የሃዋሳ ኤርፖርት የግንባታ ቦታ ለውጥ እና መዘዙ
የኤርፖርቱ ግንባታ ቦታ ለውጡን ተከትሎ የሞሮቾ ሾንዶላና ቀበሌ እና የኣከባቢው ቀበሌያት ነዋሪዎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። የሃዋሳ ከተማ በተለይ ካለፉት ጥቂት ኣመታት ወዲህ ከፍተኛ ሁለ ገብ እድገት በማስመዝገብ የነዋሪዎቿን ብቻ ሳይሆን የኣገር ውስጥ እና የውጭ ኣገር ዜጎችን መሳብ መጀመሯ የምታወቅ ነው። ከተማይቱ ከኣዲስ ኣበባ በቅርብ ርቀት ላይ መገኘቷ እና ምቹ የምድር ትራንስፖርት ፍሰት ያላት መሆኑ ኤርፖርት ሳይኖራት እንድትቆይ ምክንያት ሆኗል። የሆነ ሆኖ ሰሞኑን የመንግስት ዜና ኣውታሮች ለዘመናት ያለ ኤርፖርት የቆየችው ይችው የሲዳማ መዲና ሃዋሳ፤ የኤርፖርት ባለበት እንድትሆን ኤርፖርት ልገነባላት መሆኑን ማብሰራቸውን ተከትሎ በርካታ የሃዋሳ ነዋርዎች እንድሁም ኣጠቃላይ ሲዳማውያን ደስታቸው በተለያየ መንገድ ስገልጹ ከርመዋል። በኣሁኑ ጊዜ በሲዳማ የኤርፖርቱ ግንባታ ቁጥር ኣንድ የመወያያ ኣርዕስት ሲሆን፤ በተለይ የቦታ መረጣው የብዙዎቹን ቀልብ የሳበ ጉዳይ ሆኗል። ለሃዋሳው ኤርፖርት ግንባታ ከዚህ በፊት በሸቤዲኖ ወረዳ ውስጥ ሞሮቾ ሾንዶላና ቀበሌ እና በኣከባቢው ያለው ቀበሌ ተመርጦ የነበረ ቢሆንም፤ በኣሁኑ ጊዜ ቦታው ተቀይሮ በሃዋሳ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ኡዶ ዎጣጤና ሳማ ኤጀርሳ ቀበሌ እንዲዛዎር ተደርጓል። እንደሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ዘጋባ መሰረት የቦታ ለውጡ የተደረገው ከሞሮቾ ሾንዶላ ቀበሌ እና ከሌሎች በኣከባቢው ካሉ ቀበሌያት ለኤርፖርት ግንባታ ሲባል የምነሱ ሰዎች ቁጥር ብዙ በመሆኑ ለምነሱ ሰዎች እና ለመሬት ይዞታ ብሎም ለንብረት የምከፈለው ካሳ ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት ለካሳ የምከፍለውን ገንዘብ ለማስቀረት ሌላ ኣማራጭ ቦታ መፈለግ የግድ ሰላሆነበት መሆኑ ታውቋል።