ፓርቲዎች በምርጫ ማስፈጸሚያ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ውይይት ጀመሩ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በ2007 ዓ.ም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ ረቂቅ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ። ለ5ኛ ጊዜ በመጪው ግንቦት የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ ረቂቅ ላይ ከ23 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ነው ውይይቱ የተካሄደው። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንዳሉት ውይይቱ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርዱ ባዘጋጀው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲንቀሳቀሱ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል። በምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ የምክክር መድረክ ላይ ከተገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ ረቂቁ ሊያሰራ የሚችል ተስማሚ የጊዜ ሰሌዳ መሆኑን ተናግረዋል። የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ አየለ ጫሚሶ በበኩላቸው ረቂቅ የምርጫ ድርጊት መርሃ ግብሩ መካተት ያለባቸው ጉዳዮች የያዘ በመሆኑ ፓርቲያቸው የተወሰኑ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ አስታውቀዋል። የኢህአዴግ ተወካይ የሆኑት አቶ ደስታ ተስፋው በበኩላቸው "የ2007 ዓ.ም የምርጫ አፈጻጸም የድርጊት መርሃ ግብር ረቂቅ የሚያሰራ እና በተቀመጠው መሰረት ወደ ስራ የሚያስገባ ረቂቅ ሰነድ ነው" ብለዋል። የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አስፋው ጌታቸው ምርጫ ቦርድ እንደዚህ አይነት የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱ ለአገሪቱ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸው የቀረበውን ረቂቅ እን ደሚቀበሉት ተናግረዋል። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በረቂቁ ላይ በሰጡት አስተያየት የመራጮች ምዝገባ፤ የፓርቲዎች