ሲዳማ ቡና ከወልዲያ ከነማ 10 ሰዓት ላይ በኣበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታል
ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። በ8 ሰዓት ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከ አርባ ምንጭ ከነማ ሲገናኙ፥ ሲዳማ ቡና ከወልዲያ ከነማ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። ኢትዮጵያ ቡና ከመብራት ሃይል ከነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የፕሪሚየር ሊግ ቀሪ ጨዋታውን ሲያካሂድ ፥ ወላይታ ዲቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሀዋሳ ከነማ ከደደቢት አንድዚሁ ቀሪ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። በሌላ በኩል 23ተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይቀጥላል። የሊጉ መሪ ቼልሲ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ሊቨርፑል ከዌስት ሃም፣ ማንችስተር ዩናይትድ ከሌችስተር ሲቲ በተመሳሳይ 12 ሰዓት ነገ ይገናኛሉ። ከነገ አርሰናል በኤሜሬትስ አስቶን ቪላን 10 ሰዓት ከ30 ላይ ያስተናግዳል።