የሲዳማ ቡና በሲዳሞ ቡናነት መጠራቱን ዛሬም ቀጥሏል
ከመቶ ኣመታት በላይ በኢትዮጵያ የነበረው የነፍጠኛው ስርዓት የህዝቦችን እና የኣከባቢዎቻቸውን መጠሪያ ሰሞች በመሰለኝ እና በደሳሌኝ በመቀየር የሚታወቅ ሲሆን፤ በዘፈቀደ የተለወጡት እነዚሁ መጠሪያ ስሞች በተለይ በዛሬው የህዝቦች ማንነት ላይ ተጽዕኖ በመፈጠር ላይ ናቸው። ሲዳማ የመጠረያ የስያሜ ሞድፊኬሽን ከተደረገባቸው ህዝቦች መካከል ኣንዱ ነው። በሲዳማ የነበረው የነፍጠኛው ስርዓት የሲዳማ ኣከባቢዎች መጠረያ ሰሞችን ላይ ብቻ ሳይሆን በህዝቡ መጠረያ ስም ላይም ለውጦችን እስከማድረግ ደርሷል። ለኣብነት ያህል በሲዳማ ብሔር መጠረያ ስም ላይ ከተደረገው ለውጥ በተጨማሪ በሲዳማ ከተሞች እና ወረዳዎች ላይ መሰል ሞድፊኬሽን ተደርጓባቸዋል፦ሐዋሳን ወደ ኣዋሳ፤ ሐርቤጎናን ወደ ኣርቤጎና፤ ሐሮሬሳን ወደ ኣሮሬሳ፤ ወዘተ ይገኙበታል። እነዚህ በዘፈቀደ የተደረጉት ለውጧች በብሔሩ ማንነት ላይ ኣሉታዊ ተጽዕኖ ከመፍጠራቸው በላይ ብሔሩ እና ክልሉ በሁለት ስያሜ እንድጠራ የግድ ብሎታል። ኣንድን ብሔር ወይም ህዝብ ያለኣግባብ በሁለት ስም መጥራት ባለው ኣሉታዎ የፖለቲካ እና ማህበራዊ እንድምታ ላይ በሌላ ጊዜ የምመለስበት ሲሆን፤ ለዛሬ ግን ይህ በነፍጠኛው የተተዎው የመጠረያ ስም ለውጥ ኣሻራ በሲዳማ ምርቶች ላይ መንጸባረቅ መቀጠሉን በተመለከተ ትንሽ ማለት እወዳለሁ። እንደምታወቀው በኣገሪቱ የመንግስት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ በርካታ ኣከባቢዎች እና ህዝቦች በቀድሞው መጠረያ ሰሞቻቸው መጠራት ጀምረዋል። ሲዳማም ብሆን የዚህ እድል ተጠቃሚ መሆኑ እውን ነው። የመጠሪያ ሰሞችን ወደ ቀድሞ ስያሜዎቻቸው የመመለሱ ጉዳይ በብሔር እና በኣከባቢዎች ስያሜ ላይ ብቻ ሳይወሰን በብሔሩ እና በኣከባቢዎች ምርቶች ላይም ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል። ለም