በሃርቤ ጎና ወረዳ በአንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ቀርከሃ ልለማ ነው
ፋብሪካው በሲዳማ ዞን በአንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ቀርከሃ ለማልማት ዝግጅት እያደረገ ነው በኢትዮጵያዊ ባለሀብትና በአሜሪካ የልማት ድርጅት ትብብር የተቋቋመው « አፍሪካን ባንቡ » የተሰኘው የቀርከሃ ፋብሪካ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቀርከሃ ጣውላ በማምረት ወደ ጀርመንና የተለያዩ የዓለም ሀገራት ለመላክ ማቀዱን አስታወቀ፡፡ የአፍሪካ ባምቡ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ካሊድ ዱሪ የፋብሪካውን በይፋ ስራ መጀመር አሰመልክቶ ከትናንት በስቲያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሲዳማ ዞን አርቤጎና ወረዳ ውስጥ በ 250 ሚሊዮን ብር የተገነባው ይኸው የቀርከሃ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በየአመቱ 140 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ ለማስገባት አቅዷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከምርቱ 52 በመቶውን ወደ ጀርመን ለመላክ ስምምነት ፈጽሟል፡፡ « በሀገሪቱ የደን ሽፋን ካለፉት 40 አመታት ወዲህ እየተመናመነ በመምጣቱ የእንጨት ጥሬ እቃ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ አጋጥሟል » ያሉት ስራ አስኪያጁ፣ በየአራት ዓመቱ ራሱን በሚተካው ቀርከሃ ይህን የጥሬ ዕቃ አቅርቦቱን በመሸፈን ከቀርከሃ ጣውላ እንደሚመረት ነው ያስታወቁት። ከሀገሪቱ የደን ሽፋን ከ 50 በመቶ በላይ የሚሆነው ቀርከሃ መሆኑንም አስታውቀዋል። እንደ ስራ አስኪያጁ ገለጻ፤ የፋብሪካው ዋነኛ ጥሬ ዕቃ የሆነውን ቀርከሃ በሲዳማ ዞን አርቤ ጎና ወረዳ በአንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ለማልማት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በአሁኑ ወቅትም 50 ሺ ችግኞችን በማፍላት ለአርሶ አደሮች እየተከፋፈለ ይገኛል። በየአመቱም አርሶ አደሮቹ የሚያመረቱትን ቀርከሃ ከ 30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ እየገዛ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡አርሶ አደሮ