የቡና ግብይት ስርዓቱ ግልጽ አስተማማኝና ቀልጣፋ ነው ኣሉ
በሃዋሳ እና በሌሎች ከተሞች የተገነቡ የቡና ቅምሻና ጨረታ ማዕከላት የቡና ግብይት ስርዓቱ ላይ ይታይ የነበረውን ችግር በማስቀረት ግብይቱ ግልጽ አስተማማኝና ቀልጣፋ እንዲሆን ኣስችለዋል መባሉ ተሰምቷል፤ ከክልሉ በተያዘው ዓመት ከ134 ሺህ ቶን የሚበልጥ የታጠበና ደረቅ ቡና ለገበያ ይቀርባል እየተባለ ነው። ወሬው የኢዜኣ ነው፦ ከደቡብ ክልል ለገበያ የሚቀርበውን የቡና መጠን በጥራት በመጨመር የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ አስታወቀ፡፡ በቢሮው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከክልሉ በተያዘው ዓመት ከ134 ሺህ ቶን የሚበልጥ የታጠበና ደረቅ ቡና ለገበያ ይቀርባል። ክልሉ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ማምረት የሚችል ቢሆንም ህገወጥ የቡና ግብይትና ዝውውር በገበያው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ለውጪ ምንዛሪ መጠን ማነስ ምክንያት ሆኖ መቆየቱን ጠቁመዋል። ህገወጥ የቡና ዝውውርና ግብይትን ለማስቀረትና በግብይት ስርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ለውጪ ገበያ የሚቀርበውን ቡና ጥራት ለማስጠበቅ የቡና ግብይት ደንብና መመሪያ ተዘጋጅቶ ግባራዊ መሆኑን ገልጸዋል። የቡና ግብይት ስርዓቱ እሴት በማይጨምሩ ደላሎችና ህገወጥ የቡና አዘዋዋሪዎች እጅ የወደቀ በመሆኑ አምራቹ ለምርቱ ተመጣጣኝ ዋጋ እንደማያገኝ ገልጸው በቡናው ላይ የጥራት መጓደል ችግር የሚፈጠር በመሆኑ የሚፈለገውን ያህል ገቢ ማግኘት እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡ የቡና ግብይት ስርዓቱ ግልጽና የአምራቹን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲያስችል የገበያ መሰረተ ልማት የማስፋፋት ስራ መከናወኑን ገልጸው ባለፉት አራት ዓመታት አንድ ሺህ 618 የመጀመሪያ