ችግር ፈጥረዋል የተባሉ ስድስት የቡና ነጋዴዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
- በተጭበረበረ ሰነድ የተላከ ቡና የተሸጠበት ዶላር የደረሰበት እየተመረመረ ነው በቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸም ችግሮች ላይ ለመምከር በተጠራው ስብሰባ ላይ ስድስት ታዋቂ የቡና ላኪዎች የችግሩ መስንዔዎች ናቸው በሚል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡ ባለፈው ሐሙስ በንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ሰብሳቢነት በተካሄደው ስብሰባ 86 ከፍተኛ ቡና ላኪዎች ብሶት የተሞላበት ግልጽ ውይይት ማካሄዳቸውን ስብሰባውን የተካፈሉ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸም ደካማነት መንስዔ ናችው የተባሉት ስድስት ታዋቂ ቡና ላኪዎች በግልጽ ጣት እንደተቀሰረባቸውና በመጨረሻም ይቅርታ መጠየቃቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ስድስቱ ቡና ላኪዎች ሙለጌ፣ ሆራ ትሬዲንግ፣ ትራኮን ትሬዲንግ፣ ከማል አብደላ ቡና ላኪ፣ ለገሰ ሸሪፍ ቡና ላኪና አልታ አግሪ ቢዝነስ ናቸው ተብሏል፡፡ እነዚህ ቡና ላኪዎች ላይ የቀረበው ቅሬታ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ በውድ ዋጋ ቡና እየገዙ በዓለም ገበያ በርካሽ ይሸጣሉ የሚል ነው፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ይህንን የሚያደርጉት በውድ ገዝተው እየከሰሩ የሚሸጡት ከውጭ የሚመጣውን የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ ለሚያስገቡ ሸቀጣ ሸቀጦች እንዲጠቀሙበት ስለሚፈቀድ ነው ተብሏል፡፡ ነጋዴዎቹ በዚህ አካሄድ በቡናው ንግድ የከሰሩ ቢመስልም፣ ከውጭ በሚያስገቧቸው የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች እንደሚያካክሱ ተገልጿል፡፡ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ እነዚህን ጉዳዮች በስብሰባው ላይ ሲያነሱ ከቡና ላኪዎች ቅሬታ ቀርቦላቸዋል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ስድስት ቡና ላኪዎች ቡና በውድ ዋጋ እየገዙ በርካሽ ሲሸጡ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በዚህም በርካታ የቡና ነጋዴዎች ትክክለኛ ዋጋ በጨረታ አቅርበው ማሸነፍ ባለመቻላቸው ለኪሳራ ተዳርገዋል፡፡ ነገር ግን መ