Posts

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የምደባ ማስተካከያዎች ችግር እየፈጠሩ መሆኑ ተገለፀ

Image
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ. ) ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚመደቡበት ወቅት የሚደረጉ ማስተካከያዎች ችግር እየፈጠረብን ነው አሉ ዩንቨርስቲዎች። ዛሬ እዚህ አዲስ አበባ ላይ ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪጅስትራር የተውጣጡ ባለሙያዎች ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር እየተወያዩ ነው። በውይይቱ ፥ የትምህርት ክፍሎች ካላቸው አቅም በላይ እና በታች የተማሪ ቁጥር መመደብ እንደ ክፍተት ተነስቷል ። ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጓቸው አካል ጉዳተኞች ፤ ሴቶች እና ሌሎችም መረጃን በአግባቡ ባለመሙላትም የሚፈጠሩ ክለሳዎች ፥ ዩንቨርስቲዎችን ለተጨማሪ ስራና የጊዜ ብክነት እየዳረጉ ስለሆነ ሊቀረፍ ይገባል ብለዋል። የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሪክተር አቶ አርአያ ገብረ እግዚአብሄር በበኩላቸው ፥ የተነሱትን ሀሳቦች በመያዝ ለቀጣይ ምደባ የተሻለ ነገር ለመስራት አልሞ የተዘጋጀ መድረክ በመሆኑ እንደ ግብአት ወስደን የተሻለ ጥራት ያለው ስራ ለመስራት እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል። በውይይቱ የተማሪዎች ምደባ አፈፃፀም መመሪያ ማሻሻያ ላይ ውይይት ይደረጋል።

Parliament approves loan agreements worth USD half a billion

The House of People’s Representatives approved loan agreements worth USD half-a-billion on Tuesday, secured from various international financiers for the implementation of vital countrywide projects. The major project areas include road construction, education, sustainable land use management and development schemes. The financing agreements that were signed by the Ministry of Finance and Economic Development (MoFED) and various international institutions, notably the OPEC Fund for International Development (OFID), the Bank of Arab Development and Economic for Africa (BADEA), the Saudi Development Fund (SDF), the International Development Association, and the African Development Bank (AfDB). According to MoFED in documents presented before the House, the loans are to finance projects such as Modjo-Hawassa highway, the Arba Rakati-Gelemso Micheta road, the Second General Education Quality Improvement Project II, and the Sustainable Land Use Management Project II

የሲዳማ ተረቶች

Image
ሲዳማ ዞን የሲዳማ ተረቶች የተሰበሰቡት በየካቲት 1989 ዓ.ም. አዋሳ ላይ በተረደጉት ማሰባሰቦች ሲሆን ይህም የተሳካው በወቅቱ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ በነበሩት በአቶ አክሊሉ እገዛ ነበር፡፡ ተረቶቹ ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎሙት በብሪቲሽ ካውንስሉ ማይክል አምባቸው ነበር፡፡ የሲዳማ ቤት አዋሳ አካባቢ ሁሉም ተረቶች የተተረኩት በአበበ ከበደ ነው፡፡ ከእነዚህ ተረቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ታሪኮች በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተተረኩ ቢሆንም በአቶ አበበ የተነገሩቱ በልዩ ሁኔታ የተተረኩ በመሆኑ የተራኪውን ድንቅ የተረት አነጋገር ጥበብ ያንጸባረቁ ነበሩ፡፡

ከአዲስ አበባ በሃዋሳ ኣድርጎ እስከ ሞምባሳ የሚዘረጋውን መንገድ ኢትዮጵያና ኬንያ እያፋጠኑ ነው

Image
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ. ) አፍሪካን እርስ በእርስ የሚያገናኘው መስመር አካል የሆነው መንገድ ከኬፕታውን እስከ ግብጽ ሲደርስ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኝ የአፍሪካ ሀገራትን  ያቋርጣል፡፡ የሞምባሳ-ናይሮቢ-አዲስ አበባ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትም የዚህ የአፍሪካ ሀገራትን  በመንገድ እርስ በእርስ የማስተሳሰር ዓላማ አንድ አካል ነው፡፡ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱን ኬንያ ከሞምባሳ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ድረስ እንዲሁም ኢትዮጵያ ደግሞ ከ ሞያሌ  ድንበር  እስከ ዋና ከተማዋ እየሰሩ ነው፡፡ 500 ኪሎ ሜትር ለሚረዝመው መንገድ የሚያስፈልገው 5.3 ቢሊዮን ብር በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እንደሚለው የዚህ መንገድ ሲቪል ስራዎች በቅርቡ እንደሚጀመር ነው የገለጸው፡፡ የሞምባሳ ናይሮቢ አዲስ አበባ ከፍተኛ መንገድ ሲጠናቀቅ በሁለቱ ሐገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ በጎርጎሮሳውያኑ 2017 በ200 በመቶ ያሳድገዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዘገበው ኢሬቴድ ነው።

በልማትና በወረራ መካከል የሚዋልለው የእርሻ መሬትና የአርሶ አደሩ እንባ

በቶፊቅ ተማም     የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አንድ አካል በማድረግ የጀመረው ሰፋፊና ለም የእርሻ መሬቶችን ለውጭ አገር ባለሀብቶች በስፋት መስጠት መጀመሩ, ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተቃውሞ ካስነሱበት የኢኮኖሚ ዕርምጃዎች አንደኛው ሆኖ በመዝለቅ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ተቃውሞው ከተለያዩ አካላት እንደቀጠለ ቢገኝም፣ በመንግሥት በኩል ያሉ ቅሬታዎችን ከመፍታት ይልቅ የሚነሱት ችግሮች በአብዛኛው መሠረት ቢስ ናቸው ሲል እየሞገተ ነው፡፡ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ልዩነት ርቀት በጣም እየሰፋ ከመጣ የቆየ ሲሆን፣ መንግሥት ትችቶችን በተለመለከተ በሚያቀርበው ምክንያት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ልማት የማያስደሰታቸው አካላት ትችት ነው ሲል ቢያጣጥልም፣ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መምጣታቸውን ቀጥለዋል፡፡ መንግሥት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን በውጭ ባለሀብቶች እንዲለሙ የማድረጉ አቅጠጫ ዋነኛ ዓላማ አገሪቱ ካላት 112 ሚሊዮን ሔክታር ውስጥ ከ 60 እስከ 70 ሚሊዮን ሔክታር የሚሆነው ተስማሚ የሆነ ቴክኖሎጂና አመራር ቢያገኝ ሊለማ የሚችል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካትና ሰፊ መሠረተ ልማትና ሰፊ የሆነ ካፒታል የሚጠይቅ በመሆኑ፣ እነዚህን ሰፋፊ መሬቶች ለማልማት የሚያስችል ካፒታል፣ ዕውቀትና ከፍተኛ አቅም ላላቸው ባለሀብቶች የአገሪቱን ድንግል መሬት (Prime Soil) በቅናሽ ዋጋ በሊዝ በማከራየት ለባለሀብቶች ቢሰጥም፣ የባለሀብቶቹ ኢንቨስትመንት የታሰበውን ያህል ውጤታማ ሊሆን አልቻለም፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወስደው ወደ ሥራ ከገቡት መካከል ብዙ የተባለላቸው የቻይና፣ የህንድና የሳዑዲ ኩባንያዎች ያስመዘገቡት ውጤት አናሳ መሆኑ ሲሆን፣ ለዚህም ካሩቱሪ