Posts

የባለፈው ዓመት የሊጉ ችግሮች አይደገሙም- ፌደሬሽኑ

Image
የባለፈው ዓመት የሊጉ ችግሮች አይደገሙም- ፌደሬሽኑ ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን  ውበት ያሳጡት ችግሮች እንዳይደገሙ  ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡ የ2007 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ጥቅምት 15 መጀመራቸውን ተከትሎ ነው ከወድሁ ፌደሬሽኑ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን እየተናገረ ያለው፡፡ ፌደሬሽኑ በሊጉ ጨዋታዎች ወቅት የሚከሰቱ የዳኝነት ችግሮች፣ የጨዋታዎች ረዘም ላለ ጊዜ መቋረጥና የክልል ስታዲዮሞች ደረጃ ችግርን ለመፍታት ሰፊ ስራ መስራቱን ገልጿል፡፡ የፌደሬሽኑ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ በተለይ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት  የዳኞችንና የኮሚሽነሮችን አቅም ለማሻሻል ሰፊ የሙያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ዳኞችና ኮሚሽነሮች የባለፈውን ዓመት አፈጻጽም በመገምገምም ክፍትቶቻቸውን የሚሞሉበትን ዝግጅት ማድረጋቸውንም ገልፀዋል፡፡ ፌደሬሽኑ የዳኞችን  የስራ ተነሳሽነት ለማሳደግም  ክፍያቸውን አሻሽሏል፡፡ የ2007 የሊጉ የጨዋታ መርሃ ግብር ከዚህ በፊት እንደሚከሰተው በብሔራዊ ቡድን ዝግጅትና በሌሎች ምክንያቶች በመቋረጥ ውበቱን እንዳያጣ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ጨዋታዎችን መነሻ በማድረግ መዘጋጀቱን አቶ ወንድምኩን ገልጸዋል፡፡ በክልሎች የሚገኙ ክለቦች ደረጃውን የጠበቀ ስታዲዮም  እንዲያዘጋጁ  በማሳሰቡ፣ሁሉም የክልል ክለቦች ስታዲዮሞቻቸውን ለማሻሻል እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ እንዳቶ ምንድምኩን ገለፃ ፌደሬሽኑ የ2006 ዓ/ም አፈፃፅምን በመገምገም የነበሩበትን ክፍተቶች ለማሻሻል በመስራቱ የባለፈው ዓመት ችግሮች በዚህ ዓመት እንዳይደገሙ በጥንቃቄ ለመምራት ተዘጋጅቷል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2007 የጨዋታ መርሃ ግብር በመጪው ቅዳ

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጡት ካንስር ህክምና መሰጠት ሊጀመር መሆኑ ተሰማ

Image
የጡት ካንሰር ህክምና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት ሊጀመር ነው የጡት ካንሰር ህክምናን በ5 ዩኒቨርሲቲዎች ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በጡት ካንሰር ዙሪያ የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገለጹ። ይህን ህክምና ለመጀመር የሚያስችል የመሳሪያና የባለሞያ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። ህክምናው የሚሰጠው በጅማ፣ ሃዋሳ፣ መቀሌ፣ ጎንደር እና ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ነው። ዓለም አቀፉ የጡት ካንሰር ቀን ጥቅምት 16 በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበርም አዲስ አበባን ጭምሮ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ እና ትግራይ ክልሎች የእግር ጉዞ በማካሄድ ነው። የዚህ በአል አላማ ህብረተሰቡ የጡት ካንሰርን አስቀድሞ የመከላከል፣ የምርመራና የህክምና አማራጮችን ግንዛቤ ማሳደግ ነው። የጡት ካንሰር ህመምን ሙሉ ለሙሉ አስቀድሞ መከላከል ባይቻልም ህመሙ እንደተከሰት ተገቢው ህክምና ከተሰጠ የመዳን እድሉ  ሰፊ ነው። የዕድሜ መግፋት፣ ከመጠን ያለፍ ክብደት፣ አልኮል መጠጣት፣ ጡት አለመጥባትና መሰል ምክንያቶች ለጡት ካንሰር እንደሚያጋልጥ የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ። ምንጭ፦ EBC

UGANDA, KENYA FALL AS TANZANIA, ETHIOPIA RISE IN LATEST FIFA RANKINGS

Image
Uganda has fallen five places according to the latest Coca Cola FIFA rankings released on Thursday October 24. Uganda;  79th last month  is now ranked 84th in the world and 21st in Africa with 389 points. The fall is attributed to the back-to-back losses to Togo in the  Africa Nations Cup qualifiers  and Uganda Cubs' (U-17)  failure to go past Zambia in the Africa Youth Championship qualifiers . Neighbours Kenya have also fallen five places from 111st to 116; a fall attributed to losses against Morocco and Egypt in international friendlies. However, there was rise for Tanzania and Ethiopia who are now ranked 110 and 111 in the world respectively. Ethiopia were the biggest movers rising 21 places from 132 last month. Uganda’s opponents in  group E of the AFCON qualifiers  Ghana dropped two places to 35th (5), Togo rose 72 places to 52nd (10) whilst Guinea dropped 7 places to 55 (11). World champions Germany maintain top spot followed by Argentina, Colombia, Bel

