የተሻሻለው የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት መመርያ ተቃውሞ ገጠመው
ሰሞኑን ተሻሽሎ በቀረበው የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት መመርያ ላይ ከአስተዳደሩ ከፍተኛ ባለሥልጣን ጋር የተወያዩት ቤት ፈላጊዎች ተቃውሞአቸውን ገለጹ፡፡ የማኅበራቱ ተወካዮች ቅሬታቸውን የገለጹት፣ ከአንድ ዓመት መጉላላት በኋላ ተሻሽሎ የቀረበው መመርያ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትልና የተሻረው መመርያ የሰጠውን ጥቅም የሚያስቀር ነው በሚል ነው፡፡ ጥቅምት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይሌ፣ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸውና የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሺሰማ ገብረ ሥላሴ ከማኅበራቱ ተወካዮች ጋር በከተማው ምክር ቤት አዳራሽ ለግማሽ ቀን ውይይት አድርገዋል፡፡ በተካሄደው ድንገተኛና ያልተጠበቀ ስብሰባ የማኅበራቱ ተወካዮች ከባለሥልጣናቱ ጋር ባካሄዱት ስብሰባ ስምምነት ላይ መድረስ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ የማኅበራቱ ተወካዮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አዲሱ መመርያ ቀደም ሲል ተስፋ ጥለው የተደራጁበትን የሚሸረሽር ነው፡፡ አዲሱ መመርያ ቀደም ሲል ወጥቶ ከነበረው መመርያ ጋር በመሠረታዊ ሐሳቦች ላይ ልዩነት አምጥቷል፡፡ ቀደም ሲል የነበረው መመርያ ለፕሮግራሙ የሚቀርበው መሬት ከሊዝ ነፃ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ነገር ግን በመልሶ ማልማት ቦታዎች ነዋሪዎች የሚነሱ ከሆነ ማኅበራቱ ካሳ እንሚከፍሉ ተገልጾ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ አሠራር ቀርቶ መሬት በሊዝ እንደሚሰጥ በመጥቀሱ አዲሱ መመርያ የሐሳብ ለውጥ አምጥቷል፡፡ ሌላኛው ለውጥ መኖሪያ ቤቶቹ የሚገነቡት በሁለት አግባብ ነው፡፡ የመጀመሪያው በማስፋፊያ ቦታዎች ‹‹ታውን ሐውስ›› የተሰኘ የመኖሪያ ቤት ዓይነት እንደሚገነባ፣ በመልሶ ማልማት ቦታዎች ደግሞ ባለአምስት ፎቅ አፓርታማ እንደሚገነባ ነበር፡፡ ነ