የማድረግ መብት እንደሌሎች መብቶች ሁሉ ገደብ የሚደረግበት መሆኑን ነው፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባለፈው እሑድ ለማድረግ አስቦት የነበረውና በመንግሥት እንዳይካሄድ የተከለከለው ሰላማዊ ሠልፍ፣ እንዲሁም ጥር 24 ቀን 2007 ዓ.ም. አደርገዋለሁ ያለው ሰላማዊ ሠልፍ በፓርቲውና በመንግሥት መካከል የፈጠረው አለመግባባት የዚህ ችግር አንድ ማሳያ ነው፡፡ ባለፈው ሐሙስ ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ አመራር እንዳልሆነ ውሳኔ የሰጠበት ቡድን ውስጥ የተካተቱት የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አሥራት አብርሃም ለሪፖርተር