የቡና ግብይት ስርዓቱ ግልጽ አስተማማኝና ቀልጣፋ ነው ኣሉ

Image
በሃዋሳ እና በሌሎች ከተሞች የተገነቡ የቡና ቅምሻና ጨረታ ማዕከላት የቡና ግብይት ስርዓቱ ላይ ይታይ የነበረውን ችግር በማስቀረት ግብይቱ ግልጽ አስተማማኝና ቀልጣፋ እንዲሆን ኣስችለዋል መባሉ ተሰምቷል፤ ከክልሉ በተያዘው ዓመት ከ134 ሺህ ቶን የሚበልጥ የታጠበና ደረቅ ቡና ለገበያ ይቀርባል እየተባለ ነው። ወሬው የኢዜኣ ነው፦ ከደቡብ ክልል ለገበያ የሚቀርበውን የቡና መጠን በጥራት በመጨመር የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ አስታወቀ፡፡ በቢሮው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከክልሉ በተያዘው ዓመት ከ134 ሺህ ቶን የሚበልጥ የታጠበና ደረቅ ቡና ለገበያ ይቀርባል። ክልሉ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ማምረት የሚችል ቢሆንም ህገወጥ የቡና ግብይትና ዝውውር በገበያው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ለውጪ ምንዛሪ መጠን ማነስ ምክንያት ሆኖ መቆየቱን ጠቁመዋል። ህገወጥ የቡና ዝውውርና ግብይትን ለማስቀረትና በግብይት ስርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ለውጪ ገበያ የሚቀርበውን ቡና ጥራት ለማስጠበቅ የቡና ግብይት ደንብና መመሪያ ተዘጋጅቶ ግባራዊ መሆኑን ገልጸዋል። የቡና ግብይት ስርዓቱ እሴት በማይጨምሩ ደላሎችና ህገወጥ የቡና አዘዋዋሪዎች እጅ የወደቀ በመሆኑ አምራቹ ለምርቱ ተመጣጣኝ ዋጋ እንደማያገኝ ገልጸው በቡናው ላይ የጥራት መጓደል ችግር የሚፈጠር በመሆኑ የሚፈለገውን ያህል ገቢ ማግኘት እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡ የቡና ግብይት ስርዓቱ ግልጽና የአምራቹን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲያስችል የገበያ መሰረተ ልማት የማስፋፋት ስራ መከናወኑን ገልጸው ባለፉት አራት ዓመታት አንድ ሺህ 618 የመጀመሪያ

የጋራ ምክር ቤቱ በኣገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትና ችግሮችን ለመፍታት እድል ፈጥሯል-ፓርቲዎች

Image
የጋራ ምክር ቤቱ በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከገዥው ፓርቲ ጋር በሰከነ መንፈስ ለመወያየትና ችግሮችን ለመፍታት እድል ፈጥሯል-ፓርቲዎች አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከገዥው ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራትና በመካከላቸው የሚከሰቱ ቅሬታዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እድል መፍጠሩን አንዳንድ አባል ፓርቲዎች ገለፁ። በጋራ ምክር ቤቱ ያልተካተቱ ፓርቲዎችም በአገሪቱ የተጀመረው የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዲጠናከር የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ካነጋገራቸው የጋራ ምክር ቤቱ አባል ፓርቲዎች መካከል የአዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው ጌታቸው ከገዥው ፓርቲ ጋር የሚደረገው ውይይት በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በፓርቲዎች መካከል መግባባትን ከመፍጠር ባለፈ የመጪውን ትውልድ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ለማዳበር የጎላ ሚና አለው ብለዋል። ፓርቲዎች በአንድ አገራዊ ጉዳይ ላይ የሰከነ ውይይት ማድረጋቸው በመካከላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በቀላሉ እልባት ከመስጠቱም ባሻገር ለመደብለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓቱ መጠናከር የማይተካ ድርሻ አለው። በምክር ቤቱ ውስጥም የሁሉም አባል ፖለቲካ ፓርቲዎች አገራዊና ድርጅታዊ አጀንዳዎች እንደሚስተናገዱ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ጠንካራ ክርክሮችን በማድረግ ለህዝብ የሚቀርቡ አማራጭ ሃሳቦች ጎልተው እንዲወጡ ይደረጋል ብለዋል። አቶ አስፋው እንዳሉት እስከታችኛው የስልጣን እርከን ድረስ የምክር ቤቱ አባላት ለሚያነሷቸው ችግሮች ከሁሉም ፓርቲዎች የተውጣጡ አጣሪ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ዘላቂ እልባት እንዲኖር እድል መስጠቱንም ጠቅሰዋል። በጋራ ምክር ቤቱ የተቋቋመው ኮሚቴ በተከሰቱ ችግሮች ዙሪያ የሚያቀርበው ሪፖርት በመነሳት ገዥ