Posts

የጣሊያን ህጻናት በሃዋሳ ከተማ እና ኣከባቢያዋ የሚገኙትን ከዝቅተኛ ቤተሰብ የመጡ ተማሪዎችን በትምህርት ቁሳቁስ ለመረዳ የገቢ ማሰባሰቢያ የጎዳና ላይ ሩጫ

Image
በሃዋሳ ከተማ እና ኣከባቢያዋ የሚገኙትን ከ18 ሺ በላይ ከዝቅተኛ ቤተሰብ የመጡ ተማሪዎችን በትምህርት ቁሳቁስ ለመረዳ የገቢ ማሰባሰቢያ የጎዳና ላይ ሩጫ በሰሜናዊቷ የጣልያን ግዛት ሶውዝ ትይሮል ቦልዞን ከተማ ተካሄደ። በጎዳና ሩጫው ላይ ከ3 ሺ በላይ ህጻናት ተሳታፊ ሲሆኑ ወደ 80 ሺ ዩሮ ከሰፖንስሮች መሰብሰቡን የሩጫው ኣዘጋጆች ተናግረዋል።  ዜናው የሰቶል ነው ዝርዝር ዜናውን ከታች ያንቡ፦ Once Bolzano-Tokyo round trip Around 3,000 students, scouts, confirmands and young people of various parishes who attended the fifth edition of the "miracle run" in 15 different places in South Tyrol.  The distance walked: Bolzano-Tokyo back and forth, say, 25,000 km, to help their peers in Ethiopia. Bolzano, Laives, Neumarkt, Longostagno Gummer, Mölten, Tarsch Meransen, Dobbiaco, Kien, Neumarkt, Sarn Valley and Elections: There are many villages and towns in South Tyrol, who participated in organized by the youngCaritas solidarity initiative.   Around 3,000 students, confirmands and scouts have personal sponsors found that have per kilometer run donated a previously agreed amount. "Many boys and girls

የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ማስተካከያ ሊደረግ ነው

Image
መንግስት የዋጋ ንረትን በማይቀሰቅስ ሁኔታ የተጠና የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ማስተካከያ ከሀምሌ ወር 2006 ዓ.ም ተግባራዊ እንደሚያደረግ ተሰማ።  ለ8ኛ ጊዜ እየተከበረ ባለው የሲቪል ሰርቪስ ቀን ላይ የመንግስት ሰራተኞችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍም በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ላይ 20 በመቶ ቅድሚያ የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸቱንና የትራንስፖርት ችግርንም በተመሰሳይ ለመቅረፍም የሰርቪስ አገልግሎት በየመስሪያ ቤቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መደረጉን ተነግሯል። በሃገሪቱ የእድገት ጉዞ ውስጥ የራሱን ወሳኝ ድርሻ በመወጣት ላይ ለሚገኘው የመንግስት ሰራተኛ  የመኖርያና የትራንስፖርት ችግርን ለማቃለል የሚያስችሉ መፍትሄዎች መንግስት እንደሚያቀርብለት ተገልጿል። በተያያዘ በሁሉም ደረጃዎች ባሉ የመንግስት መዋቅሮች ልማታዊ መልካም አስተዳደርና የላቀ የስራ አፈፃፀም በማረጋገጥ የተጀመሩትን የለውጥና የሪፎርም ስራዎች ከዳር ለማድረስ በቁርጠኝነት መሰራት ይገባል ተብሏል።  በዚህ የሲቪል ሰርቪስ ቀን በዓል ላይ የኣገሪቱ ከፍተኛ ኣመራሮች መገኘታቸውን ወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ዘግቧል።

ኣዲሱ የሃዋሳ ከተማ መዝሙር

Image
በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ባህል ቱሪዝምና መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ የተዘጋጀ የሃዋሳ ከተማ መዝሙር

ኣዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም በሲዳሚኛ ቋንቋ ኣየር ላይ ዋለ!

Image
Sidama Speak

የሲዳማ ቤተሰብ ወደ ኣውስትራሊያ ያደረገው የስዴት ጉዞ

Image
Making a new life in Ulladulla By  DAYLE LATHAM June 16, 2014, 6 a.m. IN 2002 a young woman left Ethiopia, a country plagued by famine and unrest between the government and local tribes, in search of a better life. She found herself in a refugee camp in Kenya, where she spent the next seven years before being granted a refugee visa to Australia. Terefech Yako met her husband, Berhanu Geda, also a refugee, in the camp in Kenya. They both came from the same tribe in Ethiopia, although they hadn’t known one another. “We were married in Kenya in the refugee camp,” Terefech said. The couple had a son, Menase, now nine, while they were living there. He was four when the family came to Australia to live in Ulladulla. “It’s nice, it’s good. I can’t compare it with African life,” Terefech said. “It was a very bad area in Kenya in the refugee camp. Every day was 41, 42 [degrees]. We lived only in a tent. “My life in Ethiopia wasn’t bad, before the government make pr

በሸቀጦች ላይ የዋጋ ንረት እየታየ ነው

Image
በኪሎ 35 ብር የነበረው በርበሬ 55 ብር እየተሸጠ ነው  በ115 ብር እንዲሸጥ የተተመነው ባለ 5 ሊትሩ ዘይት 150 ብር ገብቷል በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች የስኳር፣ የዘይትና የዳቦ እጥረት ተከስቷል የፍላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠን የፈጠረው ነው ተብሏል       ሰሞኑን በአንዳንድ መሰረታዊ ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እየታየ ሲሆን ነጋዴዎችና  የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም ውጤት ነው ብለዋል፡፡  በተለይ የበርበሬ፣ የስንዴ ዱቄትና የምስር ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን የስኳር፣ ዘይትና ዳቦ እጥረትም መከሰቱን ሪፖርተሮቻችን በአዲስ አበባ የተለያዩ የገበያ ስፍራዎች ተዘዋውረው ባደረጉት ቅኝት አረጋግጠዋል፡፡ ሸማቾች የዋጋ ጭማሪው እንዳማረራቸው ሲገልፁ፣ ነጋዴዎች፤ የሸቀጦች አቅርቦት ከፍላጎት ጋር  አልተጣጣመም ብለዋል፡፡  ከሳምንት በፊት በኪሎ 35 ብር ይሸጥ የነበረው ዛላ በርበሬ፣ እስከ 20 ብር ጭማሪ አሳይቶ ኪሎው በ55 ብር እየተሸጠ ሲሆን በንግድ ሚኒስቴር የመሸጫ ዋጋ ተመን ከወጣላቸው ሸቀጦች አንዱ የሆነው የስንዴ ዱቄት ከ12 ብር ወደ 14 ብር ከፍ ብሏል፡፡ የምስር ዋጋም በኪሎ 21 ብር የነበረው 25 ብር እየተሸጠ መሆኑን ከተለያዩ የገበያ ስፍራዎች የተሰበሰቡ የዋጋ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡  በሌላ በኩል ስኳር፣ ዘይትና ዳቦ የመሳሰሉትን እንደልብ ማግኘት እንደተሳናቸው ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በሳሪስ አካባቢ በአንድ ዳቦ ቤት ዳቦ ለመግዛት ተሰልፈው ያገኘናቸው አቶ ወንድይፍራው ደምሴ፤ ለቤተሰቦቻቸው በየእለቱ ዳቦ እንደሚገዙ ገልፀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደታክሲ ትራንስፖርት ሁሉ ዳቦ ለመግዛትም ሰልፍ መያዝ የግድ ሆኗል ይላሉ፡፡ ከዚህም የባሰው ግን ለረጅም ደቂቃዎች ከተሰለፉ በኋላም ዳቦ አልቋ

የሲዳማ ዞን የደኢህዴን ካድሬዎች የሲኣን/ መድረክን የሃዋሳ ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በሃዋሳ ከተማ ሰብሰባ ጠርተው እንደነበር ተሰማ

የሲዳማ ዞን የደኢህዴን ካድሬዎች የሲኣን / መድረክን የሃዋሳ ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በሃዋሳ ከተማ ሰብሰባ ጠርተው እንደነበር ታውቋል። በሃዋሳ ከተማ  በተካሄደው በዚህ ሰብሰባ ላይ በዞኑ ያለውን የክረምት የግብርና ኣካሄድ እና ኣያያዝን የተመለከተ እንድሁም የሲኣን ሰላማዊ ሰልፍ በዋና ኣጄንዳነት ተይዘው የዞኑ ኣመራሮች ተወያይቶበታል። በመድረኩ ላይ ለሃዋሳው ሰላማዊ ሰልፍ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፤ በሲኣን ሰላማዊ ሰልፍ የነበረው የህዝብ ተሳትፎ ደኢህዴንን እንዳሳሰበውም በምገልጽ ሁኔታ የድርጅቱን የህዝብ ኣያያዙን ገምግሟል። በሰብሰባውም ላይ የዞኑ ህዝብ የኢህኣዴግን መስመር ጥሩነት እንድቀበል በደንብ ማስተማር እንደምገባ እና ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች በተለይ ሲኣን ለህዝቡ እንደማይጠቅም ኣስረግጠው ለህዝቡ ልነገረው እንደምገባ ተመክረዋል። ሲኣን በሲዳማ ዞን ብቻ ሳይሆን በፌደራል ደረጃ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት መሆኑን በማስረገጥ ላይ መሆኑ መገንዘባቸውን ያመለከቱ ሲሆን፤ የሲኣን ከሌሎች ኣገር ኣቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በማበር የሚያደርገው እንቅስቃሴ እና መጠናከር የደኢህዴንን ህልውና ኣደጋ ላይ እንደምጥል በማመን ደህዴንን የማጠናከር ስራ ካድሬዎቹ እንድሰሩ ማሳሰባቸውን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ዘጋባ ያመለክታል።